“ግንቦት 25–31 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው”፡ መሣፍንት 2–4፤ 6–8፤ 13–16“ .ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ግንቦት 25–31 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ፣ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
“በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ”—ነቢይቷ ዲቦራ፣ በደስ ሊቪት
ግንቦት 25–31 (እ.አ.አ)፡ “እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው”
መሣፍንት 2–4፤ 6–8፤ 13–16
ሁላችንም ኃጢአት መሥራት ምን እንደሚመስል እናውቃለን፣ ስለዚያ መጥፎ ስሜትም ይሰማናል፣ ከዚያም ደግሞ ንስሐ ገብተን መንገዳችንን ለመለወጥ እንወስናለን። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የቀድሞውን ውሳኔያችንን እንረሳለን፣ ከዚያም ፈተና ሲመጣብን፣ ያንኑ ሃጢያት እንደገና ስንሰራ እራሳችንን እናገኛለን። ይሄንን አሳዛኝ ድግግሞሽ በመጽሐፈ መሣፍንት ውስጥ እናያለን። ከምድሩ ለቀው እንዲወጡ ማድረግ ከነበረባቸው ከነዓናውያን እምነቶች እና የአምልኮ ተግባራት ተጽእኖ ምክንያት፣ እስራኤላውያን ከጌታ ጋር የነበራቸውን ቃል ኪዳን ሰብረው እርሱን ከማምለክ ዞር አሉ። በውጤቱም፣ የእርሱን ጥበቃ አጡ እንዲሁም ወደ ግዞት ወደቁ። ይሄ በተከሰተ ቁጥር፣ ጌታ የቃልኪዳን ህዝቡ ንሰሃ እንዲገባ እድሉን ሰጣቸው እንዲሁም የሚያድናቸውን፣ “መሳፍንት” የሚባል ወታደራዊ መሪ አስነሳ። በመጽሐፈ መሣፍንት ውስጥ የነበሩት መሣፍንት ሁሉ ቅዱስ አልነበሩም፣ ነገር ግን ጥቂቶቹ እስራኤልን ልጆች ለማዳን እና ከጌታ ጋር ወደነበራቸው የቃል ኪዳን ግንኙነት ለመመለስ ታላቅ እምነትን ተለማምደው ነበር። እነዚህ ታሪኮች የሚያስታውሱን ከኢየሱስ ክርስቶስ ያራቀን ምንም ቢሆን፣ እርሱ የእስራኤል ቤዛ እንደሆነ እና ሁሌም ሊያድነንና ወደ እርሱ ሊቀበለን ፍቃደኛ እንደሆነ ነው።
ስለመጽሐፈ መሣፍንት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መጽሐፈ መሣፍንት” የሚለውን ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
መሣፍንት 2፡1–19፤ 3:5–12
ንስሐ በገባሁ ቁጥር ጌታ ይቅር ይለኛል።
የመሳፍንት መጽሐፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ማበረታቻ ሊሆን ይችላል። መሳፍንት 2:1–19፤ 3፡5–12ን ስታነቡ ይህን ማስጠንቀቂያ እና ማበረታቻ ፈልጉ። ማስጠንቀቂያው እና ማበረታቻው ለእናንተ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው እንዴት ሆኖ ይሰማችኋል?
ለምሳሌ፣ መሳፍንት 2:19 ስለ ጥንቶቹ እስራኤላውያን ሳይሆን ስለ እናንተ እና ስለ ፈተናችሁ ቢሆን ኖሮ ምን ሊል ይችላል? መሣፍንት 3፡9 እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን ስላደረገው ነገር ቢሆን ምን ሊል ይችላል?
በለወጣቶች ጥንካሬ፡ ምርጫ የማድረግ መመሪያ ገጽ 9 ላይ ያለውን ጥያቄ እና መልስ ለማንበብ አስቡ። ይህ በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ ካለው የእስራኤላውያን ተሞክሮ ጋር እንዴት የሚገናኝ መስሎ ይሰማችኋል? ይህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምራችኋል?
