ኑ፣ ተከተሉኝ
ግንቦት 4–10 (እ.አ.አ)። “በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣… አትፍሩ”፡ ዘኍልቍ 11–14፤ 20–24፤ 27


“ግንቦት 4–10 (እ.አ.አ)። ‘በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ፡ ዘኍልቍ 11–14፤ 20–24፤ 27፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 4–10 (እ.አ.አ)። ‘በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

የዋዲ ራም ፎቶ

በሲና በአብዛኛው በውሃ የተከበበ መሬት አጠገብ ያለ ምድረበዳ

ግንቦት 4–10 (እ.አ.አ)፥ “በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ”

ዘኍልቍ 11–1420–2427

በእግር ቢሆን እንኳን ከሲና ምድረበዳ ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ከነዓን ለመጓዝ 40 ዓመት አይፈጅም ነበር። ነገር ግን የእስራኤል ልጆች የፈጀባቸው ያን ያህል ጌዜ ነበር—ያም የእስራኤል ልጆች የጂኦግራፊያዊ ርቀትን ሳይሆን መንፈሳዊ ርቀትን ለመጓዝ ያስፈለጋቸው ጊዜ ነበር፡ ማን እንደነበሩ እና ጌታ እንደ ቃል ኪዳን ህዝቦቹ እንዲሆኑ በፈለገው መካከል ያለው ርቀት ማለት ነው።

የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸው በፊት መማር የሚያስፈልጋቸውን ትምህርቶች ጨምሮ፣ ኦሪት ዘኍልቍ በእነዚያ 40 ዓመታት ውስጥ የተከናወኑትን አንዳንድ ነገሮች ይገልጻል። ለጌታ አገልጋዮች ታማኝ ስለመሆን ተምረዋል (ዘኍልቍ 12ን ይመልከቱ)። ወደፊታቸው ተስፋ የሌለው ቢመስልም እንኳ በጌታን ሃይል ስለመተማመን ተምረዋል (ዘኍልቍ 13–14ን ይመልከቱ)። እንዲሁም እምነት ማጣት መንፈሳዊ ጉዳት እንደሚያመጣ፣ ነገር ግን ንሰሃ መግባት እና ለመዳን ወደ አዳኙ መመልከት እንደሚችሉ ተምረዋል (ዘኍልቍ 21፥4–9ን ይመልከቱ)።

ሁላችንም በአንዳንድ መልኩ እንደ እስራኤላዊያን ነን። በመንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ መሆን ምን እንደሚመስል ሁላችንም እናውቃለን እንዲሁም የተማሯቸው ተመሳሳይ ትምህርቶች ወደራሳችን የቃል ኪዳን ምድር እንድንገባ፣ ማለትም ከሰማይ አባታችን ጋር ለዘለአለም ለመኖር እንድንዘጋጅ ሊረዱን ይችላሉ።

ስለኦሪት ዘኍልቍ አጭር ማብራሪያ በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘኍልቍ” የሚለውን ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ዘኍልቍ 11፥11–17፣ 24–2912

መገለጥ ሁሉም መቀበል የሚችለው ነው ነገር ግን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን የሚመራው በነቢዩ በኩል ነው።

ዘኍልቍ 11፥11–17፣ 24–29፣ ሙሴ የሚያጋጥመውን ችግር እና እግዚአብሔር የሰጠውን ምላሽ አስተውሉ። “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ” ብሎ ሲመኝ ሙሴ ምን ማለቱ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ? (ቁጥር 29)። ይህን ጥያቄ ስታሰላስሉ፣ በፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “Revelation for the Church, Revelation for Our Lives” ((ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93-96) መልዕክት ውስጥ ያሉትን መልሶች ፈልጉ።

ሁላችንም መገለጥ መቀበል እንችላለን ማለት ግን ሁላችንም እንደ ሙሴ የእግዚአብሔርን ህዝብ መምራት እንችላለን ማለት አይደለም። በዘኍልቍ 12 የተፈጠረው ክስተት ይህንን ግልጽ ያደርጋል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ምን ማስጠንቀቅያ ታገኛላችሁ? ስለግላዊ መገለጥ እና ነብዩን ስለመከተል ጌታ እንድትረዱ የሚፈልገው ምን እንደሆነ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 10፥17ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥1–7፤ ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ “Two Lines of Communication,” ሊያሆና፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 83–86ን ይመልከቱ።

