“ጆሴፍ እና ሃይረም ህይወታቸውን ለወንጌሉ ሰጡ” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ጆሴፍ እና ሃይረም ህይወታቸውን ለወንጌሉ ሰጡ” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
መጋቢት–ሰኔ 1844 (እ.አ.አ)
ጆሴፍ እና ሃይረም ህይወታቸውን ለወንጌሉ ሰጡ።
ነቢዩ ሞተ፣ ነገር ግን የጌታ ስራ ቀጥሏል።
ጆሴፍ ስሚዝ ተጨንቆ ነበር። ከሞተ ቤተክርስቲያኗ ምን ትሆናለች? የጌታ ስራ እንደሚቀጥል ማረጋገጥ ፈለገ። ስለዚህም ሐዋርያትን ሰብስቦ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን የክህነት ቁልፎችን ሰጣቸው። ይህም ሐዋርያት የጌታን ቤተክርስቲያን እንዲመሩ እና ስራውን መስራት እንዲችሉ ያደርጋል ማለት ነው። ይህም ጆሴፍ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ረዳው።
ቅዱሳን፣ 1፥519–20።
ነገር ግን በጆሴፍ የተናደዱ ብዙ ሰዎች ነበሩ። አንዳንዶች ሊገድሉትም ጭምር ይፈልጉ ነበር። የሚያስተምረውን ነገር አልወደዱትም። በጆሴፍ እና በቤተክርስቲያኗ ላይ ብዙ ሰዎች እንዲቆጡ ስለ እሱ በጋዜጣ ጻፉ። አንዳንዶቹ ናቩን ማጥቃት ፈለጉ።
ቅዱሳን፣ 1፥526–28፣ 530–32፣ 533–34
ጆሴፍ እና ሌሎች በናቩ ያሉ መሪዎች ጥላቻው እንዳይስፋፋ ለማድረግ ማተሚያውን አወደሙ። ይህ ደግሞ ሰዎችን የበለጠ አስቆጣ። ሕጉን ጥሶ እንደሆነ ዳኛ እንዲወስን ጆሴፍ ወደ ካርቴጅ ከተማ እንዲሄድ አገረ ገዢው ነገረው። ጆሴፍ ወደ ካርቴጅ ቢሄድ ሰዎች እንደሚገድሉት ያውቅ ነበር።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥4–15፤ ቅዱሳን፣ 1፥533–37፣ 539–41
ጆሴፍ ግን የቅዱሳኑን ደህንነት መጠበቅ ፈለገ። ወደ ካርቴጅ ከሄደ ምናልባት ሰዎች በናቩ ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን ይተው ይሆናል። ጆሴፍ ለመሄድ ወሰነ። ኤማን እና ልጆቹን ባረካቸው፣ ደህና ሁኑ በማለት ሳማቸው፣ ከዚያም ወደ ካርቴጅ ሄደ።
ቅዱሳን፣ 1፥542–44
የጆሴፍ ወንድም ሃይረም አብሮት ሄደ። ጆን ቴይለር፣ ዊላርድ ሪቻርድስ እና ሌሎች ጓደኞችም አብረዋቸው ሄዱ። ሲወጡ፣ ጆሴፍ ፈረሱን አቁሞ ወደ ናቩ ተመለከተ። “ይህ ከሰማይ በታች በጣም ተወዳጅ ቦታ እና ምርጥ ሰዎች ያሉበት ነው” አለ።
ቅዱሳን፣ 1፥543–45
ወደ ካርቴጅ ሲደርሱ፣ ወደ እስር ቤት አስገቧቸው። በእስር ቤት እያሉ ሃይረም ከመፅሐፈ ሞርሞን አነበበላቸው። ጆሴፍ መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለጠባቂዎቹ ነገራቸው።
ቅዱሳን፣ 1፥546
ጓደኞቹን ለማጽናናት፣ ጆን ቴይለር ስለ ኢየሱስ መዝሙር ዘመረ። ቆንጆ ነበር፣ እና ሃይረም እንደገና እንዲዘምር ጠየቀው።
ቅዱሳን፣ 1፥549
የዚያን ቀን ኋላ ላይ ሽጉጥ የያዙ የተቆጡ ሰዎች በፍጥነት ወደ እስር ቤት ገቡ። በሩን ገፍተው ጆሴፍና ጓደኞቹ ወደ ነበሩበት ክፍል መተኮስ ጀመሩ። ጆን ቴይለር ክፉኛ ተጎዳ። ሃይረም እና ዮሴፍ ተገደሉ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥1–2፤ ቅዱሳን, 1፥550–52
ቅዱሳኑ ጆሴፍ እና ሃይረም መሞታቸውን ባወቁ ጊዜ በጣም አዘኑ። ነቢዩን መግደል ግን ቤተክርስቲያንን እንደማያቆም ያውቁ ነበር። የአዳኙ ቤተክርስቲያን ናት፣ እርሱም መምራቱን ይቀጥላል። ቤተክርስቲያኗ እያደገች እና የእግዚአብሔርን ልጆች በአለም ዙሪያ በመባረክ ትቀጥላለች።
ቅዱሳን፣ 1፥553–59።