መሣፍንት 4:1–15
ሌሎች በጌታ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማነሳሳት እችላለሁ።
አንዳንድ ጊዜ የአንድ ሰው እምነት በብዙ ሰዎች ላይ እምነትን ሊያነሳሳ ይችላል። በመሣፍንት 4 ውስጥ ያቺ ሰው ዲቦራ ነበረች። ስለ እሷ በመሣፍንት 4:1–15 ውስጥ አንብቡ፣ እንዲሁም በአከባቢዋ በነበሩ ሰዎች ላይ የነበራትን ተጽእኖ ልብ በሉ። የእሷ ተሞክሮ በህይወታችሁ ላይ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል እንድታስቡ የሚያግዟችሁ አንዳንድ ጥያቄዎች እዚህ ይገኛሉ።
-
በወቅቱ እስራኤላውያን ይኖሩበት የነበረውን ሁኔታ እንዴት ትገልጹታላችሁ? (ቁጥር 1-3 ይመልከቱ)። ዛሬ በግለሰቦች እንዲሁም በህብረተሰብ ውስጥ ካሉ ሁኔታዎች ጋር ምን አይነት መመሳሰሎችን ታያላችሁ?
-
ከዲቦራ ቃላት ወይም ድርጊቶች የትኞቹ በጌታ እምነት እንደነበራት ያሳዩአችኋል? እምነቷ በሌሎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ አሳደረ? ስለ እርሷ ሌላ ምን ያስደንቃችኋል?
-
ዲቦራ በቁጥር 14 ውስጥ “እግዚአብሔር በፊትህ [አልወጣምን]?” በማለት ስትጠይቅ ምን ማለቷ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ጌታ “ከፊታችሁ]” እንዴት ይወጣል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፡87–88 ይመልከቱ)።
የዲቦራ እምነት ባርቅንና ሌሎች እስራኤላውያንን እንደባረከው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁ እምነት ሌሎችን እንዴት እንደሚባርክ አስቡ። ስለዚህ እንድታስቡ እንዲረዳችሁ የሽማግሌ ኒል አንደርሰን “We Talk of Christ (ሊያሆና፣ ህዳር 2020፣ 88–91) የሚለውን መልእክት ልታጠኑ ትችላላችሁ። (1) ስለ አዳኙ በግልጽ ለመናገር ምክንያቶችን እና (2) ይህን ለማድረግ መንገዶችን ለማግኘት መልእክቱን አንብቡ።
ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታውቋቸውን ነገሮች ከቅዱሳት መጻህፍት፣ በህይወት ካሉ ነቢያት ቃል እና ከግል ልምዳችሁ መዘርዘር ትችላላችሁ። ይህንን ማወቅ ያለበት ማን ነው? እንዴትስ ልታካፍሉ ትችላላችሁ?
በተጨማሪ ማቴዎስ 5:14–16፤ 1 ጴጥሮስ 3:15፤“Each Life That Touches Ours for Good,” መዝሙሮች፣ ቁ.293 ይመልከቱ።
ማካፈልን ጋብዙ አስተማሪ ከሆናችሁ—በቤት ወይም በቤተክርስቲያን—”ተማሪዎች ስለአዳኙ እና ስለ ወንጌሉ የሚማሩትን ነገር አንዳቸው ለሌላቸው እንዲያካፍሉ ዕድል ስጡ። ይህንን ማድረጋቸው የተማሩትን እውነት ወደ ውስጥ እንዲያስገቡ እና እንዲገልጹ ይረዳቸዋል” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 26)። ለምሳሌ፣ መሳፍንት 4ን አንድ ላይ ስታጠኑ፣ እያንዳንዱ ተማሪ በምዕራፉ ውስጥ የተለየ ነገር እንዲያገኝ መስጠት እና ከዚያም ያገኙትን እንዲካፈሉ መጋበዝ ትችላላችሁ።
መሣፍንት 6–8
ጌታ በመንገዶቹ ላይ ስተማመን ተዓምራት ሊሰራ ይችላል።
መሳፍንት 6–8ን ስታነቡ፣ ጌታ የማይቻል የሚመስል ነገርን ጌዴዎን እንዲያምን የጠየቀባቸውን አጋጣሚዎች አስታውሱ። እናንተን ተመሳሳይ ነገር ጠይቋችሁ ያውቃል?
