“ሉሲ ሞርሊ እና ቤተሰቦቿ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ሉሲ ሞርሊ እና ቤተሰቦቿ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ህዳር 1830 (እ.አ.አ)
ሉሲ ሞርሊ እና ቤተሰቦችዋ
ብዙዎች አመኑ እንዲሁም ተጠመቁ
አንድ ቀን፣ የ15 ዓመቷ ሉሲ ሞርሊ ጎረቤቷ አቢግኤል ዳኒልስን ልብስ ስትሠፋ እየረዳቻት ነበር። በሥራ ላይ እያሉም፣ በሩ ሲንኳኳ ሰሙ፡፡ ሶስት ሚስዮናውያን ነበሩ፡፡ አቢግኤል እንዲገቡ ጋበዘቻቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክት እንዲያካፍሉ እንደላካቸው ተናገሩ።
ቅዱሳን፣ 1፥102–3
ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ ይሆን ዘንድ ኢየሱስ እንደጠራው ሠዎቹ ለአቢግኤል እና ለሉሲ ነገሯቸው። በተጨማሪም፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን ነገሯቸው።
ቅዱሳን፣ 1፥103
አቢግኤል በመናደዷ ሉሲ ተገረመች። ሚስዮናውያን ቤቷን ለቀው እንዲወጡ አደረገች።
ቅዱሳን፣ 1፥103
እነዚህ ሚስዮናውያን የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደሆኑ አውቃ ነበር። መንገዱ ላይ ያሉትን ቤተሰቦቿን እንዲጎበኙ ነገረቻቸው። “አባቴ የሚኖረው ከዚህ አንድ ማይል ርቀት ላይ ነው” አለቻቸው። “ወደዚያ ሂዱ ትመገባላችሁ እንዲሁም ይንከባከቧችኋል።”
ቅዱሳን፣ 1፥103–4
ሉሲ ትክክል ነበረች። ሚስዮናውያኑ በሞርሊ ቤተሰብ እርሻ ውስጥ ጥሩ ምግብ ተመገቡ። የሉሲ ወላጆች የሲድኒ ሪግደን ጓደኞች ነበሩ። ኢየሱስ፣ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ለሌሎች እንዲያካፍሉ እንደሚፈልግ ያምኑ ነበር። እነርሱን እና ጓደኞቻቸውን ያስተምሩ ዘንድ ሚስዮናውያኑን ጋበዟቸው።
ቅዱሳን፣ 1፥104
በዚያ ምሽት፣ እኩለ ሌሊት አካባቢ 17 ሰዎች ተጠመቁ። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ 50 ተጨማሪ ሰዎች ከሚስዮናውያን ለመስማት ወደ ሞርሊ እርሻ መጡ፣ ከዚያም መጠመቅ ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ። የሉሲ ጓደኛ አቢግኤል ዳኒኤልስ እንኳ ስለ ሚስዮናውያን ያነበራትን ሀሳብ ቀይራ ነበር። እርሷና ባለቤቷ ቤተክርስቲያኗን ለመቀላቀል ወሠኑ።
ቅዱሣን፣ 1፥105፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥25፣ 37