“ሰኔ 8–14 (እ.አ.አ) “እግዚአብሔር…ልብን ያያል”፡ 1 ሳሙኤል 8-10፤ 13፤ 15–16፣” .ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ሰኔ 8–14 (እ.አ.አ) ‘እግዚአብሔር…ልብን ያያል’”፡ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በእረፍት ውሃ ዘንድ፣ በሳይመን ዲዊ
ሰኔ 8–14 (እ.አ.አ)፡ “እግዚአብሔር…ልብን ያያል”
1 ሳሙኤል 8–10፤ 13፤ 15–16
ሳኦል የአህዮች ጠባቂ ነበር። ምንም እንኳን ረጅም እና ያማረ ቢሆንም፣ “በአይ[ኑ]ታናሽ” እንደሆነ የሚሰማው እና ስለቤተሰቡ ሁኔታ ጥሩ አመለካከት ያልነበረው ነበር (1ሳሙኤል 9፡2–3፣21፤ 15፡17 ተመልከቱ)። በእስራኤል ፊት እንደ ንጉሣቸው በሚቀርብበት ቀን ሳይመጣ ቀረ፤ በጣም ፈርቶ ስለነበርም “[ተሸሸገ]” (1 ሳሙኤል 10፡21–22)። ሳኦልን ስትመለከቱ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ድል እንዲያደርጉ እንደሚመራ—ወይም በኋላ ላይ በትዕቢት እንደሚሞላ እና በጌታ ላይ እንደሚያምጽ ላትገምቱ ትችላላችሁ።
ዳዊት በግ ጠባቂ ነበር። እንደ ሰባቱ ታላላቅ ወንድሞቹ በአካል የሚያስደንቅ አልነበረም። ሳሙኤል ለእስራኤል አዲስ ንጉሥ ሊመርጥ በመጣበት ቀን ዳዊትን ከዕጩዎች መካከል ማካተት ጠቃሚ ስላልመሰለው እሱ ከበጎች ጋር በሜዳ ላይ ተትቶ ነበር። ዳዊትን ስትመለከቱ ግዙፉን ሰው በማሸነፍ በእስራኤል ውስጥ እጅግ የተሳካለት ንጉሥ ለመሆን እምነትና ድፍረት ይኖረዋል ብላችሁ ላትገምቱ ትችላላችሁ።
ነገር ግን ጌታ ከመለያዎቻችን፣ ከአካላዊ መልካችን እና በራስ አለመተማመናችን ባሻገር ያያል። በምትኩ እርሱ “ልብ ያያል” (1 ሳሙኤል 16፡7)። ልባችን ትክክለኛ ባይሆን እንኳን፣ ፈቃደኛ ከሆንን፣ “ሌላ ልብ” ይሰጠናል (1 ሳሙኤል 10፡9)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
1 ሳሙኤል 8
ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሴ ነው።
1 ሳሙኤል 8 የእስራኤላውያንን ዕጣ ፈንታ ለዘላለም ስለሚለውጥ ክስተት ይናገራል። እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ጥበቃ ለማግኘት ጎረቤቶቻቸው የነበራቸውን ማለትም ንጉሥ እንዲገዛቸው ፈለጉ። ስለ ጥያቄያቸው እና የጌታ ምላሽ ስታነቡ፣ ደህንነትን እና ምሪትን ለማንግኘት ማንን እንደምትፈልጉ አስቡ። ጌታ “[በእናንተ ላይ እንዲነግስ]” (1 ሳሙኤል 8፡7) ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡ።
በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ እስራኤልን እንዲመሩ ስለተጠሩ በርካታ ነገሥታት ታነባላችሁ። ስለእነሱ ስትማሩ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቡ።
-
በ1ሳሙኤል 8፡10-18 ላይ ያሉት የጌታ ማስጠንቀቂያዎች እንዴት ተፈጸሙ?
-
እስራኤላውያን ምድራዊ ንጉሥ ለማግኘት ያደረጉት ምርጫ ምን አይነት ተጽዕኖ አሳደረባቸው?