ጌታ በዚህ ምንባብ ምን ሊያስተምራችሁ እየሞከረ እንደሆነ ይሰማችኋል? የማይመስል በሚመስል መንገድ ጌታ ሥራውን ሲሠራ ያያችሁት እንዴት ነው?
መሣፍንት 13–16
ለቃል ኪዳኔ ታማኝ ስሆን እግዚአብሔር ያበረታኛል።
በተለይ ናዝራዊን የሚመለከቱትን ጨምሮ ከእግዚአብሔር ጋር የገባውን ቃል ኪዳኖች በመጣሱ፣ ሶምሶን አካላዊ እንዲሁም መንፈሳዊ ጥንካሬውን አጥቷል (ስለ ናዝራውያን መረጃ፣ ዘሁልቁ 6፥1–6፤ መጽሐፈ መሣፍንት 13፥7 ይመልከቱ)። በመሳፍንት 13-16 ስለ ሶምሶን ስታነቡ፣ ጌታ ከሶምሶን ጋር እንደነበረ እንዲሁም ሶምሶን ሙሉ በሙሉ ለጌታ እንዳልሰጠ የሚያሳዩ ጥቅሶችን አስተውሉ።
ከጌታ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳኖችንም ማሰላሰል ትችላላችሁ። እነዚህ ቃል ኪዳኖች ኃይሉን ወደ ህይወታችሁ ያመጡት እንዴት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ለገባችሁት ቃል ኪዳን ታማኝ በመሆን እንድትኖሩ የሚያነሳሳችሁን ከሶምሶን ተሞክሮዎች ምን ትማራላችሁ?
እህት አን ኤም ዲብ እንዲህ አስተምራለች፡ “ሶምሶን ሲወለድ ከታላቅ አቅም ጋር ነበር። እናቱ፣ ‘እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል’ (መሳፍንት 13፡5) የሚል ቃል ተገባላት። ነገር ግን ሶምሶን እያደገ ሲሄድ ከእግዚአብሔር መመሪያ ይልቅ ወደ ዓለም ፈተናዎች ይበልጥ ተመለከተ። ምርጫ ያደረገው እነዚህ ምርጫዎች ትክክል ስለነበሩ ሳይሆን ‘እጅግ ደስ [ስላሰኙት]’ [መሳፍንት 14:3] ነበር። ቅዱሳት መጻህፍት በተደጋጋሚ የሶምሶንን ጉዞ፣ ድርጊት እና ምርጫ ሲናገሩ ‘ወርዶም’ (መሳፍንት 14፡7) የሚለውን ቃል ይጠቀማሉ። ሶምሶን ታላቅ ችሎታውን ለመፈጸም ከመነሳት እና ከማብራት ይልቅ በአለም ተሸነፈ፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠውንም ሃይል አጣ እንዲሁም በአሳዛኝ ሁኔታ ያለጊዜው ሞተ። (“Arise and Shine Forth,” ሊያሆና, ግንቦት 2012 (እ.አ.አ) 118)።
በተጨማሪም ዳሊን ኤች ኦክስን፣ “Covenants and Responsibilities,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024፣ 93–96፣ ይመልከቱ።ዩሊሲስ ኦአሬስ “Covenant Confidence through Jesus Christ,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024፣ 17–21።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።
መሣፍንት 3:7–9፣ 12–15
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።
-
መሳፍንት 3 አዳኙ እኛን ከኃጢአት ለማዳን ስላለው ኃይል የሚያስተምር ንድፍን ይገልጻል። ልጆቻችሁ ይህንን ንድፍ እንዲያውቁ ለመርዳት፣ “ክፉ… አደረጉ፣” “ወደ እግዚአብሄር ጮሁ” እና “አዳኝ… አስነሳላቸው” የሚሉትን ሐረጎች መጻፍ ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ እነዚህን ሀረጎች በመሳፍንት 3፡7–9 እና በመሳፍንት 3፡12–15 ላይ መፈለግ ይችላሉ። ከዚህ ስለ ጌታ ምን እንማራለን?
