“ፓርሊ እና ታንክፉል ፕራት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ፓርሊ እና ታንክፉል ፕራት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ነሐሴ–መስከረም 1830 (እ.አ.አ)
ፓርሊ እና ታንክፉል ፕራት
መንፈስን ለመከተል የሚያስፈልግ እምነት
ፓርሊ ፕራት እና ታንክፉል ፕራት በኦሃዮ የሚኖሩ ገበሬዎች ነበሩ። አንድ ቀን፣ ፓርሊ መጽሐፍ ቅዱስን ለሰዎች ያስተምር ዘንድ ሃገሩን ለቅቆ እንዲወጣ መንፈስ ሲነግረው ተሰማው።
ቅዱሳን፣ 1፥92
ፓርሊ እና ታንክፉል ፕራት እርሻቸውን ሸጡ። ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም ነበር፣ ሆኖም እርሱን ስለሚያገለግሉ እግዚአብሔር እንደሚባርካቸው ያምኑ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥92
ፓርሊ እና ታንክፉል የተወሰነ ልብስ እና ገንዘብ ይዘው በጀልባ ተሳፈሩ። በኒውዮርክ ውስጥ ሲጓዙ ፓርሊ ከጀልባው እንዲወርድ መንፈስ ነገረው። ፓርሊ፣ ታንክፉል ጉዞውን ብቻዋን እንድትቀጥል ጠየቃት። በቅርቡ ወደ እርሷ እንደሚመለስ ቃል ገባላት። እግዚአብሔር በኒው ዮርክ እንዲሠራ የሚፈልገው ሥራ እንዳለ ተሰማው።
ቅዱሳን፣ 1፥92
ፓርሊ ረጅም መንገድ ተጓዘ። በመጨረሻም ወደ አንድ ሰባኪ ቤት ደረሠ። ሰባኪው አንድ ሰው ስለሰጠው ለየት ያለ መጽሐፍ ለፓርሊ ነገረው። ከወርቅ ሰሌዳዎች የተገለበጠ ሲሆን የተጻፈውም ከረጅም ጊዜ በፊት ነው። መፅሐፈ ሞርሞን ይባላል። በእግዚአብሔር ኃይል የተረጎመውም በኒው ዮርክ የሚኖር አንድ ወጣት ነው።
ቅዱሳን፣ 1፥92
ፓርሊ የማወቅ ጉጉት አደረበት። ሰባኪው መጽሐፉን ለፓርሊ አሳየው። ፓርሊ በጉጉት ከፍቶ ማንበብ ጀመረ። ሰዓታት አለፉ፣ ሆኖም ለመብላትና ለመተኛት ሲል እንኳ ማንበቡን ማቆም አልቻለም ነበር። የጌታ መንፈስ መፅሐፉ እውነት እንደሆነ ነገረው።
ቅዱሳን፣ 1፥92–93።
ፓርሊ መጽሐፈ ሞርሞንን በጣም ወደደው፣ ስለዚህም የተረጎመውን ሰው ለማግኘት ፈለገ። የጆሴፍን ወንድም ሃይረምን ወዳገኘበት ወደ ስሚዝ ቤተሰብ እርሻ አመራ። ሌሊቱን ሙሉ ሲነጋገሩ አደሩ። ሃይረም መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለፓርሊ ነገረው። የግሉን የመጽሐፉን ቅጂ ለፓርሊ ሰጠው።
ቅዱሳን፣ 1፥93
ፓርሊ ማንበቡን ሲቀጥል ኢየሱስ ክርስቶስ በአሜሪካ አህጉር የነበሩ ሰዎችን እንደጎበኘ አወቀ። መፅሐፈ ሞርሞን በአለም ካለው ሃብት ሁሉ የበለጠ ዋጋ እንዳለው መመልከት ቻለ። ወደ ታንክፉል ለመመለስ እና የተማረውን ለማካፈል ጓጉቶ ነበር።
ቅዱሣን፣ 1፥93፤ 3 Nephi 11፥1–12
ፓርሊ ለታንክፉል እና ለሌሎች የቤተሠቡ አባላት ስለመፅሐፈ ሞርሞን ነገራቸው። ስለአኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሚያስተምር ነገራቸው። ፓርሊ መንፈሱን በመከተሉ እና እግዚአብሔር እንዲሰራው የሚፈልገውን ሥራ በማግኘቱ ታንክፉል ተደሠተች። እንደ ፓርሊ ሁሉ ታንክፉል መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ በራሷ አወቀች።
ቅዱሳን፣ 1፥98–99