በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሐዋርያት በእንግሊዝ አገር ሚስዮን አገለገሉ


“ሐዋርያት በእንግሊዝ አገር ሚስዮን አገለገሉ” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ሐዋርያት በእንግሊዝ አገር ሚስዮን አገለገሉ” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሐምሌ 1838–ሐምሌ 1841 (እ.አ.አ)

ሐዋርያት በእንግሊዝ አገር ሚስዮን አገለገሉ

በጌታ ቃል ኪዳን ማመን

ጆሴፍ ስሚዝ የቤተክርስቲያኗን ሐዋርያት ለሚስዮን አገልግሎት ወደ እንግሊዝ አገር እንዲሄዱ ለመጥራት ራዕይ እየተቀበለ።

ለጆሴፍ ስሚዝ በተሰጠ ራዕይ፣ ጌታ ሐዋርያትን ከውቅያኖስ ባሻገር ወደ እንግሊዝ አገር በሚስዮን እንዲያገለግሉ ይጠራቸዋል። ምንም እንኳን የሐዋርያት በጣም ርቀው መሄድ ከባድ ቢሆንበትም ጆሴፍ በጌታ ታመነ። ቤተሰቦቻቸውን ትተው መሄድ ለሐዋርያትም ከባድ ነበር። ነገር ግን ጌታ እንደሚባርካቸው ቃል ገባ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 118

ሒበር ኪምባል እና ቤተሰቡ።

ሒበር ሲ. ኪምባል እና ሚስቱ ቪላቴ ታዳጊ ቤተሰብ ነበራቸው። ከተወለደ አንድ ወር ብቻ የሆነ ልጅ ነበራቸው። ብዙዎቹ የቤተሰባቸው አባላት በጠና ታመው ነበር።

ቅዱሳን1፥405

ብሪገም ያንግ ሚስዮን ለማገልገል ለመሄድ ሲዘጋጅ።

ብሪገም ያንግም እንዲሁ ትምሞ ነበር፣ ቤተሰቡም ድሃ ነበረ። ነገር ግን የብሪገም ሚስት ሜሪ አን፣ “ሂድ እና በምስዮን አገልግል፣ እናም ጌታ ይባርክሃል” አለችው።

ቅዱሳን1፥404-5

ብሪገም ያንግ ከሒበር ሲ. ኪምባል ጋር በቤቱ ሲቆይ

ብሪገም መሄድ ጀመረ፣ ነገር ግን ወደ ሒበር ቤት በደረሰ ጊዜ፣ በጣም ደካማ ሆኖ መራመድ አቃተው። ከሒበር ቤተሰብ ጋር ለጥቂት ቀናት ቆየ።

ቅዱሳን1፥405

ሜሪ አን ያንግ ብሪገምን እና ሒበርን እየተንከባከበች።

ብሪገም ደህና እንኪሆን እና እሱና ሒበር ተሽሏቸው እስኪሄዱ ድረስ ለመንከባከብ ሜሪ አን መጣች። ሁለቱም በጣም ቢደክሙም ወንጌልን ለመስበክ ፍላጎት ነበራቸው።

ቅዱሳን1፥405

ብሪገም እና ሒበር በሚስዮን ለማገልገል እየሄዱ።

ሒበር እና ብሪገም ሚስቶቻቸውን ተሰናብተው በሠረገላ ጀርባ ላይ ወጡ። በጣም የታመሙና ድሃ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን ትተው ሊሄዱ በመሆኑ ክፉኛ ተሰምቷቸው ነበር። ሰረገላው እየሄደ እያለ ሒበር ለብሪገም “ይህ በጣም ከባድ ነው” አለው። ቤተሰቦቻቸው ድፍረት እንዲሰማቸው ለመርዳት ፈለገ። ሒበር ሠረገላውን የሚነዳው እንዲያቆም ጠየቀው።

ቅዱሳን1:405–6

ብሪገም እና ሒበር ለመሰናበት ቆመው።

ቤት ውስጥ የነበረቸው ቪላቴ ድምጽ ሰማች። ሜሪ አን ወደቆመችበት በር መጣች። ሒበር እና ብሪገም ከሰረገላው ጀርባ ቆመው ኮፍያቸውን በአየር ላይ እያውለበለቡ አዩዋቸው እና “እንደሰት! እንደሰት! ለእስራኤል እንደሰት!” በማለት ጮሁ። ሴቶቹም “ደህና ሁኑ! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!” በማለት መለሱ።

ቅዱሳን1፥406

ብሪገም እና ሒበር በእንግሊዝ አገር እየሰበኩ።

በውቅያኖስ ላይ ረጅም ጉዞ ካደረጉ በኋላ ሒበር እና ብሪገም ወደ እንግሊዝ አገር ደረሱ። ከሌሎች ሐዋርያት ጋር፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ብዙ ሰዎችን አስተማሩ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተጠምቀው የአዳኙን ቤተክርስትያን ተቀላቀሉ።

ቅዱሳን1፥408–11

ቅዱሳን በናቩ ለመኖር እየተጓዙ።

በእንግሊዝ አገር አገር ከተጠመቁ ሰዎች መካከል ብዙዎቹ ከተማዋን እና ቤተመቅደስን ለመገንባት ወደ ናቮ ሄዱ። እነሱ በሚስዮናዊ አገልግሎት ላይ ሳሉ ጌታ የሒበርን እና የብሪገምን ቤተሰብ እንደሚንከባከባቸው የገባውን ቃል ጠበቀ።

ቅዱሳን1፥437–39