ኑ፣ ተከተሉኝ
ሰኔ 22–28 (እ.አ.አ) “ጸሎታቸውን…በሰማይ ስማ”፡ 2 ሳሙኤል 11–12፤ 1 ነገሥት 3፤ 6–9፤ 11


“ሰኔ 22–28 (እ.አ.አ) ‘ጸሎታቸውን…በሰማይ ስማ”፡ 2 ሳሙኤል 11–12፤ 1 ነገሥት 3፤ 6–9፤ 11” .ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 22–28 (እ.አ.አ) ‘ጸሎታቸውን…በሰማይ ስማ”፡ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ሰሎሞን ቤተመቅደስን እየመረቀ

ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ያለውን ቤተመቅደስ መረቀ፣ በጄምስ ቲሶት እና በሌሎች

ሰኔ 22–28 (እ.አ.አ): “ጸሎታቸውን…በሰማይ ስማ”

2 ሳሙኤል 11–121 ነገስት 36–9፤ 11

የመጀመሪያዎቹ ሦስት የእስራኤል ነገሥታት ሳኦል፣ ዳዊት እና ሰሎሞን ሁሉም የጀመሩት በብዙ ተስፋ ነበር። ቢያንስ በመጀመሪያ ትሁት፣ ደፋር እና ጥበበኞች በመሆናቸው እያንዳንዳቸው በጌታ ዘንድ ሞገስን አግኝተው ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ እያንዳንዱ ንጉስ በሰዎች ድክመቶች እና ፈተናዎች ተሸነፈ። ከጌታ ይልቅ የራሳቸውን ፍላጎት አስቀደሙ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ—እንዲሁም በራሳችን ህይወት—እንዳየነው ይህ በተደጋጋሚ ወደ አሳዛኝ ሁኔታ ይመራል።

ነገር ግን በሰሎሞን የግዛት ዘመን አንድ አስፈላጊ ነገር ተከስቷል ይህም በቃል ኪዳኑ ሕዝብ ሕይወት ውስጥ የመረጋጋትን ተስፋ የሰጠ ነበር። ሰሎሞን ቤተመቅደስን ሠራ። ከማደሪያው ድንኳን የበለጠ ቋሚ የጌታ ቤት የሚሆን ነው። እንዲሁም በህዝቡ መካከል የጌታን ቋሚ መገኘት የሚወክል ይሆናል። ሰሎሞን ሕዝቡ ድክመቶችና የተለያዩ ዓይነት ፈተናዎች እንደሚደርስባቸው ያውቅ ነበር። አዲሱን ቅዱስ ቤት ሲመርቅ “በፍጹም ልባቸው … ወደ አንተ ቢመለሱ፣ ጸሎታቸውን … ስማ” (1 ነገስት 8፡47–48) በማለት ሰሎሞን ጌታን ተማጽኗል። ያ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች የሚያደርጉልን ነገር አካል ነው—ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ይፈጥራሉ። በንስሐ እና በምሕረቱ፣ እርሱ “[በ]መካከላ[ችን] [እንደሚኖር]” እና ፈጽሞ እንደማይጥለን የገባውን ቃል ያረጋግጡልናል (1 ነገስት 6፡13)።

ስለ 1 ነገሥት መጽሐፍ አጠቃላይ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መፅሐፈ ነገስት” የሚለውን ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ሳሙኤል 1112፥1–14

የሴሚናሪ ምልክት
ኃጢአት እንድሰራ ስፈተን ጥሩ ምርጫ እንዳደርግ ጌታ ሊረዳኝ ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ በእምነታቸው የጸኑ የሚመስሉ ሰዎችን ስንመለከት ፈተና ተጽዕኖ የማያደርስባቸው አድርገን እንገምታለን። በ2 ሳሙኤል 11 ላይ የተገለጹት የዳዊት አሳዛኝ ምርጫዎች ይህ እንዳልሆነ በግልጽ ያሳያሉ። ከእርሱ ተሞክሮዎች ምን ትምህርቶች እንደምትማሩ አስቡ። እንደነዚህ ያሉት ጥያቄዎች 2 ሳሙኤል 11–12ን እንድታጠኑ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

  • ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ወደሚሄድ የኃጢያት ጎዳና የመራውን ምን ምርጫዎችን አደረገ? በምትኩ ምን ዓይነት ትክክለኛ ምርጫዎችን ማድረግ ይችል ነበር? (በተጨማሪም “To Look Upon,” የሚለውን የወንጌል ላይብረሪ ቪዲዮ ይመልከቱ።)

    4:15

    To Look Upon

    ቪዲዮዎችን መጠቀም። ቪዲዮዎች ከቅዱሳን መጽሃፍት ውስጥ የሚገኙትን ዘገባዎች በዓይነ ሕሊናችሁ እንድትታዩ እንዲሁም እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ እንድታስቡ ይረዷችኋል። ማስተማርንና መማርን ለማሻሻል እንዴት ልትጠቀሙባቸው እንደምትችሉ አስቡ። ለምሳሌ “To Look Upon” (የወንጌል ላይብረሪ) ስትመለከቱ ቪዲዮውን በተለያዩ ቦታዎች በማቆም ለማሰላሰል ወይም እዚህ በቀረቡት አንዳንድ ጥያቄዎች ላይ ለመወያየት አስቡ።

