በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኑወል እና አን ውትኒ ነቢዩ ጆሴፍን አገኙት


‘’ኑወል እና አን ውትኒ ከነቢዩ ጆሴፍ ጋር ተገናኙ፣’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

‘’ኑወል እና አን ውትኒ ከነቢዩ ጆሴፍ ጋር ተገናኙ፣’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ጥቅምት 1830–የካቲት 1831 (እ.አ.አ)

ኑወል እና አን ውትኒ ከነቢዩ ጆሴፍ ጋር ተገናኙ

በእምነት የሚሰጡ ጸሎቶች በጌታ ይመለሳሉ

አን እና ኑወል ውትኒ ሲጸልዩ።

አን እና ኑወል ውትኒ በከርትላንድ፣ ኦሀዮ መጋዘን ነበራቸው። አን ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድም ሆነ ስለጌታ በመማር አላደገችም፣ ነገር ግን እርሱን ለማወቅ ፈልጋለች። እርሷ እና ኑወል ካተጋቡ በኋላ፣ ብዙ ጊዜ ጸልየዋል እና ጌታ እንዲመራቸው ጠይቀዋል።

Saints [ቅዱሳን]1፥111–12

አን እና ኑወል ራዕይ ሲቀበሉ

በአንድ ሌሊት በጸሎት ላይ ሳሉ፣ አን እና ኑወል ራዕይ አዩ። በራዕዩም ውስጥ፣ በቤታቸው አናት ላይ ደመና አረፈ። የእግዚአብሔር መንፈስ ሞላቸው። ደመናውም ከበባቸው። ከዚያም ከሰማይ የሚመጣ ድምጽ ሰሙ፡፡ ‘’የጌታን ቃል ለመቀበል ተዘጋጁ፣ እየመጣ ነውና’’ በማለት ነገራቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥111

አን ስለ ወንጌል ከፓርሊ ፕራት ስትማር።

ከትንሽ ጊዜ በኋላ፣ ፓርሊ ፕራት ወደ ከርትላንድ መጣ። እርሱ እና የእርሱ የሚስዮን አጋሮች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አስተማሩ። እያስተማሩ ያሉትን ልክ እንደሰማች፣ ወዲያውኑ እውነት እንደሆነ አወቀች። ዜናውን ለኑወል ለማጋራት ወደ ቤቷ ሄደች። ብዙ ሳይቆይም ተጠመቁ።

Saints [ቅዱሳን]1፥112

ጆሴፍ እና ኤማ ስሚዝ ከአን እና ከኑወል ጋር ተገናኙ።

ከሁለት ወራት በኋላ፣ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ወደ ኑወል መጋዘን መጡ። ኑወል አላወቃቸውም፣ ነገር ግን ሰውየው የኑወልን እጅ ጨበጠ እና ኑወልን በስሙ ጠራው። ሰውየውም፣ ‘’እኔ ነቢዩ ጆሴፍ ነኝ’’ አለ። ጌታ የኑወልን ጸሎቶች እየመለሰ እንደሆነ ገለጸ። እርሱ አንን እና ኑወልን እንዲያገኟቸው ኤማን እና ጆሴፍን ልኳቸዋል።

Saints [ቅዱሳን]1፥113

ጆሴፍ እና ኤማ ስሚዝን ከእነርሱ ጋር እንዲኖሩ አን እና ኑወል ጋበዟቸው።

ኑወል እና አን ራዕያቸው እውን እየሆነ መሆኑን አወቁ። እነርሱም ጆሴፍ እና ኤማን በቤታቸው አብረው እንዲኖሩ ጠየቋቸው። አን እና ኑወል ኢየሱስን እና ወንጌሉን ወደዋል። ያላቸውን ሁሉ ለቅዱሳን እና ለጌታ ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥23–27፣ 34–42Saints [ቅዱሳን]1፥114