በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሳሙኤል ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን አጋራ


“ሳሙኤል ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን አጋራ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

“ሳሙኤል ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን አጋራ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1830–1832 (እ.አ.አ)

ሳሙኤል ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን አጋራ

አንድ መፅሐፍ የብዙዎችን ሕይወት ባረከ

“ሳሙኤል ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ለጆን እና ለሮዳ ግሪን እያጋራ።

ጌታ የጆሴፍን ታናሽ ወንድም ሳሙኤል ስሚዝን ወንጌልን ለማካፈል ወደ ሚስዮን እንዲሄድ ጠራው። ሳሙኤል ጆንን እና ሮዳ ግሪንን አገኛቸው ስለመፅሐፈ ሞርሞንም ነገራቸው። ጆን የሌላ ቤተክርስቲያን ሰባኪ ነበር። የመጽሐፉን ቅጂ ወስዶ በእርሡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊያነበው የሚፈልግ ሰው ካለ ለማየት እንደሚፈልግ ተናገረ።

ቅዱሳን1፥99

ሮዳ መፅሐፈ ሞርሞንን ለሳሙኤል መልሣ እየሠጠች።

ከጥቂት ወራት በኋላ ሳሙኤል ተመልሶ መጣ። ሮዳ ባለቤቷ መፅሐፈ ሞርሞንን ለማንበብ የሚፈልግ ሰው ሊያገኝ እንዳልቻለ ተናገረች። ለሳሙኤልም መልሳ ሠጠችው።

ቅዱሳን1፥99

ሮዳ መጽሐፈ ሞርሞንን ማንበብ እንደምትወድ ለሳሙኤል እየነገረችው።

ሳሙኤል አዝኖ ነበር። ለመሄድ ፊቱን አዞረ ሮዳ ግን አስቆመችው። መጽሐፈ ሞርሞንን እንዳነበበችውና እንደወደደችው ተናገረች።

ቅዱሳን1፥99

ሳሙኤል መፅሐፈ ሞርሞንን ለሮዳ እየመለሰላት እንዲሁም እግዚአብሔርን ምስክርነት እንዲሰጣት እንድትጠይቅ እየጋበዛት።

መንፈስ ቅዱስ፣ መጽሐፉን ለሮዳ መልሶ እንዲሠጣት ለሳሙኤል ነገረው። ሳሙኤልም “ምስክርነት እንዲሰጥሽ እግዚአብሔርን ለምኚ” አላት። ስለመንፈስ ቅዱስ እና መፅሐፈ ሞርሞን እውነት ስለመሆኑ እንዴት እንደምታውቅ ሮዳን አስተማራት።

ሞሮኒ 10፥3–5ቅዱሣን1፥99-100

ሳሙኤል ከሚስዮን ወደ ቤቱ እየተመለሰ።

ሳሙኤል ከሚስዮን ወደ ቤቱ ተመለሰ። ማንንም አላጠመቀም ነበር፤ እንዲሁም ለመፅሐፈ ሞርሞን ፍላጎት ያሳዩት ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ።

ሮዳ ለወንድሟ ለብሪገም ያንግ መጽሐፈ ሞርሞንን እያካፈለች።

ሮዳ እና ጆን ፀለዩ፤ መንፈስ ቅዱስም መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን ነገራቸው። ከዚያም፣ ሮዳ መጽሐፉን ለወንድሟ ለብሪገም ያንግ አካፈለች።

ቅዱሳን1፥100

ብሪገም ያንግ እና ሄበር ኪምባል መጽሐፈ ሞርሞንን እያነበቡ፡፡

ብሪገም እና ጓደኛው ሄበር ኪምባል የኢየሱስን እውነተኛ ቤተክርስቲያን እየፈለጉ ነበር። መፅሐፈ ሞርሞንን አነበቡ። ለሁለት ዓመታት ያህል የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አጠኑ እንዲሁም ጸለዩ።

ብሪገም አንድ ሚስዮናዊ ምስክርነቱን ሲያካፍል እያዳመጠ።

በዚህ ጊዜ ብሪገም እና ሄበር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ይሄዱ ነበር። ከእነዚህ ስብሠባዎች በአንዱ፣ ብሪገም አንድ ሚስዮናዊ ምስክርነቱን ሲያካፍል ሠማ። ሚስዮናዊው ታላቅ ተናጋሪ አልነበረም፤ ሆኖም በተናገረበት ጊዜ ብሪገም መንፈስ ቅዱስ ተሰማው። እውነቱን እየተናገረ እንደነበረ ብሪገም አውቆ ነበር።

ብሪገም እና ሄበር ወንጌልን እያካፈሉ።

ብሪገም፣ ሄቤር እና ሚስቶቻቸው፣ ሚርያም እና ቨሌት፣ ተጠመቁ። አዳኙን እና ወንጌሉን ወደዱ። ከዓመታት በኋላ፣ ጌታ ብሪገምን እና ሄበርን ሐዋርያቱ እንዲሆኑ እና በሚስዮን እንዲያገለግሉ ጠራቸው። ሳሙኤል መጽሐፈ ሞርሞንን በማካፈሉ፣ ብዙ ሰዎች የአዳኙን ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥127–29126ቅዱሳን1፥215–16