“የሴቶች መረዳጃ ማህበር” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የሴቶች መረዳጃ ማህበር” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
መጋቢት 1842 (እ.አ.አ)
የሴቶች መረዳጃ ማህበር
የናቩ ሴቶች ጌታን ያገለግላሉ
ማርጋሬት ኩክ በናቩ ትኖር ነበር። በልብስ ስፌት እየረዳች ለሣራ ኪምባል ትሰራ ነበር። እሷ በምትሠራበት ጊዜ በናቩ ስለሚገነባው አዲሱ ቤተመቅደስ ማውራት ይወዱ ነበር። ስለ ቤተመቅደሱ ጓጉተው ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥447
አንድ ቀን፣ ማርጋሬት ቤተመቅደሱን ከሚገነቡት ወንዶች መካከል ብዙዎቹ ያረጀ እና የተቀዳደደ ልብስ እንደሚለብሱ አስተዋለች። እሷ እና ሳራ በአንድነት ለወንዶች አዲስ ሸሚዞችን መስፋት ይችሉ እንደሆነ አሰበች። ሳራ ሃሳቡን ወደደችው። እሷ እና ማርጋሬት ሰራተኞቹን ለመርዳት ቡድን ስለማቋቋም ከሌሎች ሴቶች ጋር ተነጋገሩ።
ቅዱሳን፣ 1፥447–48
ነቢዩ ጆሴፍ ጌታ በሃሳባቸው ደስተኛ እንደሆነ እና ለእነርሱም የተሻለ ነገር እንዳለው ተናገረ። ጆሴፍ ሴቶቹ በመጋቢት 17 ቀን 1842 (እ.አ.አ) ከእሱ ጋር እንዲገናኙ ጋበዛቸው። የክህነት ስልጣንን በመጠቀም የቤተክርስቲያኗን ሴቶች አደራጀ። ቡድናቸውን የናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ብለው ለመጥራት ወሰኑ።
ቅዱሳን፣ 1፥448፣ 450–51
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሰዎችን ለቤተመቅደስ እና ለዘለአለም ህይወት በረከቶች እንዲዘጋጁ እንዲረዱ ጆሴፍ ጠየቃቸው። ኢየሱስን የመከተል ምሳሌ መሆን አለባቸው።
ቅዱሳን፣ 1፥451
በተጨማሪም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ድሆችን ፈልጎ በማግኘት መርዳት እንደሚገባቸ ተናገረ። ድሆች የነበሩ ሴቶች እንኳን የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት ይፈልጉ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥449
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ተደራጀ። ኤማ ስሚዝ ፕሬዚዳንት እንድትሆን ተጠራች። ሁለት አማካሪዎች ሣራ ክሊቭላንድ እና አን ውትኒን ጠራች። በተጨማሪም እላይዛ አር. ስኖው ፀሐፊ እንድትሆን ጠራች።
ቅዱሳን፣ 1፥450
ጌታ ኤማ ጥሪዋን እንድትፈጽም ረዳት። ኤማ በጌታ አገልግሎት ውስጥ ሴቶች ታላቅ ነገር ማድረግ እንደሚችሉ አስተማረች። እያንዳንዳቸውም መልካም ለማድረግ መንገዶችን እንዲፈልጉ ፈለገች። ከሁሉም በላይ ደግሞ ልክ እንደ ኢየሱስ ሌሎች ሰዎችን መውደድ እንዳለባቸው ነገረቻቸው። በናቩ የሚኖሩ ብዙ ሴቶች የሴቶች መረዳጃ ማህበሩን ተቀላቀሉ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥37፣ 7፤ ቅዱሳን፣ 1፥451
እነርሱም ሰዎች ለቤተመቅደስ በረከቶች እንዲዘጋጁ አግዘዋል እንዲሁም በናቩ ውስጥ የተቸገሩ ብዙ ቤተሰቦችን ረድተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ተቀላቅለዋል። ሰዎችን ማገልገላቸውን እና የቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ መርዳት ቀጥለዋል።
ቅዱሳን፣ 1፥451