“ጆሴፍ እና ስድኒ ጥቃት ደረሰባቸው፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አአ)]
“ጆሴፍ እና ስድኒ ጥቃት ደረሰባቸው፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
የካቲት 1832 (እ.አ.አ)
ጆሴፍ እና ስድኒ ጥቃት ደረሠባቸው
ብስጩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ነቢይ ስራ ለማስቆም ሞከሩ
አንዳንድ ሰዎች ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ሰማይ አባት፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና ስለ ሰማይ እያስተማረ የነበረውን ወደው ነበር። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ እርሱ ያስተማረውን አልወደዱም ነበር። ጥቂት ሰዎች ተበሳጭተዋል እና ጆሴፍን ከማስተማር ለማስቆም ፈልገዋል።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥149–50
በአንድ ምሽት ጆሴፍ በጉዲፈቻ ከሚያሳድጓቸው መንትዮች አንዱን በመንከባከብ አምሽቶ ነበር። ህጻኑ በጣም ታሞ ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥150
ኤማ ህጻኑን ወሰደች እና ጆሴፍ እንዲተኛ ነገረችው። እርሱ በጠዋት መስበክ ነበረበት። በመጨረሻም፣ ጆሴፍ እና ኤማ ሁለቱም እንቅልፍ ወሰዳቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥150
በድንገት፣ በሩ ተበረገደ፣ እና የተበሳጩ ሰዎች በአንድነት ወደ ቤቱ ሮጠው ገቡ። ሰዎቹ ጆሴፍን በክንዱ፣ በእግሩ፣ እና በጸጉሩ ሲይዙት፣ ኤማ ጮኸች። ከቤት ውጪም ጎትተው አስወጡት።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥150–51
ጆሴፍ ከሰዎቹ ራሱን ለማስለቀቅ ሞከረ፣ ነገር ግን አጥብቀው ይዘውታል። ሰዎቹ ስድኒ ሪግደንንም እንዲሁ ከቤት ጎትተው እንዳወጡት ጆሴፍ ተመለከተ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥151
ሰዎቹ የጆሴፍን ልብሶች ቀደዱ እና በቆዳው እና በጸጉሩ ላይ የፈላ እና የሚያጣብቅ ሬንጅ አፈሰሱበት። ከዚያም በላባ ሸፈኑት እና ሸሹ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥152
ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ፣ ጆሴፍ ወደ ቤቱ ወደኋላው እየተደናፈቀ ሄደ። ኤማ ጆሴፍን ባየችው ጊዜ ተደናገጠች። በአቅራቢያው ይኖሩ የነበሩ ጓደኞች የሆነውን ሰሙ እና መጥተው ለመርዳት ተቻኮሉ። ኤማ ከጆሴፍ ቆዳ ላይ ሬንጁን ፈገፈገች። በቀረው የሌሊቱ ጊዜ፣ ኤማ እና ጓደኞችዋ ጆሴፍን እና ስድኒን በመንከባከብ ረዱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥5፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥153
በሚቀጥለው ቀን፣ ጆሴፍ በታላቅ ህመም ላይ ነበር። ነገር ግን ለብሶ ተነሳ እና ለተሰበሰቡ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማረ። እርሱን ሲያጥቁ ከነበሩ አንዳንድ ሰዎች ሲያስተምር ያደምጡት ነበር፡፡ በዚያም እለት ረፋድ ላይ፣ ጆሴፍ ሶስት ሰዎችን አጠመቀ። ምንም እንኳ ሰዎች ሊያስቆሙት ቢሞክሩም፣ እርሱ የእግዚአብሔርን ስራ መስራቱን ቀጠለ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥153