ኑ፣ ተከተሉኝ
ሰኔ 1–7 (እ.አ.አ) “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና”: ሩት፤ 1 ሳሙኤል 1-7


“ሰኔ 1–7 (እ.አ.አ) ‘ልቤ በእግዚአብሔር ጸና”: ሩት 1፤ 1 ሳሙኤል 1–7 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)(2026)

“ሰኔ 1–7 (እ.አ.አ) ‘ልቤ በእግዚአብሔር ጸና’” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ሩት እና ኑኃሚን አንድ ላይ እየተጓዙ

በምትሄጂበት፣ በሳንዲ ፍሬክልተን ጋጎን

ሰኔ 1–7 (እ.አ.አ)፡ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና”

ሩት1 ሳሙኤል 1–7

አንዳንዴ ህይወታችን ከጅማሪው እስከ ፍጻሜው ግልጽ የሆነን መንገድን ይከተላል ብለን እናስባለን። ሆኖም፣ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው አጭሩ እርቀት ቀጥተኛ መስመር ነው። ህይወትም በአብዛኛው ባልጠበቅነው መንገዶች በሚወስዱን እና በመዘግየትና በልዋጭ መንገዶች የተሞላች ነች።

ሩት እና ሐና ይህን በእርግጥም ተረድተው ነበር። ሩት እስራኤላዊት አልነበረችም፣ ነገር ግን ያገባችው ሰው ነበረ፣ ባለቤትዋ ሲሞት፣ ምርጫ ማድረግ ነበረባት። ወደቤተሰቧ እና ወደቀድሞው፣ የተለመደው ህይወት ትመለስ ይሆን፣ ወይስ የእስራኤላዊ እምነትን በመቀበል ከምራቷ ጋር በአዲሱ ቤት ውስጥ ትቀጥል ይሆን? (ሩት 1፥4–18ን ይመልከቱ)። ሐና ለህይወቷ የነበራት እቅድ ልጆች መውለድ ነበር፣ ያንን ማድረግ አለመቻሏ “በልብዋ ትማረር” ነበር ( 1 ሳሙኤል 1፥1–10ን ይመልከቱ)። ስለ ሩት እና ሐና ስታነቡ፣ ህይወታቸውን ባልተጠበቁት መንገዶቻቸው ለመጓዝ የነበራቸውን እምነት አስቡ። ከዚያም ስለራሳችሁ ጉዞ አስቡ። ከሩት እና ሐና—እንዲሁም ከሌሎች—የተለየ ነው። ነገር ግን ከዚህ እና የዘለአለማዊ መድረሻችሁ ባሉት ፈተናዎች እና ግርምታዎች መካከል ሁሉ፣ እንደ ሐና “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና” ማለትን ልትማሩ ትችላላችሁ (1 ሳሙኤል 2፥1)።

ስለ ሩት እና 1 ሳሙኤል መጽሐፍቶች አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሩት

ክርስቶስ ሀዘንን ወደ ድል ደስታ መቀየር ይችላል።

ለመበለት ህይወት በየትኛውም ዘመን ከባድ ነው። ነገር ግን ሩት ባሏ ሲሞትባት ሁኔታዋ በተለይ ከባድ ነበር። በዚያ ጊዜ በነበረው በእስራኤላዊያን ባህል ፣ ባል ወይም ወንድ ልጆች የሌላት ሴት ለንብረት እንዲሁም ምንም አይነት ገቢ ለማግኘት መብት አይኖራትም። የሩትን ታሪክ ስታነቡ፣ ጌታ ሃዘንን ወደ ታላቅ በረከት እንዴት እንደቀየረ አስተውሉ። ሩትን ረድቷት ሊሆን ስለሚችል ነገር ምን ታስተውላላችሁ? ቦዔዝ ሩትን ከአጣዳፊ ሁኔታዋ እንዴት ዋጃት? ( ሩት 4፥4-10ን ይመልከቱ)። ሩት እና ቦዔዝ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሆኑት እንዴት ነው?

Be Still, My Soul,” መዝሙሮች፣ ቁ. 124 ይመልከቱ።

ሩት1 ሳሙኤል 1

ሁኔታዬ ምንም ቢሆን እግዚአብሔር እንደሚመራኝ እና እንደሚረዳኝ ማመን እችላለሁ።

ምናልባትም እንደ ሩት እና ኑኃሚን፣ ታላቅ እጦት አጋጥሟችሁ ይሆናል (ሩት 1፥1–5ን ይመልከቱ)። ወይም፣ እንደ ሐና፣ ገና ያልተቀበላችሁትን በረከቶች እየጠበቃችሁ ይሆናል (1 ሳሙኤል 1፥ 1–10ን ይመልከቱ)። እነዚህ ሴቶች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዴት አሳዩ? ከእነሱ ምሳሌነት ምን ትማራላችሁ?