  • ጠላት በኃጢአት ጎዳና ሊመራችሁ እየሞከረ ያለው እንዴት ነው? መንፈሳዊ ደህንነትን ለመጠበቅ አሁን ምን ምርጫዎችን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ዳዊት በ2 ሳሙኤል 12፡1–6 ላይ ላለው ታሪክ ለናታን የሰጠውን ምላሽ አስተውሉ። ዳዊት የሰጠው ምላሽ ለራሱ ስላለው አመለካከት ምን ያሳያል? ራሳችሁን ይበልጥ በትክክል እንድትመለከቱ እንዲረዳችሁ ጌታ ምን አድርጓል?

  • 2 ሳሙኤል 11–12 ክስተቶችን በአንድ አረፍተ ነገር ማስጠንቀቂያ እንዴት ማጠቃለል ትችላላችሁ?

ስለ ዳዊት መጥፎ ምርጫዎች ማንበባችሁ ስለ ብልግና ምስሎች እና የዝሙት ኃጢአት አደጋዎች እንድታውቁ ይረዳችኋል። ለዚህ ጥሩ ምንጭ የሆነው ለወጣቶች ጥንካሬ፡ ምርጫ የማድረግ መመሪያ በተለይም “What to do in the moment” እና “Your body is sacred” (ገጽ 21-28) የሚሉ ክፍሎች ናቸው። ዳዊት የተሻሉ ምርጫዎችን እንዲያደርግ የሚረዳውን ምክር ለማግኘት ይህን ግብአት መመልከት ትችላላችሁ። ወይም “Jesus Christ will help you” (ገጽ 6-9) ዳዊት ወደ ጌታ እንዲመለስ ይረዳው የነበረን ነገር በመፈለግ ማንበብ ትችላላችሁ።

እንደ “I Need Thee Every Hour” (መዝሙሮች፣ ቁ. 98 ያለ መዝሙር ለመዘመር እና ፈተና ሲገጥማችሁ አዳኙ እንዴት እንዳበረታችሁ ማሰላሰል ትችላላችሁ።

እንዲሁም 2 ኔፊ 28፡20–24፤ ዩሊሲስ ሶአሬስ፣ “Seek Christ in Every Thought,” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 82–85፤ “Taking Charge of Technology,” የወንጌል ላይብረሪ “Watch Your Step” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ።

2:36

Watch Your Step

1 ነገሥት 3፥1–15

የማስተዋል ስጦታ ትክክልና ስህተት የሆነውን ለመለየት እንድችል ይረዳኛል።

ጌታ እንዲህ ቢላችሁ፣ “ምን እንድሰ[ጣችሁ] ለም[ኑ]” (1 ነገሥት 3፥5)፣ ምን ትጠይቃላችሁ? ስለ ሰሎሞን ጥያቄ ምን ያስደንቃችኋል? “መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ፣ አስተዋይ ልብ” (ቁጥር 9) ለምን አስፈላጊ ስጦታ እንደሆነ አሰላስሉ። ይህንን ስጦታ ለመሻት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

እንዲሁም ሞሮኒ 7:12–19 7፡12–19ን ይመልከቱ።

1 ነገሥት 6–89:1–9

በጌታ ቤት በተገቡ ቃል ኪዳኖች አማካኝነት ጌታ ከእኔ ጋር ይኖራል።

1 ነገሥት 6–7 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር የሠራውን የተቀደሰ ቤት ዝርዝር መግለጫ ታገኛላችሁ። እንደ ጥንቶቹ እስራኤላውያን ዝርዝሩ ለእናንተ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህን ምዕራፎች ማንበብ ለእነርሱ የጌታ ቤት መኖሩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንድትረዱ ይረዳችኋል። ለእናንተስ አሰፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የሰለሞን ቤተ መቅደስ የተለያዩ ክፍሎች ምን ሊያመለክቱ እንደሚችሉ ማሰላሰል ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ በ1 ነገሥት 6፡35 ላይ ያሉት ኪሩቤል፣ ዛፎች እና አበቦች ምን ሊያመለክቱ እንደሚችሉ አስቡ። (በተጨማሪም ዘፍጥረት 3:24⁠ን ይመልከቱ።)

ምዕራፍ 8 ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሲጨርስ ያቀረበውን ጸሎት ይዘግባል (ቁጥር 22-61 ይመልከቱ)። ሰሎሞን የጠየቃቸውን በረከቶች ዝርዝር ለማውጣት አስቡ። ስለ እነዚህ በረከቶች የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው? (በ2 ነገሥት 6፡11–139፡1–9 ላይ ያለውን የጌታን ተስፋዎች አስተውሉ።) ወደ ጌታ ቤት ሄዳችሁ የምታውቁ ከሆነ እዚያ ስለማምለክ የነበራችሁን ተሞክሮ አስቡ። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን መጠበቅ የጌታን በረከቶች እንድታገኙ የረዷችሁ እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፤ ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “I Love to See the Temple,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 28–31።

