“ሆውንስ ሚል፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ሆውንስ ሚል፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ጥቅምት 1838–የካቲት 1839 (እ.አ.አ)
ሆውንስ ሚል
ጥቃት እና ተዓምር
ዊላርድ ስሚዝ 11 ዓመቱ ነበር። ቤተሰቡ በሆውንስ ሚል፣ ሚዙሪ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ይኖር ነበር። በቅርቡም ከቅዱሳን ጋር በሩቅ ምእራብ መሰባሰብን ይፈልጉ ነበር።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥7–8፤ ቅዱሳን፣ 1፥347–48
አንድ ቀን፣ ዊላርድ ከአባቱ እና ከወንድሙ፣ ሳርዲየስ እና አልማ ጋር ነበር። በድንገትም፣ የመሳሪያ ተኩስ እና ጩኸት ሰሙ። ሰዎች ቅዱሳንን ለማጥቃት መጥተዋል።
ቅዱሳን፣ 1፥348–49
እያንዳንዱ ሰው ከለላን ፍለጋ ሮጠ። አያሌ ወንዶች እና ህጻናት በብረት ቀጥቃጭ ሱቅ ውስጥ ተሸሸጉ። የዊላርድ አባት እና ወንድሞች ወደዚያው ገቡ፣ ነገር ግን ዊላርድ ከእነርሱ ተለየ። እርሱም በአንድ የማገዶ ክምር ጀርባ ተሸሸገ። በዙሪያው ሁሉ የመሳሪያ ተኩስ ሰማ።
ቅዱሳን፣ 1፥349፣ 353
ዊላርድ ለመሸሸግ ከስፍራ ወደ ስፍራ ሮጠ። በመጨረሻም የተኩስ ድምጹ ቆመ፡፡ አጥቂዎቹ ሆውንስ ሚልን ለቀው ሄዱ።
ቅዱሳን፣ 1፥353
ዊላርድ ቤተሰቡን ፍለጋ ወደ ብረት ቀጥቃጭ ሱቅ መጣ። አባቱ እና ሳርዲየስ ተገድለው ነበር። ነገር ግን የዊላርድ ትንሽ ወንድም አልማ በህይወት ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥353
አልማ ጭኑ ላይ ተመትቶ ነበር። ክፉኛ ተጎድቷል። ዊላርድ አልማን ተሽክሞ የቤተሰቡ ድንኳን ወዳለበት ወሰደው።
ቅዱሳን፣ 1፥353–54
የዊላርድ እናት፣ አማንዳ፣ የአልማን ጭን እንዴት መርዳት እንዳለባት አላወቀችም። ነገር ግን እግዚአብሔር እንደሚያውቅ አውቃለች። ጸለየች፣ እናም በትክክል ምን ማድረግ እንዳለባት የሚነግራትን ድምጽ ሰማች።
ቅዱሳን፣ 1፥354
አማንዳ የአልማን ቁስል በአመድ አጠበች። ከዚያም አንዳንድ የዛፍ ስር ነቅላ በቁስሉ ላይ አኖረች። ጭኑን በልብስ ጠቀለለች። ‘’እንደዚህ ተጋደም፣ እንዳትንቀሳቀስ፣’’ በማለት ተናገረች፣ ‘’እና ጌታ ሌላ ጭን ያበጅልሃል።’’
ቅዱሳን፣ 1፥354–55
በኋላም፣ የሀገር ገዢው ቅዱሳን ሚዙሪን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አለዚያም እንደሚገደሉ አወጀ። ነገር ግን የአልማ ጭን እስካሁን መሻሻል አላሳየም። አማንዳ ጸለየች እናም የጌታን እርዳታ ጠየቀች። አንድ ድምጽ ኢየሱስ ቤተሰቧን በፍጹም እንደማይተው ነገራት። አማንዳ ምንም ነገር ሊጎዳት እንደማይችል ተሰማት።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥83፣ ቅዱሳን፣ 1፥372፣ 378–79
ከጸለየች በኋላ ወዲያውኑ፣ አማንዳ ልጆቿ ሲጮሁ ሰማች። እነርሱን ፍለጋ ሮጠች፣ በሮጠችም ጊዜ አልማ በስፍራው እየሮጠ ነበር። ‘’ደህና ነኝ፣ እናቴ፣ ደህና ነኝ!’’ አለ። ጭኑ ተፈውሷል! ይህም ከጌታ ዘንድ የሆነ ተዓምር ነበር። አማንዳ እና ልጆችዋ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር የተሻለ ስፍራን በመፈለግ ሚዙሪን ለቀው ሄዱ።
ቅዱሳን፣ 1፥379