እርግጥ ነው፣ ስለ ልጅ የሚጸልይ ሁሉ ልጅ አያገኝም፣ የትዳር አጋሩ የሞተበትም ሁሉ ደግሞ አያገባም። ነገር ግን ወደ አዳኙ የሚመለስ ሁሉ የእርሱን እርዳታ እና መመሪያ ይቀበላል። በአስቸጋሪ ጊዜ በጌታ እንዴት “መጠጊያ [እንዳገኛችሁ]” (ሩት 2፥12) አስቡ።

እንዲሁም ኤሚ ኤ. ራይትን፣ “Abide the Day in Christ,”፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 9–11 ይመልከቱ።

ሃና እና ልጇ

ለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፣፣ በኤልስፒት ያንግ

1 ሳሟኤል 24–7

የጌታን እርዳታ ለመቀበል፣ እሱን ማመን እና ትእዛዙን መጠበቅ አለብኝ።

እስራኤላውያን ጠላቶቻቸው ጥቃት በሰነዘሩባቸው ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት መያዛቸው ብቻ ጥበቃ የሚያስገኝላቸው መስሏቸው ነበር። 1 ሳሙኤል 4–6ን በምታነቡበት ጊዜ ያ ለምን እንዳልሆነ አስቡ። (በተጨማሪም በ1ሳሙኤል 2፡12–25 ላይ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ ካህን ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የዔሊ ልጆች የፈጸሙትን ክፋት አስተውሉ፣ ።) ጌታ ህዝቡን ለማስተማር የሞከረው ምን ይመስላችኋል? ፍልስጤማውያን ታቦቱን ከማረኩ በኋላ ካጋጠማቸው ነገር ምን ትማራላችሁ? (ምዕራፍ 5-6 ይመልከቱ)። በ1 ሳሙኤል 7 ላይ የጌታን ጥበቃ ዳግም ለማግኘት እስራኤል ካደረገገው ጥረት ምን ትማራላችሁ?

1ሳሙኤል 2፡1–10 ላይ የሃናን የውዳሴ ግጥም በማንበብ ልትነሳሱ ትችላላችሁ። የዔሊ ልጆችንና የተቀሩትን እስራኤላውያንን ሊረዳቸው ይችል የነበረውን ከንግግሯ ምን ታገኛላችሁ?

1 ሳሙኤል 3

የሴሚናሪ ምልክት
የጌታን ድምጽ ልሰማ እና ልታዘዝ እችላለሁ።

አንዳንድ ጊዜ፣ እንደ ሳሙኤል የጌታን ድምፅ እንደ ሰማችሁ ነገር ግን ሳታውቁት እንደቀራችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ልክ እንደ ሁላችን፣ ሳሙኤል የጌታን ድምጽ እንዴት ማወቅ እንደሚችል መማር ነበረበት። 1 ሳሙኤል 3ን ስታነቡ፣ ከዚህ ወጣት ልጅ የጌታን ድምጽ ስለመስማት እና መታዘዝ ምን ትማራላችሁ? እንዲሁም እነዚህን ተጨማሪ ጥቅሶች መፈለግ እና አንድ ሰው የጌታን ድምጽ እንዲያውቅ የሚረዱ መመሪያዎችን መዘርዘር ትችላላችሁ፡ 1 ነገሥት 19፡11–12ሉቃስ 24:15-323 ኔፊ 11፡3–7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፡22–238:2–39፡7–9

ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማያት እንደተዘጉ እና እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር መገናኘት እንደማይፈልግ ሆኖ ሊሰማችሁ ይችላል። ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “እግዚአብሔር በእውነቱ እናንተን ሊናገራችሁ ይፈልጋል? አዎን!” (ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያን፣ ራዕይ ለሕይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93–96።) የፕሬዘዳንት ኔልሰንን መልእክት ስታጠኑ፣ የጌታን ድምጽ እንድትሰሙ እና እንድትታዘዙ የሚያነሳሳችሁን ምን ታገኛላችሁ? ፕሬዘደንት ኔልሰን ምን እንድታደርጉ ጋብዘዋል፣ እንዲሁም ምን በረከቶችን ቃል ገብተዋል? በተጨማሪም ስለ ራዕይ ግብዣዎችን እና ተስፋ የተሰጡ በረከቶችን “በእግዚአብሔር ብርሃን ተመላለሱ” (ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ 16–20) በሚለው ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። “መገለጥን የመቀበል መንፈሳዊ አቅማችሁን ለመጨመር” ማድረግ የምትችሉትን አንድ ነገር ለመምረጥ አስቡ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሩት

በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች ፍቅር እና ደግነት ማሳየት እችላለሁ።

  • ለልጆቻችሁ የሩትን ታሪክ ስታካፍሉ (“ሩት እና ኑኃሚን” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች 100-103 መጠቀም ትችላላችሁ) በታሪኩ ውስጥ የደግነት ተግባር በሰሙ ቁጥር እጃቸውን እንዲያነሱ ጋብዟቸው። እንዲሁም ሌሎች መልካም ሲሆኑላቸው ወይም ለሌሎች ደግ ሲሆኑ የሚሰማቸውን ስሜት ማካፈል ይችላሉ። አዳኙ እንዴት ቸርነትን አድርጎልናል? የእርሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (“Kindness Begins with Me,የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 145 ይመልከቱ)።

    2:0

    Ruth and Naomi

ሩት1 ሳሙኤል 1

በጌታ እምነት ሊኖረኝ ይችላል።

  • የሩት እና የሃና ታሪክ ልጆቻችሁ በአስቸጋሪ ጊዜያት ታማኝ በመሆን እንዲቆዩ ሊያነሳሳቸው ይችላል። ፈተናዎችድርጊቶችበረከቶች በሚሉ ርዕሶች ቀላል ሰንጠረዥ እንዲሰሩ ለመርዳት አስቡ። ከዚያም ሩት 1:3–5፣ 8፣ 162:1–3፣ 8–124:13–171 ሳሙኤል 1፡1–18 አንድ ላይ ካነበቡ በኋላ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሚያገኙትን ከርዕሱ ስር ይጻፉ። ሩት እና ሐና በጌታ ያላቸውን እምነት ያሳዩት እንዴት ነው ? እናንተ ወይም ልጆቻችሁ ጌታ በአስቸጋሪ ጊዜያት እንዴት እንደባረካችሁ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ማካፈል ትችላላችሁ።

1 ሳሙኤል 1:1–18

የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም ይመልሳል።

  • ስለ ሐና ለመማር ልጆቻችሁ 1 ሳሙኤል 1፡1–18ን ወይም “ሐና”ን በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች (104–5) ማንበብ ወይም “Hannah’s Faith” (ቪዲዮ፣ የወንጌል ላይብረሪ) መመልከት ይችላሉ። ኳስን ወደ አንድ ልጅ መወርወር፣ ከዚያም ኳሱን ለሌላ ሰው ከማስተላለፉ በፊት የታሪኩን ክፍል እንዲናገር መጋበዝ አስደሳች ሊሆን ይችላል። ከሐና ምሳሌ ስለ ጸሎት ምን እንማራለን?

    1:15

    Hannah

    3:9

    Hannah's Faith

ሳሙኤል እና ዔሊ

ሳሙኤል ለኤሊ እውነቱን ይነግረዋል፣ በሮበርት ቲ ባሬት

1 ሳሙኤል 3:1–10

የጌታን ድምጽ መስማት እና መታዘዝ እችላለሁ።

  • ምናልባት ቀላል ትወና ልጆቻችሁ ከሳሙኤል ልምድ በመገለጥ እንዲማሩ ሊረዳቸው ይችላል። 1ሳሙኤል 3፡1–10ን በምታነቡበት ጊዜ አንድ ልጅ ሳሙኤልን፣ ሌላው ደግሞ ዔሊን መስሎ ሊተውን ይችላል (በተጨማሪም “ነቢዩ ሳሙኤል” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 106–9፣ ወይም “Samuel and Eli,” የተሰኘውን ቪዲዮ በየወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)። የጌታን ድምፅ እንዴት እንደምንሰማ ከሳሙኤል ምን እንማራለን? ጌታ ሲናገረን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናችንን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

    2:10

    Samuel the Prophet

    1:58

    Samuel and Eli

  • ልጆቻችሁ ጌታ እንዴት እንደሚናገራቸው ለአንድ ሰው እንዴት ሊያብራሩ እንደሚችሉ ጠይቋቸው። በትምህርቶች እና ቃል ኪዳኖች 6፡22–238:2–39፡7–9መልስ እንዲፈልጉ ልታግዟቸው ትችላላችሁ።

ልጆቻችሁ መንፈስን እንዲያውቁ እርዷቸው። የራሳችንን ስሜት ከመንፈስ ቅዱስ መለየት ቀላል አይደለም። ሁሉም ሰው ከጊዜ ወደ ጊዜ በዚህ ይቸገራል። ልጆቻችሁ የመንፈስ ተጽእኖ ሲሰማቸው እንዲገነዘቡ ለመርዳት ያገኛችሁትን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀሙ። ለምሳሌ፣ 1 ሳሙኤል 3፡1–10ን እና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የተጠቆሙትን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ጌታ በአእምሯችሁ እና በልባችሁ ያስተማራችሁን ልምዶች ማካፈል ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ሳሙኤል በአልጋ ላይ ከእንቅልፉ ነቅቶ

በጌታ የተጠራው ብላቴናው ሳሙኤል፣ በሃሪ አንደርሰን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም ይመልሳል