“ሜሪ እና ካሮሊን ሮሊንስ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ሜሪ እና ካሮሊን ሮሊንስ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ህዳር 1830(እ.አ.አ)—ሐምሌ 1831 (እ.አ.አ)
ሜሪ እና ካሮሊን ሮሊንስ
ለቅዱሳት መጻህፍት ብርቱ ፍቅር
ማሪ ሮሊንስ ሚስዮናውያን ከርትላንድ፣ ኦሃዮን ሲጎበኙ 12 አመቷ ነበር። ስለመፅሐፈ ሞርሞን ሲናገሩ ሰማቻቸው። በዚያን ጊዜ፣ በከርትላንድ ውስጥ አንድ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂ ብቻ ነበር፣ እና አይዛክ ሞርሊ የሚባል የቤተክርስቲያን መሪ የነበረው ሰው ይዞት ነበር።
ሜሪ ወደ ወንድም ሞርሊ ቤት አመራች እና መፅሐፉን ለማየት ጠየቀች። ወንድም ሞርሊም እንድትይዘው አደረጋት። ሜሪ ወደ ቤቷ ይዛው መሄድ ትችል እንደሆነ ጠየቀች።
ወንድም ሞርሊ የእርሱን የመጽሐፍ ቅጂ ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም። እርሱ ብዙውን ክፍል አላነበበም ነበር። ሜሪ መጽሐፉን እንዲያውሳት ወንድም ሞርሊን ተማጸነች።
ወንድም ሞርሊም ተስማማ። እርሱም በሚቀጥለው ቀን በጊዜ መልሳ የምታመጣ ከሆነ መጽሀፉን ወደ ቤቷ ይዛ መሄድ እንደምትችል ነገራት። ሜሪ እንደ ሀብት ቆጠረችው። እርሷም አብዛኛውን ሌሊት በማንበብ አሳለፈች።
ሚሪ መጽሐፉን በመለሰች ጊዜ፣ ወንድም ሞርሊ ባነበበችው ብዛት ተገረመ። ‘’ልጄ ሆይ፣’’ እርሱም አለ፣ ‘’ይህን መጽሀፍ ወደ ቤትሽ ወስደሽ ጨርሽው። እኔ ልጠብቅ እችላለሁ።’’
ሜሪ በከርትላንድ መጽሐፉን ሙሉ ለሙሉ ያነበበች የመጀመሪያ ሰው ነበረች። ካነበበችውም በኋላ፣ ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጋር ተገናኘች። እርሱም ሜሪ ምን ያህል መጽሐፈ ሞርሞንን እንደምትወድ ባወቀ ጊዜ የወንድም ሞርሊን ቅጂ ልትወስድ እንደምትችል ነገራት። ለወንድም ሞርሊ ሌላ እንደሚሰጠው ተናገረ።
በዚያም ዓመት መገባደጃ፣ ሜሪ እና ቤተሰቧ ወደ ኢንዲፔንደንስ፣ ምዙሪ ተዛወሩ። እርሷም የቤተክርስቲያን አባላት የትእዛዛቱ መጽሐፍ የተሰኘን አዲስ መጽሐፍ በአንድነት መጠረዝ ሲጀምሩ በማየቷ ተደሰተች። ይህ መፅሐፍ ኢየሱስ ኪርስቶስ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሰጠውን ብዙ ራዕዮችን የያዘ ነው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፤ 70፥1–4፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥178
ነገር ግን በኢንዲፔንደንስ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ቤተክርስቲያኗን አልወደዱም ነበር። እነርሱም ቅዱሳኑ ለቀው እንዲወጡ ይመኙ ነበር። አንድ ቀን፣ ብስጩ ሰዎች የትእዛዛቱ መጽሐፍ እየታተመ የነበረበትን ህንጻ ሰብረው ገቡ። የማተሚያ ማሽኑን በመስኮት ወረወሩት እና የመፅሐፍ ትእዛዛት ገጾች ጎዳና ላይ በታተኗቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥177–78
ሜሪ እና እህቷ ካሮሊን ከአጥሩ በስተጀርባ ሆነው እየተመለከቱ ነበር። ሜሪ ለካሮሊን፣ ገጾቹ ከመጥፋታቸው በፊት ልታገኛቸው እንደፈለገች ነገረቻት። ካሮሊን የተበሳጩትን ሰዎች ፈርታቸው ነበር። ‘’ይገድሉናል፣’’ በማለት ተናገረች። ነገር ግን ሜሪ እና ካሮሊን እነዚያ ገጾች በላያቸው ላይ የእግዚአብሔርን ቃላት እንደያዙ ያውቁ ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥178
እህቶቹ ሰዎቹ ማየት እስከማይችሉበት ጊዜ ድረስ ጠበቁ። ከዚያም ወደ ጎዳናው ሮጡ እና መያዝ የሚችሉትን ያህል ገጾች ሰበሰቡ። በፍጥነት በመሮጥ ላይ እያሉ፣ የተወሰኑ ሰዎች አዩአቸው ከዚያም እንዲያቆሙ መጮህ ጀመሩ። ሜሪ እና ካሮሊን ገጾቹን አጥብቀው ይዘዋል እናም በአቅራቢያው ወዳለው የበቆሎ ማሳ በቻሉት ፍጥነት ሮጡ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥178–79
ሁለት ወንዶች እህቶቹን በበቆሎው ማሳ ውስጥ አሳደዷቸው። በቆሎው በጣም ረዥም ነበር፣ ሚሪ እና ካሮሊን የሚሄዱበትን ማየት አልቻሉም ነበር። ራሳቸውን ወደ መሬት ጣሉ እና ገጾቹንም በሰውነታቸው ደበቋቸው። ሁለቱ ወንዶች በበቆሎው መሃል እየተራመዱ ሲፈልጓቸው በቀስታ አዳመጡ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥179
ወዲያውኑም ወንዶቹ ተስፋ ቆረጡ። ሜሪ እና ካሮሊን ደህና ሆኑ። እነርሱም የጌታን ራዕይ ገጾች ለመፅሐፈ ትእዛዛት እንዲገኙ አተረፏቸው። ዛሬ እነዚያ ራዕዮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መጽሐፍ ውስጥ ናቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥179