ኑ፣ ተከተሉኝ
ሚያዝያ 27–ግንቦት 3 (እ.አ.አ) “ቅድስና ለእግዚአብሔር”፡ ዘጸአት 35–40፤ ዘሌዋውያን 1፤ 4፤ 16፤ 19


“ሚያዝያ 27–ግንቦት 3 (እ.አ.አ) ‘ቅድስና ለእግዚአብሔር፦ ዘጸአት 35–40፤ ዘሌዋውያን 1፤ 4፤ 16፤ 19” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)

“ሚያዝያ 27–ግንቦት 3 (እ.አ.አ) ‘ቅድስና ለእግዚአብሔር’” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ሪዮ ደ ጀኒየሮ ብራዚል ቤተመቅደስ

ሪዮ ደ ጀኒየሮ ብራዚል ቤተመቅደስ

ሚያዝያ 27–ግንቦት 3 (እ.አ.አ)፡ “ቅድስና ለእግዚአብሔር”

ዘጸአት 35–40ዘሌዋውያን 141619

ግብፅን ትቶ መሄድ አስፈላጊ ቢሆነም፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች ያለውን ዓላማ ሙሉ በሙሉ አልፈጸመም። በተስፋው ምድር ውስጥ የተመቻቸ ህይወት እንኳን የእግዚአብሔር የመጨረሻ ዓላማ አልነበረም። እነዚህ እግዚአብሔር ለህዝቡ በእውነት ወደሚፈልገው መሻገሪያዎች ብቻ ነበሩ፥ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ” (ዘሌዋውያን 19፥2)። በምርኮ ለትውልዶች ከኖሩ በኋላ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዴት ቅዱስ ለማድረግ አቀደ? በምድረበዳ የቅድስና ቦታ—የማደሪያው ድንኳን እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው። ድርጊቶቻቸውን እንዲመሩ እና ልባቸውን ለመለወጥ ቃል ኪዳኖችን እና ህጎችን ሰጣቸው። ለኃጢአታቸውም ስርየት ያስተምራቸው ዘንድ የእንስሳትን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ አዘዛቸው። ይህ ሁሉ አእምሯቸውን፣ ልባቸውን እና ሕይወታቸውን ወደ አዳኙ ለመጠቆም ነበር። እርሱ ለእስራኤላውያን እና ለእኛ ወደ ቅድስና የሚመራ እውነተኛ መንገድ ነው። ሁላችንም በኃጢአት ምርኮ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ አሳልፈናል፣ ሁላችንም ኃጢአትን እንድንተው “ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥7) በማለት ቃል የገባውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተል ተጋብዘናል።

ስለዘሌዋውያን አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዘሌዋውያን” የሚለውን ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ዘጸአት 35–40ዘሌዋውያን 19

የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ ቅዱስ እንድሆን ይፈልጋል።

ዘፀአት 35–40 እስራኤላውያን ቅዱስ ህዝብ ይሆኑ ዘንድ የሚረዷቸው ሥርዓቶች የሚሰጡበት የማደርያውን ድንኳን የመስራት ጥረትን ይዘግባል። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ ጌታ ህዝቡ በድንኳኑ ውስጥ እንዲያኖሩ የጠየቃቸውን ነገሮች ፈልጉ። እነዚህ እቃዎች ምን ሊወክሉ ይችላሉ? በቅድስና ስለመጨመር ለእናንተ ምን ይጠቁማሉ? በተለይም እነዚህ ነገሮች ሀሳቦቻችሁን ወደ አዳኙ እንዴት እንደሚያዞሩ አስቡ። እንደ እነዚህ ያለ ሰንጠረዥ ሊረዳችሁ ይችላል፥

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

የቃል ኪዳኑ ታቦት (ዘጸአት 37፥1–940፥20–21)

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

(ዘጸአት 25፡20–22፤ የቅዱሳን መጽሃፎች መመሪያ፣ “የቃል ኪዳኑ ታቦት” የሚለውን ይመልከቱ)

