በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ከአንድ በላይ ሚስቶችን ማግባት


“ከአንድ በላይ ሚስቶችን ማግባት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ከአንድ በላይ ሚስቶችን ማግባት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1831–1890 (እ.አ.አ)

ከአንድ በላይ ሚስቶችን ማግባት

ለተወሰነ ጊዜ የተሰጠ ትእዛዝ

ጆሴፍ ስሚዝ ቅዱሳን መጻህፍትን ሲያጠና እና ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት ልምምድ ሲያስብ።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ መጽሐፍ ቅዱስን እያጠና ሳለ፣ ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው ስለነበሩት ነቢያት እንደ አብርሃም እና ሙሴ የመሳሰሉትን አነበበ። ጆሴፍ ስሚዝ አያሌ ጥያቄዎች ነበሩበት። ስለዚህ ለመጸለይ እና ጌታን ለመጠየቅ ወሰነ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥1ቅዱሳን1፥121503

ሰዎች በእግዚአብሔር ሲታዘዙ ብቻ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ሊያገቡ እንደሚችሉ ጆሴፍ ተማረ።

ጌታም አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው አንዲት ሚስት ብቻ ሊኖረው እንደሚገባ ተናገረ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ጌታ አንድን ሰው ከአንድ በላይ ሚስት እንዲኖረው አድርጓል። ይህም ከአንድ በላይ ሚስቶችን ማግባት ይባላል። ጌታ ሲያዛቸው ብቻ የእርሱ ሰዎች ከአንድ በላይ ሚስት እንደሚኖራቸው ለጆሴፍ ነግሮታል።

ያእቆብ 2፥27–30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥34–15ቅዱሳን1፥121290–91489–90503

ጆሴፍ ስለ ትእዛዙ እየጸለየ።

ከዓመታት በኋላ፣ ጌታ ለጆሴፍ እና ለሌሎች ቅዱሳን ከአንድ በላይ ሚስቶች እንዲኖሯቸው ነገራቸው። በዚህ ትእዛዝ መኖር ቀላል አልነበረም።

ቅዱሳን1፥290–91444–46

አንድ የቤተክርስቲያኗ አባል ከአንድ በላይ ሚስቶች ስለነበሩት በዳኛ ፊት ቆሞ።

መንግስትም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን በመቃወም ህጎችን አወጣ። አንዳንድ ቅዱሳን፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጨምሮ፣ ወደ እስር ቤት ተጣሉ።

ቅዱሳን2፥501–4

የቤተክርስቲያን አባላት ከዚህ በኋላ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ያለማግባት ትእዝዙን ያከብራሉ ።

በ1890፣ ጌታ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለውልፈርድ ውድረፍ፣ ማንም ሰው ከዚህ በኋላ ከአንድ በላይ ሚስቶች ሊኖሩት እንደማይገባ ነገረ። የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ይህንን ትእዛዝ ለቅዱሳን አካፈሉ። ዛሬም ይህ የጌታ ትእዛዝ ነው—አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ብቻ ሊያገባ ይገባል።

አስተዳደራዊ አዋጅ 1; ቅዱሳን2፥598–601607–9