የባራንኪላ ኮሎምቢያ ቤተመቅደስ

የባራንኪላ ኮሎምቢያ ቤተመቅደስ

1 ነገሥት 8:6111:1–11

“[ልቡ ከእግዚአብሄር ጋር ፍጹም አልነበረም]”

“ከእግዚአብሄር ጋር ልባችሁ ፍጹም ይሁን” ማለት ምን ማለት ነው? (1 ነገሥት 8:61)። ተግባራችን ፍጹም ከመሆን የተለየ ነገር ነው? እንዴት? 1 ነገሥት 11፡1–11ን አንብቡ እና ጌታ ስለ ሰሎሞን ልብ የተናገረውን አስተውሉ። በሕይወታችሁ ውስጥ ልባችሁን ከጌታ ወደ “ሌሎች አማልክት” ሊያዞሩ የሚችሉ ተጽዕኖዎች ይኖሩ እንደሆን ማሰብ ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ሳሙኤል 11

ስፈተን ጌታ ሊረዳኝ ይችላል።

  • ንጉሥ ዳዊት” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 117–20፣ በ2 ሳሙኤል 11 ላይ ያለውን ታሪክ ለልጆቻችሁ እንድትነግሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ዳዊት ያደረጋቸውን የተሳሳቱ ምርጫዎች እንዲለዩ ልጆቻችሁን ጠይቋቸው፣ በምትኩ ሊያደርግ የሚገባውን ጥሩ ምርጫዎች ጠቁሙ። በምንፈተንበት ጊዜ ትክክለኛውን ምርጫ እንድናደርግ የሚረዱን ልናደርጋቸው የምንችላቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?

    2:11

    King David

  • ስለ ዳዊት አሳዛኝ ኃጢአቶች ማንበብ የብልግና ምስሎችን ስለሚያስከትለው ጉዳት ለመወያየት ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። “What Should I Do When I See Pornography?” የሚለው ቪዲዮ (ወንጌል ቤተ መጻሕፍት) ጠቃሚ መመሪያ አለው። ልጆቻችሁ የብልግና ምስሎች ሲያጋጥሟቸው ሊያደርጉ ስለሚችሉት ነገር እቅድ እንዲያወጡ እርዷቸው።

    5:46

    What should I do when I see pornography?

1 ነገሥት 8፥8፡22–61

በጌታ ቤት ቃል ኪዳኖችን ማድረግ እንዲሁም መጠበቅ በመንገዱ እንድሄድ ይረዳኛል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በ1 ነገሥት 8 ውስጥ ስለ ቤተመቅደስ መመረቅ ስትማሩ፣ በዚህ ሳምንት ዝርዝር ውስጥ የቤተመቅደሶችን ሥዕሎች መመልከት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በሥዕሎቹ ላይ ስለሚያዩዋቸው ዝርዝሮች እንዲናገሩ አድርጉ። በቁጥር 57–58 ላይ አጽንኦት ልትሰጡ ትችላላችሁ። “[በጌታ መንገድ] ሁሉ እንሄዳለን” ሲባል ምን ማለት ነው? (1 ነገሥት 8:58)። ልጆቻችሁ ለሚሰጡት ለእያንዳንዱ መልስ አንድ እርምጃ ሊሄዱ ይችላሉ።

  • በቤተመቅደስ ውስጥ የምትገቡትን ቃል ኪዳኖች መጠበቅ በጌታ መንገዶች እንድትሄዱ እንዴት እንደሚረዳችሁ ለልጆቻችሁ ንገሩ። እነዚህ ቃል ኪዳኖች ምን እንደሆኑ ልትነገሯቸው ትችላላችሁ (አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ27.2፣ የወንጌልላይብረሪ ይመልከቱ)። እንዲሁም እንደ “I Love to See the Temple” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 95) ያለ አንድ መዝሙር አብረው መዘመር ይችላሉ።

የሰለሞን ቤተመቅደስ

የሰሎሞን ቤተመቅደስ የሚያሳይ ስዕል፣ በሳም ሎውሎር

1 ነገሥት 11:1–11

በህይወቴ ጌታን ማስቀደም እችላለሁ።

  • የሰሎሞን ሚስቶች በእሱ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት እንደሆነ ማንበባችን ስለ “ሌሎች አማልክት” ምሳሌዎች ወይም በጌታ ምትክ ሰዎች ስለሚያመልኳቸው ወይም ስለሚወዷቸው ነገሮች ውይይት ሊመሩ ይችላሉ። በሕይወታችን ውስጥ ከምንም ነገር በላይ እርሱን እንደምንወደው እንዴት እናሳያለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

የሰለሞን ቤተመቅደስ

በኢየሩሳሌም የሚገኘው የሰሎሞን ቤተመቅደስ ምርቃት፣ በዊልያም ሆል

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ በጌታ ቤት ቃል ኪዳኖችን ማድረግ በመንገዱ እንድሄድ ይረዳኛል