ኑ፣ ተከተሉኝ
ግንቦት 18–24 (እ.አ.አ)። “ጽኑ፥ አይዞአችሁ”፡ ኢያሱ 1–8፤ 23–24


“ግንቦት 18–24 (እ.አ.አ)። ‘ጽኑ፥ አይዞአችሁ፣’”ኢያሱ 1–8፤ 23–24፡ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 18–24 (እ.አ.አ)። ‘ጽኑ፥ አይዞአችሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ሙሴ ኢያሱን እየባረከ

ሙሴ ኢያሱን እየሾመ፣ በዳረል ቶማስ (ዝርዝር)

ግንቦት 18–24 (እ.አ.አ)፡ “ጽኑ፥ አይዞአችሁ”

ኢያሱ 1–823–24

በርካታ ትውልዶችን ቢወስድም የጌታ የተስፋ ቃል ሊፈፀም ተቃርቧል፦ የእስራኤል ልጆች የተስፋውን ምድር ለመውረስ በስተመጨረሻ ጫፍ ላይ ነበሩ። ነገር ግን የዮርዳኖስ ወንዝ፣ የኢያሪኮ ቅጥር እና ጌታን የካዱ ሃያላን ሰዎች በመንገዳቸው እንቅፋት ሆኑ (1 ኔፊ 17፥35ን ይመልከቱ)። ይህንን ሁሉ የሚወዱት መሪ ሙሴ በሌለበት ሊጋፈጡ ነው። ሁኔታው አንዳንድ እስራኤላዊያንን ደካማነት እና ፍራቻ እንዲሰማቸው አድርጎ ይሆናል፣ ነገር ግን ጌታ “ጽኑ፥ አይዞአችሁ” አላቸው። እንዲበረቱ ምን አይነት ምክንያት ነበራቸው? በራሳቸው—ወይም በሙሴ ወይም በኢያሱ—ጥንካሬ ሳይሆን “[በሚሄዱበት ሁሉ አምላካቸው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር” (ኢያሱ 1፥9) ስለሚሆን ነው። እኛ የምናቋርጠው የራሳችን ወንዝ እና የምንጥለው ግድግዳ ሲኖረን በሕይወታችን ውስጥ አስደናቂ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ ምክንያቱም “እግዚአብሔር በመካከ[ላችን] ድንቅ ነገር [ስለሚያደርግ]” (ኢያሱ 3፥5) ነው።

ስለመፅሐፈ ኢያሱ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መፅሐፈ ኢያሱ” የሚለውን ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢያሱ 1፥1–9

ለእርሱ ታማኝ ለመሆን ስጥር እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ይሆናል።

ሙሴን እንዲተካ መጠራቱ ለኢያሱ ምን ይመስል እንደነበር አስቡት። ጌታ በኢያሱ 1፥1–9 ውስጥ እርሱን ሊያበረታታው ምን እንዳለ አስተውሉ። ስለሚገጥሟችሁ አስቸጋሪ ፈተናዎች አስቡ፤ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ ብርታትን ይሰጧችኋል?

ኢያሱ (በዕብራይስጥ ዬሁሻ ወይም ዬሹዋ) የሚለው ስም “ያህዌህ ያድናል” ማለት ነው። ኢየሱስ የሚለው ስም የመጣው ከዬሹዋ ነው። ስለዚህ ስለ ኢያሱ በምታነቡበት ጊዜ የእስራኤልን ልጆች የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደገቡ በመምራት የተጫወተውን ሚና ተመልከቱ። የእሱ ተልእኮ ክርስቶስ ለእኛ ካደረገልን ጋር እንዴት ይመሳሰላል?

ኢያሱ 1፡8

የሴሚናሪ ምልክት
የእግዚአብሔር ቃል መንገዴን የበለፀገ ያደርገዋል።

ጌታ ኢያሱን ሲያበረታታ በኢያሱ 1፡8 ላይ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም “የሕግ መጽሃፍ” ምክር ሰጥቶታል። የኢያሱን ከባድ ኃላፊነት ስንመለከት ይህ ምክር በተለይ ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው ለምንድነው?

ጌታ ቅዱሳት መጻህፍትን እንድናነብ ሲጋብዘን ቃላትን ከማንበብ ባለፈ መልኩ ብዙ ጊዜ ይጠቀማል። ታላቅ በረከትንም ቃል ይገባል። ከታች ያለው ሰንጠረዥ እነዚህን ግብዣዎች እና ቃል የተገቡ በረከቶችን እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል፡

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

ኢያሱ 1፡8

ግብዣ

በቀንም በሌሊትም አስበው

ቃል የተገቡ በረከቶች

1 ኔፊ 15፡23–24

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

2 ኔፊ 32፡3

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

ሞዛያ 1፡7

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

በምድሪቱ ላይ መበልጸግ

ሔለማን 3:29–30

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥85

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

ረሴል ኤም. ኔልሰን፣ “ስሙት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ.)፣ በገጽ 89 የመጨረሻው አንቀጽ

ግብዣ

ቃል የተገቡ በረከቶች

ጌታ እነዚህን ተስፋዎች በህይወታችሁ የፈፀመው እንዴት ነው? ቅዱሳን መጻህፍትን የማጥናት ልማዳችሁን ለመገምገም አሁን ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። ጥሩ እየሄደ ያለው ምንድነው? በእግዚአብሄር ቃል ላይ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖራችሁ ምን መነሳሳት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም “As I Search the Holy Scriptures ፣” መዝሙር፣ ቁ. 277 ይመልከቱ።

ኢያሱ 2

እምነት እና ስራ ሁለቱም ለደህንነት አስፈላጊ ናቸው።

የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ረዓብን የእምነትም እንዲሁም የሥራ ኃያል ምሳሌ አድርገው ይመለከቷት ነበር ( ዕብራዊያን 11፥31ያዕቆብ 2፥25ን ይመልከቱ)። እናንተ ኢያሱ 2ን ስታነቡ፣ እራሷን፣ ቤተሰቧን እና የእስራኤልን ሰላዮች በማዳን ረገድ የረዓብ እምነት እና ስራ ምን ሚና እንዳለው አስቡ። በክርስቶስ ላይ ያላችሁ እምነት እና ስራዎቻችሁ በእናንተ እና በሌሎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ይህ ምን ያስተምራችኋል?

ረዓብ በመስኮትዋ ወደ ውጭ እያየች

ረዓብ በመስኮትዋ። ተስፋውን መጠበቅ፣ በኤልስፒት ያንግ (ዝርዝር)

ኢያሱ 3–4

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን፣ የእግዚአብሄርን “ድንቅ ነገር” ማየት እችላለሁ።

ጌታ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲመራቸው በህዝቡ መካከል ድንቅን አድርጓል፣ ለእናንተም እንዲሁ ማድረግ ይችላል። የኢያሱ 3–4ን ጥናታችሁን እንዲመራ አንዳንድ ጥያቄዎች እዚህ ይገኛሉ።

  • እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ከመሻገራቸው በፊት ራሳቸውን መቀደስ ያስፈለጋቸው ለምን ይመስላችኋል? (ኢያሱ 3፥5 ተመልከቱ)።

  • “የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ” ብቻ ወንዙ እንደተከፈለ ልብ በሉ (ኢያሱ 3:13፣ 15)። ይህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ሌሎች በርካታ ጉልህ ክስተቶች ተከስተዋል—2 ነገሥት 2፥6–155፥1–14፤ እና ማርቆስ 1፥9–11ን ተመልከቱ። በእነዚህ ክስተቶች መካከል ምን ዓይነት ግንኙነቶችን ታያላችሁ?

  • ጌታ በህይወታችሁ “ድንቅን” ያደረገው እንዴት ነው (ኢያሱ 3፥5)። እነዚያን ድንቅ ነገሮች በብዛት እንዴት ልትለማመዱ ወይም ልትገነዘቡ ትችላላችሁ? (ለምሳሌ ኢያሱ 3፥17ን ን ይመልከቱ)።

ኢያሱ 6–8

መታዘዝ የእግዚአብሔርን ኃይል ወደ ሕይወቴ ይጋብዝል።

ኢያሱ 6–8 በኢያሪኮ እና በአይ መሬት ስለሚደረጉ ውጊያዎች ይናገራሉ። እንዚህን ስታነቡ፣ ፈተናን እንዴት እንደምትዋጉ አስቡ (ለምሳሌ፣ ኢያሱ 7፥10–13ን ይመልከቱ)። እግዚአብሔር እንዴት ሊረዳችሁ እንደሚችል እና የእርሱን ኃይል ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፣ ኢያሪኮን ለመውሰድ ጌታ በሰጠው መመሪያ የትኛው ያስደንቃችኋል? (ኢያሱ 6፥1–5ን ይመልከቱ)። ምናልባት በኢያሱ 7 ውስጥ ያለው መዝገብ በሕይወታችሁ ውስጥ ማስወገድ ያለባችሁን “የተረገመ ነገር” እንዳለ ለማወቅ ያነሳሳ ይሆናል (ኢያሱ 7፥13)።

ኢያሱ 23–24

“የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ።”

ኢያሱ 23-24 ውስጥ ኢያሱ ለእስራኤላውያን የሰጠው የመጨረሻ ትምህርት ጠቃሚ ማስጠንቀቂያዎችን፣ ምክሮችን እና ተስፋ የተደረጉ በረከቶችን ያጠቃልላል። ስለምታገኙት ዝርዝር ማውጣት ትችላላችሁ። እስራኤላውያን ያለፉበትን ሁሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢያሱ በሕይወቱ መጨረሻ እነዚህን ነገሮች ለእነሱ ለመንገር የመረጠው ለምን ይመስላችኋል? “ወደ አምላካችሁ [ለመጠጋት]” ምን ያነሳሳችኋል? (ኢያሱ 23፥8)።

በተጨማሪም ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “በዛሬ ቀን ምረጡ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 104–6 ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኢያሱ 1–4፤ 6

“ጽና፥ አይዞህ”

  • ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት “[እንዲጸኑ እና እንዲበረቱ]” (ኢያሱ 1:6) ልንረዳ የምንችልበት አንዱ መንገድ እዚህ ይገኛል። በኢያሱ 1፡6፣ 9 እና 18 ላይ የተደጋገመ ሀረግ እንዲፈልጉ ጋብዟቸውና እንዲጽፉት ወይም በቃላቸው እንዲይዙ አድርጓቸው። ልጆቻችሁ ልክ እንደ ኢያሱ ይህ መልእክት ሊያስፈልጋቸው የሚችሉ ሁኔታዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው። በኢያሱ 1-46 ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ታሪኮች አንድ ላይ መከለስ ትችላላችሁ (በተጨማሪም “ነቢዩ ኢያሱ” እና “ረዓብ እና ሰላዮቹ” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 85–91 ይመልከቱ)። በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ያሉት ሰዎች በጌታ ድፍረትንና ብርታትን ያሳዩት እንዴት ነው?

    2:59

    Joshua the Prophet

    1:39

    Rahab and the Spies

ኢያሱ 1፡8

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት በረከቶችን ያመጣልኛል።

  • ኢያሱ 1:8ን ማንበብ ልጆቻችሁ ቅዱሳት መጻህፍትን በራሳቸው እንዲያነቡ ሊያነሳሳቸው ይችላል። ቅዱሳት መጻህፍትን እንዴት እና ለምን ማንበብ እንዳለብን የሚያስተምሩ ቃላትን በዚህ ጥቅስ ውስጥ እንዲያገኙ እርዷቸው። በ1 ኔፊ 15፡23–242 ኔፊ 31፡2032:3ያዕቆብ 4:6ሔለማን 3፡29–30 ተመሳሳይ ነገርን መፈለግ ይችላሉ። ቅዱሳት መጻህፍትን ለማንበብ እቅድ በማውጣት እንዲፈጽሙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ።

ኢያሱ 3–4

ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት መጠመቅ አለብኝ።

  • እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገሩበትን ታሪክ—አሮጌውን ህይወታችንን በምድረ በዳ በመተው ከእግዚአብሔር ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት መጀመርን እንደ ጥምቀት ምሳሌ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ስለዚህ ኢያሱ 3–4ን (ወይም “ነቢዩ ኢያሱ”ን በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 85–89) አብራችሁ ስታነቡ፣ ኢየሱስ ሲጠመቅ የሚያሳይ ሥዕል ማየትና ኢየሱስ የተጠመቀው እስራኤላውያን በተሻገሩበት ወንዝ መሆኑን ማስረዳት ትችላላችሁ። ከዚያም እንደ “Baptism” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 100–101) ያለን መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። መጠመቅ በኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት ውስጥ አዲስ ሕይወት እንደመጀመር እንዴት እንደሆነ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

    2:59

    Joshua the Prophet

ኢየሱስ እና አንድ ወጣት ሲጠመቁ የሚያሳይ ምስል

ኢያሱ 24፥15

ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል መምረጥ እችላለሁ።

  • ኢያሱ እስራኤላውያንን እንዲያደርጉ እንደጋበዘ ሁሉ ልጆቻችሁም ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል እንዲመርጡ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? የሚከተሉትን ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፡-

    • ኢያሱ 24፡15 አንድ አጠር ያለን ሐረግ በቃላቸው እንዲይዙ። ለልጆቻችሁ አስደሳች ለማድረግ ሞክሩ። በቃላቸው የሚይዙት የቃላት ብዛት በእድሜያቸው የተመሰረተ ሊሆን ይችላል።

    • ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ስለመረጡ ሰዎች ታሪኮችን እንዲያገኙ። በጓደኛ መጽሔት፣ በየወንጌል አርት መጽሐፍ፣ ወይም የብሉይ ኪዳን ታሪኮች እና በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ታሪኮች መጻሕፍት ውስጥ መመልከት ይችላሉ።

    • አዳኙን ለመከተል እና ለማገልገል የሚመርጡበትን ሁኔታዎች እንዲተውኑ

የተለያዩ አክቲቪቲዎችን ተጠቀሙ። “ሁሉም ልጆች የተለዩ ናቸው እንዲሁም እያደጉ ሲሄዱ ፍላጎታቸው ይቀየራል። የማስተማር ዘዴያችሁን መቀያየር የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን እንድታሟሉ ይረዳችኋል” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር31)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

Placeholder

ወደ ዮርዳኖስ የመጀመርያ የእምነት እርምጃ፣ በትሬንት ጉድመንድሰን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት መጠመቅ አለብኝ