“ወደ ኦሀዮ መሰባሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ወደ ኦሀዮ መሰባሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ታህሳስ 1830–ግንቦት1831 (እ.አ.አ)
ወደ ኦሃዮ መሰባሰብ
የሉሲ ስሚዝ እምነት እና ተአምር
በኦሀዮ፣ የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ እየተቀላቀሉ ነበር። በሌሎች ስፍራዎች እየኖሩ ያሉ ቅዱሳን በኦሀዮ መሰባሰብ እንዳለባቸው ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። ይህም ረዥም ጉዞ ይሆናል። ነገር ግን ከተሰባሰቡ በኋላ፣ ለቅዱሳን ህጉን እንደሚያስተምራቸው እና ይሰሩ ዘንድ በሀይሉ እንደሚባርካቸው ጌታ ቃል ገባላቸው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፤ 38፥32፣ Saints [ቅዱሣን]፣ 1፥109–110
የጆሴፍ እናት፣ ሉሲ፣ እና ወደ 80 የሚሆኑ የቤተክርስቲያን አባላት በኒውዮርክ ያለ ቤታቸውን ትተው ወደ ኦሃዮ ተዘዋወሩ። የጉዞአቸውን የተወሰነ እርቀት ወደሚወስዳቸው ጀልባ ውስጥ ገቡ። ለጥቂት ቀናት ከተጓዙ በኋላ፣ ጀልባው መቆም ነበረበት። በውሃ ውስጥ የነበረ ግግር በረዶ መንገዳቸውን ገታባቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥121–22
በረዶው እስኪሰባበር ቅዱሳኑ መጠበቅ ነበረባቸው። ደክሟቸው፣ ርቧቸው፣ ረጥበው፣ እና በርዷቸው ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥122
መጠበቁ ከባድ ነበር። የተወሰኑ ቅዱሳን እርስ በርሳቸው መጨቃጨቅ ጀምረው ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥122
ሉሲ ቅዱሳን ሲጨቃጨቁ መስማቷን አልወደደችውም። አንድ ነገር መናገር እንዳለባት አውቃለች። “እምነታችሁ ወዴት አለ?” በማለት ጠየቀች። ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ፣ መንገዳቸውን ይቀጥሉ ዘንድ እርሱ በረዶውን እንደሚሰብርላቸው ሉሲ ለቅዱሳኑ ተናገረች።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥122–23
በድንገት፣ በረዶው ለሁለት ሲከፈል እንደ መብረቅ ያለ ድምጽ ሰሙ። በበረዶው ውስጥ መንገድ ተከፈተ፣ ይህም ጀልባቸው ሊያልፍ የሚችልበት በቂ ስፋት ያለው ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥123
ቅዱሳኑ ተገርመዋል እንዲሁም አመስጋኞች ነበሩ። ቅዱሳን የሰማይ አባትን ለማመስገን ለጸሎት ተሰበሰቡ። ጀልባቸው በሰላም ወደ ኦሀዮ ተጓዘ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥123
ቅዱሳን በኦሀዮ ሲደርሱ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት በሠላምታ ተቀበሏቸው እና የሚኖሩበትንም ስፍራ በመፈለግ አገዟቸው። ጌታ ለቅዱሳን ህጉን እንደሚያስተምራቸው እና ይሰሩ ዘንድ በሀይሉ እንደሚባርካቸው የገባላቸውን ቃል ጠብቋል።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥126