“ልስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች
ከኢያሱ መጽሐፍ አንስቶ እስከ አስቴር በተለምዶ የብሉይ ኪዳን “ታሪካዊ መጽሐፎች” ተብለው ይጠራሉ። ይህ ግን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሌሎች መጽሐፎች ታሪካዊ ዋጋ የላቸውም ማለት አይደለም። በምትኩ፣ ታሪካዊ መጽሐፎች ተብለው የተጠሩት የፀሀፊዎቻቸው ዋነኛ አላማ በእስራኤል ህዝብ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን እጅ ማሳየት ስለነበረ ነው። አላማው ዘሌዋውያን እና ዘዳግም እንደሚያደርጉት የሙሴን ህግ መዘርዘር አይደለም። መዝሙረ ዳዊት እና ሰቆቃው ኤርምያስ እንደሚያደርጉት ምስጋናን ወይም በግጥም መልኩ ለቅሶን ለመግለፅ አልነበረም። የኢሳይያስ እና የሕዝቅኤል መጽሐፎች እንደሚያደርጉት የነብያትን ቃላት መመዝገብም አይደለም። ይልቁንም ታሪካዊ መጽሐፎቹ ታሪክን ይናገራሉ።
የእይታ ጉዳይ
እንደሚጠበቀው፣ እነዚያ ታሪኮች የተነገሩት ከሆነ እይታ አንፃር ነው። አበባን፣ ድንጋይን ወይም ዛፍን በአንድ ጊዜ ከአንድ አቅጣጫ በላይ ማየት እንደማይቻል ሁሉ፣ የታሪክ መዝገብ የፀሃፊውን ሰው ወይም የሰዎቸ ስብስብ እይታ ማንፀባረቁ የማይቀር ነው። ይህ እይታ የፀሃፊውን አገር ወይም የጎሳ ትስስር እንዲሁም ባህላዊ እሴቶች እና እምነቶች ያካትታል። ይህን ማወቅ የታሪካዊ መጽሐፎች ፀሃፊዎች እና ሰብሳቢዎች በተወሰኑ ዝርዝሮች ላይ እንዳተኮሩ ሌላዎቹን ደግሞ እንደቀነሱ እንድንገነዘብ ሊረዳን ይችላል። ሌሎች የማይኖራቸው አይነት ግምቶች ነበሯቸው። በእነዚያም ዝርዝሮች እና ግምቶች ላይ በመመስረት ወደ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ መጽሐፎች መካከል (አንዳንድ ጊዜም በአንድ መጽሐፍ ውስጥ) የተለያዩ እይታዎችን መመልከት እንችላለን። እነዚህን እይታዎች ከግምት ስናስገባ ታሪካዊ መጽሃፎችን ይበልጥ መረዳት እንችላለን።
ለሁሉም የብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎች የጋራ የሆነው አንዱ እይታ የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች የሆኑት የእስራኤል ልጆች እይታ ነው። በእግዚአብሔር ያላቸው እምነት በሕይወታቸው እንዲሁም በህዝባቸው ጉዳዮች የእርሱን እጅ እንዲያዩ ረድቷቸዋል። ዓለማዊ የታሪክ መጽሐፎች ነገሮችን በዚህ መልኩ የማየት ዝንባሌ ባይኖራቸውም ይህ መንፈሳዊ አመለካከት እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ለመገንባት ለሚሹ ሰዎች የብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎችን በጣም ጠቃሚ የሚያደርግ አካል ነው።
አውድ ለተቀረው ብሉይ ኪዳን
ታሪካዊ መጽሐፎቹ የዘዳግም መጽሐፍ መጨረሻ ላይ እና የእስራኤላውያን የብዙ ዓመታት የምድረበዳ ውስጥ መንከራተት ሊያበቃ ሲል ይጀምራሉ። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ የእስራኤል ልጆች ወደቃልኪዳን ምድራቸው ወደ ከነዓን ሊገቡ ተዘጋጅተው ያሳያል እንዲሁም እንዴት እንዳከናወኑት ይገልፃል። ቀጥለው የተከተሉት መጽሐፎች፣ ከመሣፍንት አንስቶ እስከ 2ኛ ዜና መዋዕል፣ በቃልኪዳን ምድር ውስጥ ከሰፈሩበት ጊዜ አንስቶ በአሦር እና በባቢሎን እስከተማረኩበት ጊዜ ድረስ እስራኤል ያሳለፈችውን ይገልፃሉ። የዕዝራ እና ነህምያ መጽሐፎች ከአስርተ ዓመታት በኋላ ብዙ እስራኤላውያን ቡድኖች ዋና ከተማቸው ወደሆነችው ኢየሩሳሌም መመለሳቸው ይናገራሉ። በመጨረሻም መጽሐፈ አስቴር በፋርስ ግዛት ስር ይኖሩ ስለነበሩት እስራኤላውያን ታሪክ ይገልፃል።
እዚያ ላይ ነው የብሉይ ኪዳን የታሪክ ቅደም ተከተል የሚያቆመው። የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ጊዜ አንባቢዎች ከግማሽ በላይ የብሉይ ኪዳንን ገፆች አንብበው ሳይጨርሱ የብሉይ ኪዳንን ታሪክ አንብበው በመጨረሳቸው ይገረማሉ። ከ አስቴር፣ በኋላ ስለእስራኤላውያን ታሪክ ብዙ መረጃዎችን አናገኝም። በምትኩ፣ የሚከተሉት መጽሐፎች—በተለይ የነብያት መጽሐፎች—ታሪካዊ መጽሐፎቹ በቀረቡበት የጊዜ መስመር ውስጥ ይገኛሉ። ለምሳሌ፣ የነብዩ ኤርምያስ አገልግሎት የ 2ኛ ነገሥት 22–25 (በ 2ኛ ዜና መዋዕል 34–36ውስጥ ያለውም ተመሳሳዩ ዘገባ) ክስተቶች በተመዘገቡበት ወቅት ተከናውኗል። ይህን ማወቅ የታሪካዊ ትረካዎችን እና የትንቢት መጽሐፎችን በሚያነቡበት መንገድ ላይ ተፅዕኖ ሊያደርግ ይችላል።
የሆነ ነገር መግጠም ሳይችል ሲቀር
ልክ እንደማንኛውም ታሪክ ብሉይ ኪዳንን ሲያነቡ፣ ለዘመናዊ ዓይኖች ባዕድ ወይም የሚረብሽ የሚመስሉ ነገሮችን ሰዎች ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ ሊያነቡ ይችላሉ። ይህን መጠበቅ ይኖርብናል—የብሉይ ኪዳን ፀሐፊዎች ዓለምን በተወሰነ መልኩ ከእኛ በሚለይ እይታ ተመለከቱ። አመፅ፣ ጎሳዊ ግንኙነቶች እና የሴቶች ሚና የጥንት ፀሐፊዎች ከእኛ በተለየ መልኩ ከተመለከቷቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው።
ስለዚህ በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ የሚረብሹ የሚመስሉ ምንባቦች ሲያጋጥሙን ምን ማድረግ አለብን? መጀመሪያ፣ እያንዳንዱን ምንባብ በሰፊ አውድ ማሰብ ሊረዳ ይችላል። በእግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ ውስጥ እንዴት ይገጥማል? ስለሰማይ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጥሮ ከሚያውቁት ጋር እንዴት ይገጥማል? በሌላ ቅዱሳን መጽሐፍት ወይም በሕያው ነብያት ትምህርቶች ውስጥ ከተገለፁ እውነታዎች ጋር እንዴት ይገጥማል? እንዲሁም ለልቦት እና ለአዕምሮዎት ሹክሹክታ ከሚያሰማው መንፈስ ጋር እንዴት ይገጥማል?
በተወሰነ መልኩ ምንባቡ ከእነዚህ ጋር በደንብ የሚገጥም ላይመስል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ምንባቡ ካገጣጠሙት የቁርጥራጭ እንቆቅልሾች ጋር የሚገጥም የማይመስል ልክ እንደ አንድ የእንቆቅልሽ ቁራጭ ሊሆን ይችላል። ቁራጩ የግድ እንዲገጥም መሞከር የተሻለ አቀራረብ አይደለም። ነገር ግን በመላ እንቆቅልሹ ላይ ተስፋ መቁረጥም የተሻለ አይደለም። በምትኩ ቁራጩን ለጊዜው ወደ ጎን መተው ሊኖርባችሁ ይችላል። የበለጠ ሲማሩ እና ብዙ እንቆቅልሾችን አገጣጥመው ሲጨርሱ፣ ቁራጩ እንዴት እንደሚገጥም የበለጠ ለማየት ይችሉ ይሆናል።
በሆነ እይታ ከመወሰኑም በተጨማሪ የቅዱሳን መጽሐፍት ታሪኮች ለሰው ስህተት የተጋለጡ መሆናቸውን ማስታወስ ሊረዳም ይችላል። ለምሳሌ፣ በብዙ ክፍለ ዘመናት ሂደት ውስጥ የትምህርት እና የስርዓቶች ጠቃሚ እውነታዎችን ጨምሮ “ብዙ ግልፅ እና ውድ ነገሮች [ከመጽሐፍ ቅዱስ] ተወስደው [ነበር]” (1ኛ ኔፊ 13፥28፤ እንዲሁም ቁጥር 26፣29፣40ይመልከቱ)። በተመሳሳይ መልኩ የገዛ አመለካከቶቻችን ውስን መሆናቸውን አምነን ለመቀበል ፍቃደኞች መሆን አለብን፦ ሙሉ በሙሉ የማንረዳቸው ነገሮች እና መመለስ የማንችላቸው ጥያቄዎች ሁሌም ይኖራሉ።
አንዳንድ የቅዱስ ጽሁፍ ምንባቦች ከቀረው የሚገጣጠም እንቆቅልሽ ጋር እንዴት እንደሚገጥም እንደማናውቀው የእንቆቅልሽ ቁራጭ አይነት ሊሆኑ ይችላሉ።
ዕንቁዎችን ማግኘት
አንዳንድ ጊዜ እነዚያ ዕንቁዎች በሚረብሹ ልምዶች እና ፍፁም ባልሆኑ ሰዎች በሚደረጉ ደካማ ምርጫዎች ድንጋያማ ምድር ውስጥ የተደበቁ ቢሆኑም እንኳን ለአሁን፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙት ከውዶቹ የዘላለም እውነት ዕንቁዎች ሊያቆሙን አይገባም። ምናልባት ከእነዚህ ዕንቁዎች መካከል የበለጠ ውዶቹ ስለእግዚአብሔር ፍቅር የሚመሰክሩት ታሪኮች እና ምንባቦች ናቸው—በተለይ አዕምሯችንን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት የሚጠቁሙት። ከማንኛውም ማዕዘን ቢመለከቷቸው፣ እንደነዚህ ዓይነት ዕንቁዎች ልክ እንደ ከዚህ ቀደም ዛሬም ድረስ በብሩህ ያንፀባርቃሉ። እናም እነዚህ ዘገባዎች ስለእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች በመናገራቸው ምክንያት—እነሱም የሰው ድክመቶች ያሉባቸው ወንዶች እና ሴቶች ቢሆኑም እግዚአብሔርን ስለወደዱ እና ስላገለገሉ—የእውነታ ዕንቁዎች በብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎች ውስጥ ተትረፈረፉ።