ከሁሉ አስፈላጊ በሆነው ላይ አተኩሩ። አንዳንድ ሰዎች ኑ፣ ተከተሉኝ በሚለው ሳምንታዊ የንባብ ጥቆማዎች ይጨናነቃሉ። ይህን ጽሁፍ ስታነቡ፣ መንፈስን ተከተሉ። የእናንተን እና እናንተ የምታስተምሯቸውን ሰዎች ፍላጎት ግምት ውስጥ አስገቡ። በአንድ ሳምንት ውስጥ አንድን መርሆ መረዳት እና ሙሉ በሙሉ መተግበር ላይ ላዩን ብዙ ምዕራፎችን ከማንበብ የበለጠ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ዘኍልቍ 12፥3

“ሙሴ … እጅግ ትሑት ነበር።”

አንዳንድ ሰዎች በፈርዖን ፊት ቆሞ በጌታ ሃይል ድንቅ ተአምራትን ያደረገው ታላቁ መሪ ሙሴ፣ “እጅግ ትሑት” እንደነበረም ሲማሩ ይገረማሉ (ዘኁልቁ 12፡3)። ትሁት መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በመልእክታቸው “Meek and Lowly of Heart” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 30–33) ውስጥ ስለ ትህትና የሰጡትን ማብራሪያ መከለስ ወይም በ “የዋህ፣ የዋህነት” በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (የወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ማጥናት ትችላላችሁ።

ዘጸአት 18፡13–25ዘኍልቍ 11:26–29ዘኍልቍ 12ዕብራውያን 11:24–27፤ እና ሙሴ 1፡10–11 ላይ ከሙሴ የትህትና ምሳሌዎች ምን ትማራላችሁ? በተጨማሪም አዳኙ እንዴት ትህትና እንዳሳየ ማሰላሰል ትችላላችሁ (ማቴዎስ 11:2927:11–14ሉቃስ 22:41–42ዮሐንስ 13:4–5 ተመልከቱ)። እነዚህ ምሳሌዎች ምን ያስተምሯችኋል?

ዘኍልቍ 13–14

በጌታ በመተማመን፣ ለወደፊቱ ተስፋ ሊኖረኝ ይችላል።

ዘኍልቍ 13–14 ስታነቡ፣ እራሳችሁን በእስራኤላውያን ቦታ ለማድረግ ሞክሩ። “ወደ ግብፅ መመለስ” ለምን የፈለጉ ይመስላችኋል? (ዘኍልቍ 14፥3)። ካሌብ የነበረውን ሌላ “መንፈስ” እንዴት ትገልፁታላችሁ? ዘኍልቁ 14:24)። ስለ ካሌብ እና ኢያሱ እምነት ምን ያስደንቃችኋል፣ እንዲሁም ምሳሌያቸውን በሚገጥሟችሁ ሁኔታዎች ላይ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

ሙሴና አንዳንድ እስራኤላዊ ሰላዮች

ከእስራኤል ሰላዮች መካከል አሥሩ ፈርተው ነበር፣ ኢያሱና ካሌብ ግን እምነት ነበራቸው። ኢያሱ እና ካሌብ፡ ታዛዥ ሰላዮች፣ በዳግላስ ክላውባ © ላይፍዌይ ስብስብ/ፈቃድ ከ goodsalt.com

ዘኍልቍ 21፥4–9

የሴሚናሪ ምልክት
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት ከተመለከትኩ፣ በመንፈስ ሊፈውሰኝ ይችላል።

ዘኍልቍ 21፥4–9 ውስጥ የተመዘገበውን ታሪክ የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢያት ያውቁት ነበር እንዲሁም መንፈሳዊ ጠቀሜታውን ተረድተው ነበር። ስለዚህ ታሪክ ትምህርቶቻቸውን በ1 ኔፊ 17፡40–41አልማ 33፡18–22 እና ሔለማን 8፡13–15 ላይ አንብቡ። ይህን ስታደርጉ ልታሰላስሉ የምትችሏቸው አንዳንድ ጥያቂዎች እነዚህ ናቸው፥

  • የናሱ እባብ ምንን ሊወክል ይችላል?

  • በእባብ መነደፍ ምንን ሊያመለክት ይችላል?

  • ለመፈወስ እስራኤላውያን “የናሱን እባብ [መመልከት]” (ዘኍልቍ 21፥9) ነበረባቸው። አንዳንድ ሰዎች ለማየት ፈቃደኛ ያልነበሩት ለምን ይመስላችኋል? ተመሳሳይ ነገር በእናንተ ላይ ደርሶ ያውቃል?

  • ሙሉ ለሙሉ “በእምነት የእግዚአብሔርን ልጅ [ለመመልከት]” እና ለመፈወስ ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል? (ሔለማን 5፥12)።

እነዚህን ማንበብ ሰዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ትኩረታቸውን በክርስቶስ ላይ ማድረግ ስለነበረባቸው ሌሎች ጊዜያትን ሊያስታውሳችሁ ይችላል። ለምሳሌ፣ የዘኍልቍ 21፡4–9 መልእክት ከማቴዎስ 14፡25–31 እና 1 ኔፊ 8፡24–28 ጋር አወዳድሩ (በዚህ ሳምንት ዝርዝር መጨረሻ ላይ ያሉትን ሥዕሎችም ይመልከቱ)። ከክርስቶስ እንድንርቅ የሚያደርገን ምንድን ነው? በእርሱ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሰዎችን የሚባርከው እንዴት ነው?

በተጨማሪም “Jesus, the Very Thought of Thee፣” መዝሙሮች፣ ቁጥ 141ን ይመልከቱ።

ዘኍልቍ 22–24

ሌሎች እንዳላደርገው ሊያሳምኑኝ ቢሞክሩም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል እችላለሁ።

የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ እስራኤላውያን እየቀረቡ መሆናቸውን ባወቀ ጊዜ በረከትን እና እርግማንን በመናገር የታወቀውን ሰው በለዓምን ጠራ። ባላቅ እስራኤላውያንን እንዲረግም ፈለገ። ባላቅ በለዓምን ለማሳመን እንዴት እንደሞከረ ልብ በሉ (ዘኍልቍ 22፥5–7፣15–17)፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ፈቃድ በተቃራኒ እንድትሄዱ የሚገጥሟችሁን ፈተናዎች አስቡ። በዘኍልቍ 22፥18፣ 3823፥8፣ 12፣ 2624፥13 ውስጥ ያለው የበለዓም ምላሽ ምን ያስደንቃችኋል? አሳዛኙ ነገር፣ በለዓም በመጨረሻ በግፊቱ ተሸንፎ እስራኤልን ከዳ (ዘኍልቍ 31፥16ይሁዳ 1፥11ን ይመልከቱ)። በሌሎች ግፊት ቢኖርም ለጌታ ታማኝ ሆናችሁ ለመቆየት እንዴት እንደምትችሉ አሰላስሉ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘኍልቍ 11:4–10

እግዚአብሔር ለሰጠኝ ነገር አመስጋኝ መሆን እችላለሁ።

  • ጌታ እስራኤላውያንን ለመርዳት ያደረጋቸውን አንዳንድ ተአምራት ያስታውሱ እንደሆን ልጆቻችሁን ጠይቋቸው (“የግብፅ መቅሰፍት” እና “ፋሲካ” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 67–74 ይመልከቱ)። ከዚያም እስራኤላውያን በረከቶቻቸውን እንደረሱና እያጉረመረሙ እንደነበር አጽንዖት በመስጠት ዘኍልቍ 11:4-10ን ጠቅለል ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ። አንዳንድ ጊዜ ምን በረከቶችን እንረሳለን?

