በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የማርቲንስ ቤተሰብ


“የማርቲንስ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“የማርቲንስ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሚያዝያ 1972–ህዳር 1978 (እ.አ.አ)

የማርቲን ቤተሰብ

የጌታን በረከቶች መጠባበቅ

ሄልቬሲዮ ማርቲንስ ከስራ ወደቤት እየነዳ ሲሄድ።

ሄልቬሲዮ ማርቲንስ በሪዮ ዴ ዣኔሮ፣ ብራዚል ከስራ ወደቤት እየነዳ ይሄድ ነበር። መንገዱ በመኪኖች ተሞልቶ ስለነበር የትኞቹም መንቀሳቀስ አልቻሉም። ሄልቬሲዮ ስለህይወቱ አሰበ። እርሱ ጥሩ ስራ ነበረው። ባለቤቱን ሩዳን፣ እና ሁለት ልጆቹን፣ ማርከስን እና ማሪሳን ይወዳቸው ነበር። ነገር ግን እርሱ አንዳች ነገር እንደጎደለው ተሰምቶታል።

ቅዱሳን4፥229–30

ሄልቬሲዮ ለጸሎት ተንበርክኮ።

ሄልቬሲዮ ከመኪናው ወጥቶ ይጸልይ ጀመረ። እርሱም ‘’አምላኬ ሆይ፣’’ አለ፣ ‘’የት እንደሆንክ አላውቅም፣ ነገር ግን የሆነ ቦታ እንዳለህ አውቃለሁ።’’ ቤተሰቡ አንድን ነገር እየፈለገ እንደሆነ እና የእርሱን እርዳታ እንደሚሹ ለሰማይ አባት ነገረ። ከዚያም ሄልቬሲዮ ወደ መኪናው ተመለሰ እና ወደ ቤቱ እየነዳ ሄደ።

ቅዱሳን4፥230

የማርቲን ቤተሰብ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሚስዮናውያን ሰላምታ እየሰጡ።

በኋላም፣ ጌታ ከዩናይትድ ስቴትስ ሚስዮናውያንን ላከ። እነርሱም የማርቲንስን ቤተሰብ ጎበኙ። ሄልቬሲዮ እነርሱ ወደቤቱ ሰላማዊ መንፈስን እንዳመጡለት መገንዘብ ቻለ። በወቅቱ፣ ጥቁር የቆዳ ቀለም የነበራቸው ሰዎች በአሜሪካ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በመልካም እየታዩ እንዳልሆነ አወቀ። እንዲህም በማለት ጠየቀ፣ ‘’የእናንተ ሃይማኖት ጥቁሮችን እንዴት ይመለከታቸዋል?’’

ቅዱሳን4፥230–31

ሚስዮናውያን የቤተመቅደስን እና የክህነትን ክልከላዎች ለማርቲንስ ሲገልጹለት።

ሚስዮናውያን ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች መጠመቅ እንደሚችሉ ገለጹ። ነገር ግን፣ በዚያን ጊዜ፣ የአፍሪካ ዝርያ ያላቸው ጥቁር ህዝቦች ክህነትን እንዲያገኙ ወይም የቤተመቅደስ ስርዓቶች ውስጥ እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም ነበር። ሄልቬሲዮ እና ሩዳ ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎች ነበሯቸው። ሚስዮናውያኑ ጥያቂዎቹን ለመመለስ የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ።

ቅዱሳን4፥231

የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ኦ. ማኬይ ለጸሎት ተንበርክከው።

ለአያሌ ዓመታት፣ ነቢያት የክህነት እና የቤተመቅደስ በረከቶች ለሁሉም ህዝቦች መቼ መሰጠት እንዳለባቸው ጸልየዋል።

ቅዱሳን4፥71

ማርቲንስ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ለሰዎች ሰላምታን ሲሰጡ።

ሄልቬሲዮ እና ሩዳ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ሙከራን ለማድረግ ወሰኑ። በዚያ የነበሩ ቅዱሳን አፍቃሪ እና ደግ ነበሩ። የማርቲንስ ቤተሰብ በቤተክርስቲያን የተማሯቸውን ነገሮች ወደዋቸዋል።

