በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች


“ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች፣ ” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 እ.አ.አ)

“ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች፣ ” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1841–1843 (እ.አ.አ)

ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች

በጌታ በእምነት መራመድ

ጄን ማኒንግ እየተጠመቀች።

ጄን ማኒንግ እና ቤተሰቧ አንዳንድ ሰዎች በማይወዷቸው ስፍራ እና በቆዳቸው ቀለም ምክንያት እንደሚገባ በላስተናገዷቸው ቦታ ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን፣ ጄን የአንድን ሚሲዮናዊ ትምህርት ሰማች። የእርሱም መልእክት እውነት እንደነበር አወቀች። ወዲያውም በቀጣዩ እሁድ፣ ተጠመቀች።

Saints [ቅዱሳን]1፥500–501

ጄን እና ቤተሰቧ ጉዞአቸውን ወደ ናቩ ሲጀምሩ።

የጄን ቤተሰብም እንዲሁ በቤተክርስቲያኗ ተቀላቀሉ። ጌታ ቅዱሳኑ በአንድነት በናቩ እንዲሰበሰቡ ፈልጎ ነበር። ጄን ጌታን ወደደች። እርሷ እና ቤተሰቧ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር አብረው መሆንን ፈለጉ። በመሆኑም ጉዞአቸውን ወደ ናቩ ጀመሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥25Saints [ቅዱሳን]1፥501

ጄን እና ቤተሰቧ በጀልባ እንዳይጓዙ ተከለከሉ።

ከፊሉን መንገዳቸውን፣ በጀልባ ተጓዙ። በጀልባው የነበሩ አብዛኞቹ ሰዎች በጉዞአቸው መጨረሻ ገንዘባቸውን ይከፍሉ ነበር። ነገር ግን ጥቂት ግለሰቦች የጄንን ቤተሰብ በመጀመሪያ መክፈል እንዳለባቸው ነገሯቸው። በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም ነበር። ሰዎቹም ከጀልባው እንዲወርዱ አደረጓቸው፣ እና ጀልባውም ያለእነርሱ ሄደ።

Saints [ቅዱሳን]1፥501

ጄን እና ቤተሰቧ በእግራቸው ወደ ናቩ ተጓዙ።

የጄን ቤተሰብ 800 ማይሎችን ወይም 1300 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ ነበረባቸው። ጥልቅ የሆነን ወንዝ ያለድልድይ ማቋረጥ ነበረባቸው። ውጪ መተኛትም ነበረባቸው። የአየር ጸባዩም በአብዛኛው ቀዝቃዛ ነበር። ነገር ግን የጄን ቤተሰብ ወደ ናቩ ለመድረስ ቆርጠው ነበር። በጉዞአቸውም ወቅት በመዘመር ራሳቸውን ያነቃቁ ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥501505–6

ጄን የቤተሰብ አባላትን ስትንከባከብ።

ጄን እና ቤተሰቧ ጫማቸው እስኪያልቅ ተጉዘዋል እና እግራቸውም ተጎድቷል። እነርሱም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በጸለዩ ጊዜ፣ እግራቸውን ፈውሶላቸዋል።

Saints [ቅዱሳን]1፥505

ጄን እና ቤተሰቧ ህመምተኛን ልጅ እየረዱ።

በጉዞአቸው ወቅት ያገኟቸውን ሰዎች ረድተዋቸዋል። በእምነታቸው ምክንያት የታመመን ልጅ ለመፈወስ ረድተዋል።

Saints [ቅዱሳን]1፥505–6

ኤማ እና ጆሴፍ ጄንን በቤታቸው ተቀበሏት።

በመጨረሻም፣ ጄን እና ቤተሰቧ ወደ ናቩ ደረሱ! ደክመው ነበር እና የሚያርፉበትም ስፍራ አስፈልጓቸው ነበር። በመሆኑም ወደ ኤማ እና ወደ ጆሴፍ ቤት ሄዱ። ጆሴፍም ያለፉበትን ሁሉ ከሰማ በኋላ፣ ለጄን እንዲህ አላት፣ ‘’እግዚአብሔር ይባርክሽ። አሁን በጓደኞችሽ መካከል ነሽ።’’ ጆሴፍና ኤማ ጄን አብራቸው እንድትኖር ጋበዟት።

Saints [ቅዱሳን]1፥506