  • ስለ ምስጋና እንደ “Count Your Blessings” (መዝሙር፣ ቁጥር 241) ያለ መዝሙር ስትዘምሩ ወይም ስታዳምጡ ልጆቻችሁ ጌታ ስለሰጣቸው በረከቶች ስዕል መሳል ይችላሉ።

ዘኁልቁ 12

ጌታ ነቢዩን እንድከተል ይፈልጋል።

  • ዘኍልቍ 12ን ለማስተዋወቅ፣ ጌታ የሙሴ ወንድም እና እህት በሆኑት በአሮን እና በማርያም ደስተኛ እንዳልነበረ ለልጆቻችሁ መንገር ትችላላችሁ። ለምን እንደሆነ እንዲያውቁ ዘኍልቍ 12፡1–8ን እንዲያነቡ ጋብዟቸው። ልጆቻችሁ የጌታን ነቢይ የሚያከብሩ እና የተባረኩ ሰዎችን ምሳሌ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንዲያገኙ ለመርዳት የወንጌል አርት መጽሐፍን ለመጠቀም አስቡ። የጌታን ነቢይ ስንከተል እንዴት እንባረካለን?

ዘኍልቍ 21:6–9

ኢየሱስ ክርስቶስን መመልከት እችላለሁ።

  • ዘኁልቁ 21፡6–9 ውስጥ የሆነውን ነገር ልጆቻችሁ እንዲያውቁ ለመርዳት በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 83–84 ላይ “ሙሴ እና የናሱን እባብ” መጠቀም ትችላላችሁ። የናሱ እባብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይመስላል? (ዮሐንስ 3፡14–15 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ እባብን ከወረቀት በመሥራት እና በላዩ ላይ “በእምነት… የእግዚአብሔርን ልጅ [ለመመልከት]” ማድረግ የሚችሏቸውን አንዳንድ ቀላል ነገሮችን መጻፍ ሊያስደስታቸው ይችላል።(ሄለማን 8:15)

    1:2

    Moses and the Brass Serpent

  • ትልልቅ ልጆች ከሚከተሉት ምዕራፎች ውስጥ አንዱን መምረጥ እና ለታሪኩ የሚጨምርላቸውን መረዳት ማካፈል ይችላሉ፡ 1 ኔፊ 17፡41አልማ 33፡18–20ሔለማን 8፡13–15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፡36

የናሱ እባብ

የናሱ እባብ፣ በብሬንት ኢቫንስ

ዘኍልቍ 22–24

ሌሎች እንዳላደርገው ሊያሳምኑኝ ቢሞክሩም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል እችላለሁ።

  • ለልጆቻችሁ በለዓም ምንም እንኳን የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ክብርና ሀብት ቢያቀርብለትም የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንዴት ከመራገም እንደተቆጠበ ትኩረት በመስጠት ዘኍልቍ 22፡1-18ን ጠቅለል አድርጉ። ከዚያም ልጆቻችሁ በለዓም እግዚአብሔርን ለመከተል እንደፈለገ የሚያሳዩ ሐረጎችን በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ እንዲፈልጉ መርዳት ትችላላችሁ: ዘኍልቍ 22:1823:2624:13። ልጆቻችሁ ለጌታ መታዘዝን እንዲያስታውሱ ለመርዳት የሚወዱትን አንድ ሀረግ መርጠው በካርድ ላይ ይፃፉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ኢየሱስን በመስቀል ላይ፣ የናሱን እባብ፣ ኢየሱስ ጴጥሮስን በውሃ ላይ እንዲራመድ ሲረዳው እና የሌሂን ራዕይ የሚያሳይ ምስል አዘግጁ።

ከላይ በተግራ፡ የክርስቶስ ስቅለት። ከላይ በስተቀኝ፡- ሙሴ እና የናሱ እባብ፣ በጁዲት መህር። ከታች በስተግራ፡ የእምነት ፈጻሚ ፣ በኬልሲ እና ጀሲ ላይትዌቭ ከታች በስተቀኝ፡ የሌሂ ህልም፣ በጄሪ ቶምፕሰን

የልጆች የአክቲቪት ገጽ፡ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መመልከት እችላለሁ