በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተመረቀ


“የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተመረቀ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተመረቀ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

መጋቢት 1836 (እ.አ.አ)

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተመረቀ

የጌታን መንፈስ በእርሱ ቤት ውስጥ ማግኘት

አንድ ቤተሰብ ወደ ከርትላንድ ቤተመቅደስ በእግር ሲጓዝ።

በግምት ከሶስት ዓመታት ከባድ ስራ በኋላ፣ የከርትላንድ ቤተመቅደስ በስተመጨረሻ ተጠናቀቀ። ነቢዩ ጆሴፍ ቤተመቅደሱን ለመመረቅ ቅዱሳንን ለልዩ ስብሰባ ጋበዛቸው። ልዩ የሆነ ጸሎትን በማድረግ ቤተመቅደስንም ለጌታ ሰጠ። ይህም የጌታ የተቀደሰ ቤት ይሆን ዘንድ ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥235

ሰዎች ለምርቃቱም በቤተመቅደሱ ተሰብስበው ነበር።

ማለዳ በስብሰባው እለት ጠዋት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቅዱሳን በቤተመቅደሱ ውስጥ ተከማችተው ነበር። መቀመጫዎቹ በሙሉ በተያዙ ጊዜ፣ በመስኮት በመመልከት፣ ሰዎች በበር መግቢያው ላይ እና በውጪ ቆመው ነበር። ቤተመቅደሱ ሲመረቅ በማየታቸው ሁሉም ሰዎች ተደስተው ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥235–36

ጆሴፍ ስሚዝ የምረቃውን ጸሎት ሲያነብ።

ጆሴፍ ቤተመቅደሱን ለመመረቅ ጸሎትን አነበበ። ለጌታም ቅዱሳኑ ለእርሱ ታዛዥ የነበሩ መሆናቸውን ተናገረ። እርሱም ጌታ ቤተመቅደሱን እንደራሱ ቤት እንዲቀበለው ጠየቀ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥1–5

ህዝቡም ለጸሎት አይኖቻቸውን ጨፍነው።

ጆሴፍ ወደ ቤተመቅደሱ የሚመጣ ሁሉ የጌታ ሃይል እንደሚሰማው እና ይህም የእርሱ ቤት መሆኑን ማወቅ እንዲችል ጸለየ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥13

ጉባኤው ጌታን ሲያወድሱት።

እንዲሁም ጆሴፍ ቅዱሳን ሃጢያትን ባደረጉ ጊዜ፣ ወዲያውኑ ንሰሃ መግባት እንዲችሉ ጸለየ። ጌታንም በአለም ሁሉ ወንጌሉን እንዲያካፍሉ ሃይልን እንዲሰጣቸው ጠየቀ። ከጸሎቱም በኋላ፣ መዘምራኑ ‘’የእግዚአብሐር መንፈስ’’ የሚለውን አዲሱን መዝሙራቸውን ዘመሩ። ህዝቡም በሃሴት ተሞሉ። ቆሙ እና ጌታን አመሰገኑ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥21–32መዝሙሮችቁ. 2Saints [ቅዱሳን]1፥237

ደማቅ ብርሃን በቤተመቅደሱ ላይ ሲወርድ።

ብዙ ሰዎች በዚያ ቀን በቤተመቅደስ ውስጥ መላክቶችን ተመለከቱ። ከሰማይም ደማቅ ብርሃን ወደ ቤተመቅደሱ ሲወርድ ተመለከቱ። አንዳንድ ሰዎች ደመናን ይመስላል በማለት ተናገሩ፤ ሌሎች ደግሞ እሳት መሰለ በማለት ተናገሩ። ሁሉም ቤተመቅደስ ቅዱስ ስፍራ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። በእርግጥም አሁን ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥237