በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የጃክሰን ቤተሰብ


“የጃክሰን ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“የጃክሰን ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ግንቦት–ህዳር 1856 (እ.አ.አ)

የጃክሰን ቤተሰብ

የእምነት እና የማዳን ጉዞ

የጃክሰን ቤተሰብ በሊቨርፑል፣ እንግሊዝ በአንድ መርከብ ተሳፈሩ።

የመጀመሪያዎቹ የቅዱሳን ስብስብ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ከሄዱ በኋላ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ቅዱሳንም እንዲሁ ሄደዋል። ረዥም መንገድ ተጉዘዋል፣ እና ጌታም ረድቷቸዋል። ጉዞውን ካደረጉ ቤተሰቦች መካከል የጃክሰን ቤተሰብ አንዱ ነበር። በእንግሊዝ የነበረውን ቤታቸውን በመተው ጽዮንን በመገንባት ቅዱሳንን ለመርዳት በመሄዳቸው ደስተኞች ነበሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥1–11ቅዱሣን2፥222–23

የጃክሰን ቤተሰብ በመርከብ እየተጓዘ።

የጃክሰን ቤተሰብ በመርከብ ውቂያኖስን ተሻገረ። ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ የሚደረገውን የጉዞ ክፍል በባቡር ተጓዙ። ቀሪውን መንገድ በእግራቸው መጓዝ ነበረባቸው።

ቅዱሳን2፥222–23

የጃክሰን ቤተሰብ የእጅ ጋሪያቸውን በመጫን ላይ እያሉ።

ምግባቸውን፣ ልብሳቸውን፣ እና ሌሎች ነገሮችን እንዲይዝላቸው አንድ ትንሽ የእጅ ጋሪ ሰሩ። አያሌ ቅዱሳን በዚህ መንገድ ነበር ጉዞአቸውን ያጠናቀቁት።

ቅዱሳን2፥223–26

የጃክሰን ቤተሰብ በእጅ ጋሪያቸው ወደ ምእራብ እየተጓዙ።

ኤልሳቤጥ እና አሮን ጃክሰን ከባዱን የእጅ ጋሪያቸውን ይጎትቱ ነበር። ልጆቻቸው ማርታ፣ ማርያም፣ እና አሮን፣ ዳግማዊም በእግር ተጉዘዋል። ይህም ከባድ ስራ ነበር። ክረምት ከመግባቱ በፊት ወደ ሸለቆው ለመድረስ ተስፋ አድርገው ነበር። ነገር ግን የበልግ ወቅት ሲመጣ፣ አሁንም ብዙ ርቀት መጓዝ ነበረባቸው። ቅዝቃዜው ጀምሯል፣ ምግብም እያለቀባቸው ሄዷል።

ቅዱሳን2፥223–26229231–32

ብሪገም ያንግ ወደ ምእራብ እየተጓዙ ያሉትን ቅዱሳን እንዲረዷቸው በሶልት ሌክ ያሉትን ቅዱሳን ጠየቁ።

በሶልት ሌክ ሲቲ፣ ወደ ሸለቆው እየመጡ ስለነበሩት ቅዱሳን ብሪገም ያንግ አውቁ። እርሳቸውም ስለእነርሱም ተጨንቀው ነበር። በሚቀጥለው ቀን በቤተክርስቲያን ላይ፣ እነዚህ ቅዱሳን ችግር ላይ መሆናቸውን ለሁሉም ነገሯቸው። ቅዱሳን በሚያስፈልጓቸው ነገሮች ሰረገላዎቹን እንዲሞሉ ጠየቋቸው። ‘’ሂዱ እና እነዚያን ሰዎች አምጧቸው፣” አሉ።

ቅዱሳን2፥229–30

በሶልት ሌክ ያሉ ቅዱሳን ወደ ምእራብ እየተጓዙ የነበሩትን ቅዱሳን ለመርዳት ቁሳቁሶችን እያሰባሰቡ።

በስብሰባው የነበሩ ሴቶች የሞቁ ካልሲዎቻቸውን በማውለቅ በሰረገላው ላይ አስቀመጡ። ሌሎችም ምግባቸውን፣ የብርድ ልብሶቻቸውን፣ ጫማዎቻቸውን እና ልብሶቻቸውን ሰጡ። ከሁለት ቀናት በኋላ፣ ከ50 የሚበልጡ ወንዶች እና 20 ሰረገላዎች ሸለቆውን ትተው ለእርዳታ ሄዱ።

ቅዱሳን2፥230

አሮን ጃክሰን እና ሌሎች ቅዱሳን የኖርዝ ፕሌት ወንዝን እየተሻገሩ።

የጃክሰን ቤተሰብ በእግር እየተጓዙ፣ በረዶ መጣል ጀመረ። አሮን በጣም ታመመ። ለእርሱ በእግር መሄድ ከባድ ነበር። ቅዱሳን በረዷማውን ወንዝ መሻገር ነበረባቸው፣ እና ይህም አሮንን ይበልጥ አደከመው። በዚያ ሌሊት፣ አሮን ሞተ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ቤተሰቡ ያለእርሱ ጉዞአቸውን መቀጠል ነበረባቸው።

ቅዱሳን2፥232–34

የጃክሰን ቤተሰብ እና ሌሎች ቅዱሳን በበረዶ ውስጥ የእጅ ጋሪያቸውን እየጎተቱ።

በሚቀጥለው ቀን፣ በዛ ያለ በረዶ መሬት ላይ ነበር። የጃክሰን ቤተሰብ እና ሌሎች ቅዱሳን በበረዶ መሃል የእጅ ጋሪያቸውን ይጎትቱ እና ይገፉ ነበር ። እግዚአብሔር ይረዳቸው ዘንድ በየእለቱ ይጸልዩ ነበር ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥29ቅዱሳን2፥234–35

ኤልሳቤጥ ጃክሰን ስለባሏ ህልም እያየች።

በአንድ ሌሊት፣ ኤልሳቤጥ ስለልጆቿ ትጨነቅ ነበር። ርቧቸው እና በርዷቸው ነበር። እስከ ሶልት ሌክ ሸለቆ መመጓዝ በህይወት ይደርሱ ይሆን? አንቀላፋች እና በህልሟም አሮንን አየች። እርሱም፣ ‘’ደስ ይበልሽ፣ ኤልሳቤጥ’’ አለ። እርዳታ እየመጣ እንደነበርም ነገራት።

ቅዱሳን2፥235–36

ሰዎች ቅዱሳንን ለመርዳት ሲደርሱ።

አሮን ትክክል ነበር። ወዲያውም፣ ከሶልት ሌክ ሲቲ የመጡ ሰዎች ከነሰረገላዎቻቸው ደረሱ። ለቅዱሳን ምግብ እና አልባሳት ሰጧቸው። ቅዱሳንም ተደሰቱ እናም ሰዎቹን በሳቅ ተቀበሏቸው እንዲሁም አቀፏቸው። መዝሙር ዘመሩ እናም ጸሎቶቻቸውን ስለመለሰላቸው የሰማይ አባትን አመሰገኑ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥28ቅዱሳን2፥236

ተጓዥ ቅዱሳን በመጨረሻ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ሲደርሱ።

በመጨረሻ ወደ ሸለቆው ሲደርሱ፣ እለቱ እሁድ ነበር። ብሪገም ያንግ በሶልት ሌክ ሲቲ ለነበሩ ቅዱሳን ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ ይልቅ፣ ለደረሱት ቅዱሳን አቀባበል እንዲያደርጉላቸው ነገሯቸው። በቅዝቃዜ እና በድካም ውስጥ ለነበሩት ቅዱሳን ሰላምታ አቀረቡላቸው እናም በየቤቶቻቸው እንዲቆዩ ግብዣን አቀረቡላቸው።

ቅዱሳን2፥239–40