-
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን መሆኑን ለማጉላት የኢየሱስን ሥዕል ጨምሮ የብዙ ሰዎችን ሥዕል በመሰብሰብ ገልብጣችሁ አስቀምጧቸው። ልጆቻችሁ ተራ በተራ ሥዕሎቹን እንዲገልጡ አድርጉ። የኢየሱስን ሥዕል ሲያገኙ፣ ስለ እርሱ መዝሙር ዘምሩ፣ ለምሳሌ “He Sent His Son” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 34–35) እንዲሁም እንዴት እንዳዳናችሁ ለልጆቻችሁ ንገሩ።
መሣፍንት 4:1–15
ሌሎች በጌታ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማነሳሳት እችላለሁ።
-
በመሳፍንት 4 ላይ ያለውን ታሪክ ለልጆቻችሁ ለመንገር በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 92–95 ላይ “ነቢይት ዲቦራ”ን መጠቀም ትችላላችሁ። ስለ ዲቦራ የምታደንቁትን አንዳችሁ ለሌላው አጋሩ። በጌታ ላይ ያላት እምነት በዙሪያዋ ያሉትን ሰዎች የባረከው እንዴት ነው? ሌሎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የበለጠ እምነት እንዲኖራቸው ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?
2:9Deborah the Prophetess
መሳፍንት 7፡1-21
ጌታ ትልቅ ስራን ለመስራት ትናንሽ ነገሮችን ሊጠቀም ይችላል።
-
ጌታ የእስራኤልን ጦር እንዴት እንዳሳነሰ ልጆቻችሁን ለማስተማር መሳፍንት 7፡4–7፣ የዚህ ሳምንት የአክቲቪት ገጽ ወይም “የጌዴዎን ጦር” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች 96–99 ተጠቀሙ። ጌታ የጌዴዎን ጦር በጣም ትንሽ እንዲሆን የፈለገው ለምንድነው? (መሳፍንት 7፡2 ይመልከቱ)።
2:37The Army of Gideon
-
ልጆቻችሁ የሰይፍ፣ የጋሻ፣ የመለከት፣ የመብራት እና የማሰሮ ምስል መሳል እና ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ የትኛውን በጦርነት ወቅት እንደሚፈልጉ መናገር ይችላሉ። ከዚያም ጌታ የጌዴዎን ሠራዊት እንዲጠቀም የነገረውን ለማወቅ መሣፍንት 7፡16ን ማንበብ ይችላሉ። በመሳፍንት 7፡19-21 ላይ ስላለው ጦርነት ስታነቡ፣ ከዚህ ታሪክ ስለጌታ የተማራችሁትን አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።
ሶምሶን ምሰሶዎችን ሲጥል፣ በጄምስ ቲሶት እና በሌሎች
መሣፍንት 13፥5
ቃል ኪዳኖችን መጠበቅ ብርታት ይሰጠኛል።
-
ከጌታ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ለሶምሶን ብርታት እንደሰጠው ሁሉ ቃል ኪዳኖቻችን ለእኛ ብርታት ይሰጣሉ። ልጆቻችሁ የተወሰነ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግ እና እነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዴት እንድንጠነክር እንደሚረዱን በመወያየት ሊደሰቱ ይችላሉ። ቃል ኪዳናችንን መጠበቅ መንፈሳችንን ጠንካራ የሚያደርገው እንዴት ነው? (ሞዛያ 18፡8–10፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፡77፣ 79 ይመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።