ቅዱሳን4፥231–32

የማርቲንስ ቤተሰብ ለመጠመቅ ሲወስኑ።

አንድ ቀን፣ ከቤተክርስቲያን ወደ ቤት ሲመለሱ፣ ማርከስ ደስተኞች መስለው እንደሚታዩ ለቤተሰቡ ነገራቸው። ማርከስም ‘’ይህንን ምን እየፈጠረው እንዳለ አውቃለሁ’’ አለ። ‘’የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል።’’ የተቀሩት የቤተሰቡ አባላት ማርከስ ትክክል እንደነበር አውቀዋል። ለመጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመቀበል ወሰኑ።

ቅዱሳን4፥232

ሄልቬሲዮ እና ሩዳ የሳኦ ፖሎ ብራዚል ቤተመቅደስን እይታ እየጎበኙ።

ከዓመታት በኋላ፣ በብራዚል የነበሩ ቅዱሳን ቤተመቅደስን በመስራት ተጠምደው ነበር። የማርቲንስ ቤተሰብ ተደስተው ነበር፣ ነገር ግን ደግሞ በጣም አዝነው ነበር። ከተመረቀ በኋላ ወደ ቤተመቅደሱ ለመግባት እይችሉም ነበር። ‘’አትጨነቂ፣’’ በማለት ሄልቪሲዮ ለሩዳ ነገራት። “ጌታ ሁሉን ያውቃል።’’

ቅዱሳን4፥293–94

የማርቲንስ ቤተሰብ ከአንድ ጓደኛቸው ጋር ሲነጋገሩ።

በታማኝነት መቆየት ቀላል አልነበረም። ሰዎች በማርቲንስ ቤተሰብ ላይ ይቀልዱ ነበር። ጓደኖቻቸው እንኳን ለምን በቤተክርስቲያኑ አባልነት እንደቆዩ ሊረዱ አልቻሉም ነበር። ነገር ግን ሄልቪሲዮ እና ቤተሰቡ ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሆኑን አውቀው ነበር።

ቅዱሳን4፥251–52

ሩዳ ከሄልቪሲዮ ጋር ስለ ቤተመቅደሱ እና ስለ ክህነቱ ክልከላ ማብቃት ስትነጋገር።

አንድ ቀን፣ ሄልቪሲዮ ከስራ ወደቤት በመጣ ጌዜ፣ ሩዳ እንዲህ አለችው፣ ‘’አንድ፣ አስገራሚ ዜና አለኝ!’’ ከብዙ ጾም እና ጸሎት በኋላ፣ ነቢዩ፣ ፕሬዚዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል፣ ራእይን ተቀበሉ። ማንም፣ የቆዳ ቀለሙ ምን ይሁን ምን፣ የክህነትን እና የቤተመቅደስን ሁሉንም በረከቶች ሊያገኝ እንደሚችል እግዚአብሔር ነገራቸው።

አስተዳደራዊ አዋጅ 2ቅዱሳን4፥318–19

የማርቲንስ ቤተሰብ በቤተመቅደስ ሲያመልኩ።

የማርቲንስ ቤተሰብ እና ሌሎች ብዙዎች ለረዥም ጌዜ ጠብቀው ነበር። አሁን መጠበቁ አበቃ! ሄልቪሲዮ እና ማርከስ ክህነትን ተቀበሉ። ሄልቪሲዮ፣ ሩዳ፣ እና ልጆቻቸው እንደቤተሰብ በቤተመቅደስ በአንድነት ተሳሰሩ። አሁን እነርሱ የወንጌልን በረከቶች ሁሉ መቀበል ይችላሉ።

ቅዱሳን4፥319–21