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

የዕጣን መሠዊያ (ዘጸአት 40፥26–27፤ በተጨማሪም ዘጸአት 30፥1፣ 6–8ን ይመልከቱ)

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

(ራዕይ 8:3–4 ይመልከቱ)

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

የሻማ መቅረዝ ወይም የአምፖል መቅረዝ (ዘጸአት 37፥17–24

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

(ማቴዎስ 5:14–16ዮሃንስ 8:12 ይመልከቱ)

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

የመስዋዕት መሠዊያ (ዘጸአት 38፥1–7፤ በተጨማሪም ዘጸአት 27፥129፥10–14ን ይመልከቱ)

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

(የቅዱሳን መጽሃፎች መመሪያ፣ “መሥዋዕት” ተመልከቱ)

ምን አይነት እቃ አገኛችሁ?

መታጠቢያ ሰንና (ገንዳ) (ዘጸአት 30፥17–21)

ይሄ ምንን ሊወክል ይችላል?

(2 ዜና 4:6ኢሳይያስ 1:16ኤርምያስ 33:8 ተመልከቱ)

በእርግጥ በተቀደሱ ስፍራዎች መሆናችን ብቻ ቅዱስ አያደርገንም። ዘሌዋውያን 19 እስራኤላውያን ቅድስናቸው እንዲጨምር እግዚአብሔር የሰጣቸውን ህጎች እና ትእዛዛት ይገልጻል። ከጌታ ቅድስናን እንድትፈልጉ የሚረዷችሁን በእነዚህ ትእዛዛት ውስጥ ምን ታገኛላችሁ? እነዚህን መርሆች በተሟላ ሁኔታ ለመኖር ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል?

እንዲሁም ሄንሪ ቢ. አይሪንግን፣ “Holiness and the Plan of Happiness,” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 100–103፣ ይመልከቱ። “The Tabernacle” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ።

7:19

The Tabernacle

መዝሙር ተጠቀሙ። መዝሙር የመንፈስን ተፅእኖ ለመጋበዝ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን ለመገንባት ታላቅ ኃይል አለው። በመዝሙሮች ውስጥ ያሉት መልእክቶች ብዙውን ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለውን ትምህርት ያጠናክራሉ። ለምሳሌ፣ እንደ “More Holiness Give Me” (መዝሙር ቁ. 131) ያለ መዝሙር መዘመር በዘሌዋውያን 19 ላይ የሚገኙ አንዳንድ አስተምሮቶችን መልእክቶች ያጠናክራል። እንዲሁም እንደ አዳኙ የበለጠ ቅዱስ መሆን ምን ማለት እንደሆነ እንድታስቡ እና እርሱ ቅድስናን እንድትጨምሩ እንዴት እየረዳችሁ እንደሆነ እንድታስቡ ሊረዳችሁ ይችላል።

ዘጸአት 35:4–3536:1–7

ጌታ በፈቃደኝነት መስዋእቴን እንዳቀርብ ይጠይቀኛል።

ከግብፅ ከወጡ ከአመት በኋላ የእስራኤል ልጆች ከያህዌህ ጋር ያላቸው ግንኙነት ተለዋዋጭ ነበር ማለት ይቻላል። ሆኖም፣ ዘጸአት 35፥4 እና 36፥7ን በምታነቡበት ጊዜ እስራኤላውያን የማደርያ ድንኳኑን ለመገንባት ለተሰጠው ትእዛዝ እንዴት ምላሽ እንደሰጡ ልብ በሉ። ከእስራኤላውያን እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ሊረዳችሁ የሚችል ምን ትማራላችሁ?

እናንተን ለድንኳን የሚሆን የከበረ ብረቶች፣ የተልባ እግር ወይም እንጨት ላይጠይቃችሁ ይችላል። ጌታ ምን ሰጥቷችኋል እንዲሁም ምን እንድትሰጡት እየጠየቃችሁ ነው? “ሥራውን ለመሥራት… ል[ባችሁ] [የተነሳሳው]” መቼ ነው?

