በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሱሳ ያንግ ጌትስ እና ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ


‘’ሱሳ ያንግ ጌትስ እና ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ሱሳ ያንግ ጌትስ እና ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1902–1918 (እ.አ.አ)

ሱሳ ያንግ ጌትስ እና ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ

ስለ መንፈስ ዓለም የሚገልጸው ራእይ

ብሪገም ያንግ ከሴት ልጁ ሱሳ ጋር ሲነጋገር

ሱሳ ያንግ ጌትስ የብሪገም ያንግ ሴት ልጅ ነበረች። እርሷ በዩታ የተወለደች እና እዚያው ያደገች ነበረች። መጻፍን የምትወድ እና በጌታ ቤት ውስጥም ማገልገልን የምትወድ ነበረች።

ቅዱሳን3፥9–1064

ሱሳ የክህነት ቡራኬን እየተቀበለች።

ሱሳ ጎልማሳ በነበረችበት ወቅት በጣም ታመመች። የክህነት ቡራኬን ታገኝ ዘንድ ጠየቀች። በቡራኬውም መሃል፣ ጌታ የቤተመቅደስ ስራን እንድትሰራ እንደሚፈልግ ነገራት።

ቅዱሳን3፥193–94

ሱሳ ከሌላ ሴት ጋር ስለ ቤተመቅደስ እና ስለ ቤተሰብ ታሪክ እያወራች።

ከቡራኬውም በኋላ ሱሳ ከህመሟ እየተሻላት ሄደ። ጊዜዋን ስለ ቤተሰቧ ታሪክ በመማር ታሳልፍ ነበር። ሳይጠመቅ የሞተ የቤተሰብ አባል ባገኘች ጊዜ፣ ስለ እነርሱ ለመጠመቅ ወደ ቤተመቅደስ ትሄድ ነበር። ስለ ለቤተሰብ ታሪክ ሥራ ለሰዎች መናገርን ትወድ ነበር። አሳዛኙ ነገር፣ አያሌ ሰዎች ፍላጎቱ የላቸውም ነበር።

ቅዱሳን3፥194–95206

ሱሳ  ከጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ጋር ስትነጋገር።

አንድ ቀን፣ ሱሳ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት የነበሩትን፣ ጓደኛዋን ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝን ጎበኘች። ፕሬዚዳንት ስሚዝ ለአያሌ ሳምንታት ታመው ነበር። ልጃቸው በመሞቱ ምክንያት በጣም አዝነው እንደነበርም አወቀች። እንደ ጦርነት እና በሽታ የመሳሰሉ ሌሎች ነገሮች በአለም ላይ በመከሰታቸውም ጭምር አዝነዋል።

ቅዱሳን3፥197–99205–6

ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ስለራእያቸው ለሱሳ ነገሯት።

ነገር ግን ሱሳ ከፕሬዚዳንት ስሚዝ ጋር በተቀመጠች ጊዜ፣ ከእርሷ ጋር በመነጋገሩ ተደሰቱ። እግዚአብሔር ልዩ ራእይን እንደሰጫቸውው ለሱሳ ነገሯት። ይህም ሰዎች ከሞቱ በኋላ ስለሚሄዱበት፣ ስለ መንፈሱ ዓለም ነበር። ራዕያቸው በወረቀት ላይ ተጽፎ ነበር። ፕሬዚዳንት ስሚዝ ለሱሳ ሰጧት እናም እንድታነበውም ጠየቋት።

ቅዱሳን3፥206–7

ሱሳ ስለ ራእዩ እያነበበች ሳለች።

ሱሳ ወረቀቱን አነበበች። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የመንፈሱን ዓለም ጎበኘ ይላል። በህይወት በነበሩበት ጊዜ ወንጌልን ያልተቀበሉትን መንፈሶች ለማስተማር አዳምን፣ እና ሌሎች ታማኝ ወንዶችን እና ሴቶችን ላከ። እነርሱም ሰዎች ስለእነርሱ በቤተመቅደስ እንዲጠመቁላቸው እነዚህን መንፈሶች ለማዘጋጀት እየረዱ ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥11–19፣ 29–48ቅዱሳን3፥206–7

ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እና ሱሳ እያወሩ።

ሱሳ የፕሬዚዳንት ስሚዝን ራእይ ባነበበች ጊዜ ተገረመች። ፕሬዚዳንት ስሚዝ ወደ እርሷ ፈገግ አሉ። እንዲህም አሉ፣ ‘’ሱሳ፣ ታላቅን ስራ እየሰራሽ ነው ያለሽው።’’ እርሷ በጌታ ስላላት እምነት እንደሚወዷት ነገሯት።

ቅዱሳን3፥206

ሱሳ በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ አጠገብ ተቀምጣ።

ሱሳ በማስታወሻዋ ስለ ራእዩ ጻፈች። ‘’እንግዲህ፣ ይህ ለእኔ መጽናኛ ነው!’’ አለች። ይህንንም ነገር ለጓደኞቿ እና ለሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት ለመናገር ቸኩላ ነበር። የፕሬዚዳንት ስሚዝ ራእይ በመንፈስ ዓለም ላሉ ሰዎች የቤተመቅደስ ስራን እንዲሰሩ በመርዳት ቅዱሳንን የሚያነሳሳ እንደሆነ አውቃለች።

ቅዱሳን3፥207