“ግንቦት 11–17 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ”: ዘዳግም 6–8፤ 15፤ 18፤ 29–30፤ 34 ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
“ግንቦት 11–17 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ’” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ሙሴ በናባው ተራራ ላይ፣ በጆን ስቲል © Providence Collection/licensed from goodsalt.com
ግንቦት 11–17 (እ.አ.አ)፡ “እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ”
ዝዳግም 6–8፤ 15፤ 18፤ 29–30፤ 34
የሙሴ ምድራዊ አገልግሎት የጀመረው በተራራ ላይ እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል በተናገርው ጊዜ ነበር (ዘጸአት 3፥1–10ን ይመልከቱ)። የተጠናቀቀውም ከ40 አመታት በኋላ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ በናባው ተራራ አናት ላይ የቃል ኪዳኗን ምድር በጨረፍታ ባሳየው ጊዜ በተራራ ላይ ነበር (ዘዳግም 34፥1–4)። ሙሴ የእስራኤል ልጆች ወደዚያ የቃል ኪዳን ምድር እንዲገቡ በማዘጋጀት የህይወቱን ጊዜ አሳልፏል፣ እንዲሁም ኦሪት ዘዳግም የመጨረሻ መመሪያዎቹን፣ ማስታወሻዎቹን፣ ማሳሰቢያዎቹን፣ እና ለእስራኤላዊያን ተማጽኖዎቹን ይዘግባል። የእርሱን ቃላት ማንበብ የሙሴ አገልግሎት ትክክለኛ አላማ በምድረበዳ ስለመትረፍ፣ ጠላቶችን ድል ስለማድረግ፣ ወይም ሃገርን ስለመገንባት አልነበረም—ህዝቡ ያስፈልገው የነበርውን ዝግጅት እንዲያደርግ ነበር። እግዚአብሔርን ስለመውደድ፣ ለእርሱ ስለመታዘዝ፣ እና ለእርሱ ታማኝ ሆኖ ለመቆየት ስለመማር ነበር። ወደ ዘለአለማዊ ህይወት የቃል ኪዳን ምድር ለመግባት ሁላችንም የሚያስፈልገን ዝግጅት ይህ ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን ሙሴ እግሩ “ወተትና ማር [የ]ምታፈስሰው[ን] አገር” (ዘጸአት 3፥8) በፍጹም ባይረግጥም፣ በእምነቱ እና በታማኝነቱ ምክንያት፣ እግዚአብሔር ለሚከተሉት ሁሉ ወዳዘጋጀው የቃል ኪዳን ምድር ገብቷል።
ስለ ኦሪት ዘዳግም አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘዳግም” የሚለውን ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዘዳግም 6፥4–7፤ 8፥2–5፣ 11–17፤ 29፥18–20፤ 30፥6–10፣ 14–20
“አምላክህን እግዚአብሄርን በፍጹም ልብህ … ውደድ።”
የሙሴ ሕግ ብዙ ውጫዊ አከባበሮችን እና ሥርዓቶችን ያካትታል። በዘዳግም ውስጥ በሙሴ ምክር እንደምታዩት፣ ጌታ የህዝቡ ውስጣዊ ሁኔታ—ስለልባቸው መንፈሳዊ ሁኔታም አሳስቦት ነበር።
ከታች ባሉት ጥቅሶች ውስጥ፣ ልብ የሚለውን ቃል በመፈለግ ምንን ሊያመለክት እንደሚችል አስቡ። እነዚህን ዘገባዎች በልባችሁ ላይ መንፈሳዊ ምርመራ እንደማድረግ ልታስቧቸው ትችላላችሁ። ለራሳችሁ ምን ዓይነት የምርመራ ውጤት ትሰጣላችሁ? የልባችሁን መንፈሳዊ ጤንነት ለማሻሻል ምን ዓይነት ሕክምናዎችን ታዛላችሁ? የሚሰማችሁን ጻፉ፡
-
ዘዳግም 6፥4–7፦
-
ዘዳግም 8፥2–5፦
-
ዘዳግም 8፥11–17፦
-
ዘዳግም 29፥18–20፦
-
ዘዳግም 30፥6–10፦
-
ዘዳግም 30፥14–20፦
ሃሳባችሁን የምታደራጁበት አንዱ መንገድ ልብን በመሳል ጌታ በልባችሁ ውስጥ ሊኖር ይገባል ያለውን ነገር በመፃፍ ሊሆን ይችላል። ከዚያም ከልባችሁ ማራቅ ያለባችሁን ነገር ከልቡ ውጪ መጻፍ ትችላላችሁ።
እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ እንደምትወዱት እንዴት ታሳያላችሁ? ሃሳቦችን ለማግኘት፣ “Love God, love your neighbor፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣10–12 ተመልከቱ።
በተጨማሪም ኤም. ረስል ባላርድ፣ “Lovest Thou Me More Than These?,” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ) 51-53 ን ይመልከቱ።
የራሳችሁን መንፈሳዊ ግንዛቤ ፈልጉ። ኑ፣ ተከተሉኝ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ማተኮር ስላለባችሁ ምንባቦች እና መርሆዎች ይጠቁማል፣ ነገር ግን ያ የእናንተን ጥናት እንዲገድብ አታድርጉ። ኦሪት ዘዳግምን ስታነቡ እዚህ ላይ ጎልቶ ያልወጣን መርሆ ልታገኙ ትችላላችሁ። መማር ወዳሚያስፈልጋችሁ ነገሮች መንፈስ ቅዱስ እንዲመራችሁ አድርጉ።
ዘዳግም 6፥4–12፣ 20–25
“እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።”
ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር የሚገቡ አብዛኛዎቹ እስራኤላውያን በግብጽ ቸነፈርን አላዩም ወይም ቀይ ባህርን አላቋረጡም። እነሱ—እንዲሁም የወደፊት ትውልዶች—የእግዚአብሔር ህዝቦች ሆነው መቀጠል ካለባቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት እና የእግዚአብሔርን ህግጋት ማስታወስ እንድሚያስፈልጋቸው ሙሴ ያውቅ ነበር።
በዘዳግም 6፥4–12፣ 20–25 ውስጥ ከሚገኙት ምክሮች ውስጥ እግዚአብሔር ስላደረገላችሁ ታላቅ ነገር ማስታወስ እንድትችሉ የሚረዳችሁ የትኛው ነው? የጌታ ቃል ዘወትር “በል[ባችሁ]” እንዲሆን ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል? (ቁጥር 6)።
እንዲሁም የወንድም ጃን ኢ ኒውማንን “Preserving the Voice of the Covenant People in the Rising Generation” (ሊያሆና፣ ህዳር 2023፣ 36–38) የተሰኘውን መልእክት በማጥናት በክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት ለትውልድ እንዴት እንደምታስተላልፉ አስቡ።
በተጨማሪም ዘዳግም 11፡18–21፤ ዴል ጂ. ሬንለንድ፣ “Consider the Goodness and Greatness of God,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 41–44፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “Frontlets or phylacteries.” ተመልከቱ።
ዘዳግም 15፥1–15
የተቸገሩትን መርዳት ለጋሽ እጆችን እና ፍቃደኛ ልብን ይጠይቃል።
“በመካከ[ላችን] ድሀ [የማይገኝበትን]” ቀን ገና አልደረስንም (ዘዳግም 15፡4)፣ ሆኖም ምንም እንኳን ልዩ ልምዶች ቢቀየሩም በዘዳግም 15 ላይ ድሆችን ስለመርዳት ያሉት መመሪያዎች አሁንም ጠቃሚ ናቸው። ከቁጥር 1–15 ውስጥ የተቸገሩ ሰዎችን ለምን እንደምንረዳ እና ስለዚህም ያለን አመለካከት ምን መሆን እንዳለበት ምን እንደሚያስተምር ተመልከቱ።
ለተቸገሩ ሰዎች “እጅህን … ክፈት” ሲባል ምን ማለት ነው? (ቁጥር 8፣ 11)። የተቸገሩ ሰዎችን ስለመርዳት ከጌታ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ? (ቁጥር 15 ይመልከቱ)።
“Have I Done Any Good?,” መዝሙሮች፣ ቁጥር 223 ይመልከቱ።
ዘዳግም 18፥15–19
ሙሴ “[እንደ]” ኢየሱስ ነበር።
በዘዳግም 18፥15–19 ውስጥ ስላለው ትንቢት ጴጥሮስ፣ ኔፊ፣ ሞሮኒ፣ እና አዳኝም ሃሳብ ሰጥተው ነበር (የሐዋርያት ስራ 3፥20–23፤ 1 ኔፊ 22፥20–21፤ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥40፤ 3 ኔፊ 20፥23ን ይመልከቱ)። ስለአዳኙ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ትማራላችሁ? ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ስለ ሙሴ ያነበባችሁትን አስቡ። ሙሴ “[እንደ]” ኢየሱስ የነበረው እንዴት ነበር?
ኢየሱስ ክርስቶስ የጥንቷ አሜሪካ ህዝቡን ነቢዩ “ሙሴ የተናገረለት እኔ ነኝ” (3 ኔፊ 20፡23) ሲል ተናግሯል።
ዘዳግም 29፥9፤ 30፥15–20
ጌታ መልካምን ከክፉ እንድመርጥ ይጋብዘኛል።
በዘዳግም 29፡9፤ 30፡15–20 ውስጥ የሚገኘውን የሙሴን ቃላት ከአንዳንድ ሌሂ ለቤተሰቡ በ2 ኔፊ 2፡26–29፤ 4፡4 ላይ ካስተማራቸው የመጨረሻ ትምህርቶቹ ጋር ማነጻጸር ትኩረት የሚስብ ሊሆን ይችላል። ሙሴ ያስተማረውን ሌሂ እንዴት አብራራ? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ “ህይወትን [እንድትመርጡ]” የሚያነሳሷችሁን ምን ታገኛላችሁ? (ዘዳግም 30፥19)።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘዳግም 6፥5።
እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ መውደድ እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁ ዘዳግም 6:5ን እንዲረዱ ለመርዳት ልብን፣ የሰውነት ቅርጽንና ጠንካራ ክንድ መሳል ትችላላችሁ። እናንተ “ልብ”፣ “ነፍስ” እና “ኃይል” የሚሉ ቃላትን ከጥቅሱ ውስጥ ስታነቡ ልጆቻችሁ ወደ ሥዕሎቹ ሊጠቁሙ ይችላሉ። ጌታን በፍጹም ልባችን፣ ነፍሳችን እና ኃይላችን እንደምንወደው እንዴት እናሳየዋለን?
ዘዳግም 6:6–15
የእግዚአብሄርን ቃል በልቤ ማኖር እችላለሁ።
-
የቅዱሳት መጻሕፍት ጥቅሶችን በየቀኑ የሚያዩዋቸው ቦታ እንዲያደርጉ ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጠውን ምክር ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ (ዘዳግም 6፡6–9 ይመልከቱ)። ይህ እናንተ እና ልጆቻችሁ “እግዚአብሄርን እንዳት[ረሱ]” (ቁጥር 12) እና ያደረገላችሁን እንድታስታውሱ መንገዶችን እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል።
-
ዘዳግም 6፡13፣ 16 እና 8፡3 አዳኙ በህይወቱ በአንድ አስፈላጊ ጊዜ ውስጥ ረድቶት እንደነበረ ልትጠቁሙ ትችላላችሁ። እንዴት እንደሆነ ለማየት ማቴዎስ 4፡1–10ን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም በችግር ጊዜ የረዷችሁን አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አንዳችሁ ለሌላው ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
ዘዳግም 18:15–18
ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምሩናል።
-
ዘዳግም 18፡18ን አብራችሁ ስታነቡ ልጆቻችሁ በዚህ ጥቅስ ላይ እንደ ሙሴ ያለው ነቢይ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ሙሴ ያደረጋቸውን ነገሮች እና ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸውን ነገሮች ሥዕሎች በመመልከት ልጆቻችሁ እንዲያዛምዷቸው አድርጉ (የወንጌል አርት መጽሐፍ፣ ቁጥር 15፣ 16፣ 38፣ 39 ተመልከቱ)። ዛሬ ላይ ነቢያችን ስለ አዳኙ ምን አስተምረውናል?
ዘዳግም 29:12–13፤ 30:8–10
በቃል ኪዳኖቼ ምክንያት፣ እኔ የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል ነኝ።
-
ስለ ዘዳግም 29:12–13 መነጋገር ቤተሰባችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ለሚያደርጉት ወይም ስላደረጉት ቃል ኪዳኖች እንዲወያዩ እድል ይሰጣል። የእግዚአብሔር ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? የገባነው ቃል ኪዳን የእግዚአብሔር ሰዎች የሚያደርገን እንዴት ነው? (ቁጥር 13ን እንዲሁም ሞዛያ 18፡8–10 ተመልከቱ)።
-
ልጆቻችሁ ቃል ኪዳን ምን እንደሆነ ለመረዳት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ በቅዱሳን መጽሃፍቶች መመሪያ (የወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ “ቃል ኪዳን” ላይ ትርጉም እንዲያገኙ ጠቁሙ። በዘዳግም 30፡8-10 ውስጥ እግዚአብሔር እና እስራኤላውያን ቃል የገቡት ምን ነበር ? ከእግዚአብሔር ጋር ምን ቃል ገብተናል? ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:37፣ 77)ይመልከቱ)። እነዚህ ተስፋዎች እኛን ከእርሱ ጋር እንዴት ያገናኙናል? እንደ “Standing on the Promises” (የወንጌል ላይብረሪ) ያለ የቃል ኪዳን መዝሙር አንድ ላይ ለመዘመር አስቡ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።