በተጨማሪም፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “መስዋዕት፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

እስራኤላዊያን ለድንኳኑ ስጦታ እየሰበሰቡ

የእስራኤል ልጆች ለድንኳኑ “[በ]ልብ ፍቃድ” ስጦታ አቅርበዋል (ዘጸአት 35፥5)። በኮርበርት ጎዚየር የተሳለ ምስል © Lifeway Collection/licensed from goodsalt.com

ዘጸአት 40:12–14

የቤተመቅደስ ሥርዓቶች በጥንት ጊዜ ይሰጡ ነበር።

ዘጸአት 40፡12–14 የሚያመለክተው በዘመናችንም በጌታ ቤት ውስጥ ስለሚደረጉ ጥንታዊ ስርዓቶችን ነው። እነዚህ ስርዓቶች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚመሰክሩ ለመማር የሚረዷችሁ አንዳንድ ተጨማሪ ጥቅሶች እነዚህ ናቸው፥

  • መታጠብ፡ መዝሙር 51:2ሕዝቅኤል 36:25-27

  • የተቀደሰ ልብስ መልበስ፡ ኢሳይያስ 61፡10ማቴዎስ 22:11-14ራእይ 19:7-8

  • መቀባት፡ ሉቃስ 4፡18–19የሐዋርያት ሥራ 10፡38

ዘሌዋውያን 1፥1–9416

በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት በኩል ይቅር ልባል እችላለሁ።

እንደ የእንስሳት መስዋዕቶች፣ ደምን እና ውሃን ያካተቱ ሥነ ሥርዓቶች እና የህይወትን ዝርዝር ጉዳዮች የሚመለከቱ ሕጎችን የያዘው አብዛኛው የዘሌዋውያን መጽሐፍ ለእኛ እንግዳ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ሥነ-ሥርዓቶች እና ህጎች የተለመዱ መርሆዎችን፣ እንዲሁም ንስሀ መግባትን፣ ቅድስናን እና የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ ለማስተማር የተደረጉ ነበሩ። እነዚህን መርሆዎች ለማግኘት ዘሌዋውያን 1:1–94፤ 16ን ስታነቡ እነዚህን ስለመሳሰሉ ጥያቄዎች አስቡ፥

  • ኢየሱስ ክርስቶስን እና የኃጢያት ክፍያውን የሚያስታውሱኝን የትኞቹን ቃላት ወይም ሀረጎች አገኛለሁ?

  • ከእነዚህ መስዋዕቶች ስለአዳኙ መስዋዕትነት ምን እማራለሁ?

  • እኔ እንዴት እነዚህን መስዋእቶች እንዳደረጉት ሰዎች ነኝ?

ጌታ የእንስሳት መሥዋዕት አይፈልግም። ነገር ግን መስዋዕትነት አሁንም ጠቃሚ የወንጌል መርህ ነው። ጌታ ስለሚፈልገው አይነት መሥዋዕት ለማወቅ፣ 3 ኔፊ 9፡19–20ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፡34ን አጥኑ። እንደዚህ አይነት መስዋዕቶችን እንዴት እያቀረባችሁ ነው? ሙሴ 5:7 መሥዋዕቶቻችሁን እንዴት መመልከት እንዳለባችሁ ምን ያስተምራችኋል?

በተጨማሪ “Thoughts to Keep in Mind: The Tabernacle and Sacrifice.” የሚለውን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘጸአት 35:20–2936:1

እግዚአብሔር በሥራው እንድረዳ ስጦታዎችን ሰጥቶኛል።

  • በዚህ መግለጫ መጨረሻ ላይ የእስራኤላውያን የምድረበዳ የማደሪያ ድንኳን ሥዕል አለ። ከልጆቻችሁ ጋር ልትመለከቱት ትችላላችሁ እንዲሁም የማደሪያውን ድንኳን ለመሥራት ምን ቁሳቁሶች አስፈልጓቸው እንደነበር ጠይቋቸው። ከዚያም እነዚህ ቁሳቁሶች እንዴት እንደቀረቡ ለማወቅ ዘፀአት 35:20-29ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ጌታ መንግሥቱን ለመገንባት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንድናደርግ የጋበዘን እንዴት ነው?

  • እግዚአብሔር ባስልኤልና ኤልያብ የማደሪያውን ድንኳን ለመሥራት እንዲረዱ ምን እንደሰጣቸው ለማወቅ ዘጸአት 36፡1ን በአንድነት አንብቡ። ከዚያም ጌታ መንግስቱን ለመገንባት እንዲረዱ እንደሰጣቸው ስለሚሰማችሁ ነገር ከልጆቻችሁ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ። እነዚህን ነገሮች ሌሎችን ለመባረክ ልንጠቀምባቸው የምንችለው እንዴት ነው?

የሮም ጣልያን ቤተመቅደስ

የሮም ጣልያን ቤተመቅደስ

ዘጸአት 40፡17-34

በተቀደሱ ቦታዎች የጌታ መገኘት ሊሰማኝ ይችላል።

  • ዘጸአት 40፡17–34 የእስራኤላውያን የማደሪያ ድንኳን ክፍል የሆኑትን ነገሮች ይዘረዝራል። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ እንዲሁም በዚህ ማብራሪያ መጨረሻ ላይ ከሚገኘው የማደሪያው ድንኳን ሥዕል ላይ ልታገኟቸው ትችላላችሁ። እያንዳንዱ የድንኳኑ ክፍል ስለ አዳኙ ወይም የሰማይ አባት እንዴት ሊያስተምር እንደሚችል ተነጋገሩ። ለምሳሌ፣ የምስክሩ ታቦት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት፣ መሠዊያው ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት እና የመሳሰሉትን ሊያስታውሱን ይችላሉ።

  • ዛሬ ላይ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ እንድንቀርብ የሚረዱን ምን ቅዱስ ቦታዎች አሉን? እንደዚህ ውይይት አካል፣ “Temples” (የወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ አብራችሁ መመልከት ትችላላችሁ። እንዲሁም እንደ “Holy Places” (የወንጌል ላይብረሪ) ያለ መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። እንደ ቤተ መቅደስ ስላሉ ቅዱስ ቦታዎች የሚሰማችሁን ስሜት አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።

5:41

What Is a Temple?

ዘሌዋውያን 1:1–4

በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት በኩል ይቅር ልባል እችላለሁ።

  • በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጹት የእንስሳት መሥዋዕቶች ለእስራኤል ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ስለ ይቅርታ ለማስተማር የታሰቡ ናቸው። ስለእነዚህ መሥዋዕቶች ማንበብ ለልጆቻችሁም በተመሳሳይ መልኩ እንዴት እንደሚረዳ አስቡ። ከልጆች ጋር ዘሌዋውያን 1፡1–4ን ስታነቡ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕሎች በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ ማሳየት ትችላላችሁ (የወንጌል አርት መጽሐፍ ቁጥር 5657 ይመልከቱ)። የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት የሚያስታውሷቸውን ቃላትን ወይም ሀረጎች እንዲያገኙ እርዷቸው።

  • እንዲሁም በእንስሳት ምትክ እንድንሰዋ የታዘዝነውን ለማወቅ 3 ኔፊ 9፡19–20ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስን ለጌታ ማቅረብ ማለት ምን ማለት ነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት እንዲረዳችሁ የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ “የተሰበረ ልብ” (የወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

የጥንት ድንኳን

የጥንቱ ድንኳን፣፣ በብራድሊ ክላርክ

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ በተቀደሱ ቦታዎች የእግዚአብሔር መገኘት ይሰማኛል።