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ከምድራዊ ነገሥታት የሚለየው እንዴት ነው? ክርስቶስ ንጉሳችሁ እንዲሆን ከሕይወታችሁ ምን ዓይነት ዓለማዊ ተጽዕኖዎችን ማስወገድ እንዳለባችሁ አስቡ።
በተጨማሪም “Rejoice, the Lord Is King!,” መዝሙሮች፣ ቁጥር 66 ይመልከቱ።
1 ሳሙኤል 9–10፤ 16:1–13
እግዚአብሔር ሰዎች በመንግሥቱ እንዲያገለግሉ በትንቢት ይጠራቸዋል።
እግዚአብሔር የእስራኤልን ነገሥታት እንዴት እንደመረጠ በ1ሳሙኤል 9–10 እና 16 አንብቡ (በተለይ 9፡15–17፤ 10፡1–12፤ 16፡1–13 ተመልከቱ)። ዛሬ በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ “በትንቢት… በእግዚአብሔር መጠራት” ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚረዷችሁን ምንባቦች ፈልጉ (የእምነት አንቀፅ 1፡5)። ጥሪውን የሚያስተላልፈውን (ሳሙኤልን)፣ የሚጠራውን ሰው (ሳኦል እና ዳዊትን) እንዲሁም እነሱ ያገለግሏቸው ዘንድ የተጠሩት ሰዎች (እስራኤላውያን) ቦታ ራሳችሁን ለማስቀመጥ አስቡ። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ከንግግራቸው እና ከተግባራቸው ምን ትማራላችሁ?
ሳሙኤል ሳኦልን ሲቀባ የሚያሳይ ምስል፣ በፒ. Mann, © Providence Collection/ፈቃዱ የተገኘው ከ goodsalt.com
1 ሳሙኤል 13፥5–14፤ 15
“መታዘዝ ከመስዋእትነት … ይበልጣል።”
ሳኦል በ1 ሳሙኤል 10 ላይ ምን ያህል ዓይናፋር እንደነበረ ስንመለከት፣ ንጉሥ ከሆነ በኋላ ስለሱ “አመጸኝነት” እና “እልከኝነት” ማንበብ ያስገርማል (1ሳሙኤል 15፡23)። ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? በ1ሳሙኤል 13፡5-14 ላይ ለውድቀት የዳረገውን ምን አይነት አመለካከቶች እና ባህሪዎች ታያላችሁ?
በ1 ሳሙኤል 15 ላይ ሳኦል ጥሩ ምክንያት እንዳለው በማሰብ ከጌታ የተሰጠውን ትእዛዝ ስላለመታዘዘዙ ታነባላችሁ። ከሳኦል ትክክለኛ ያልሆኑ ምርጫዎች ለመማር ቁጥር 22ን ተመልከቱ እንዲሁም “መስዋዕት” እና “የአውራ በግ ስብ” የሚሉትን ቃላት እንደ መስማት እና ጌታን እንደመታዘዝ አስፈላጊ ባልሆኑ ነገር ግን መልካም በሚመስሉ ነገሮች ተኩ። በህይወታችሁ የጌታን ፈቃድ በማስቀደማችሁ እንዴት ተባረካችሁ?
1 ሳሙኤል 16:6–12
“እግዚአብሔር … ልብን ያያል”
የአንድን ነገር ወይም ሰው “ፊት [በማየት]” ላይ ብቻ በመመስረት ውሳኔ ላይ በመድረሳችሁ ኋላ ላይ ትክክል እንዳልነበራችሁ ታውቋችሁ ያውቃል? ምናልባት እንደሚታየው ጣፋጭ ያልሆነ ነገር በልታችሁ ታውቁ ይሆናል። ወይም በአንድ ሰው ላይ አላግባብ ፈርዳችሁ ይሆናል።
ሳሙኤል የእስራኤልን አዲስ ንጉሥ ሲፈልግ፣ እግዚአብሔር የተሻለን መንገድ አስተማረው። ስለሱ በ1 ሳሙኤል 16፡6-7 አንብቡ እና ሰዎች የሌሎችን “ፊት [በማየት]” የሚመዝኑባቸውን መንገዶች ለመዘርዘር አስቡ። አንዳንዶቹን ከሽማግሌ ክሪስቶፍ ጂ.ጂራድ-ኬሪየር “We Are His Children” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ) 114–16) መልእክት ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። ልክ እንደ ጌታ “ልብን” ማየት ምን ማለት ነው? (1 ሳሙኤል 16፥7)። በሽማግሌ ጂራድ-ኬሪየር መልእክት ውስጥም የዚህን ምሳሌዎች ማግኘት ትችላላችሁ። አዳኙ ከሰው ውጫዊ ገጽታ ባሻገር የተመለከተበትን ሌሎች ጊዜያት ማሰብ ትችላላችሁ። (ለምሳሌ፣ ማርቆስ 12:41–44፤ ሉቃስ 5:1–11፤ 19:1–9፤ ዮሐንስ 4:5–30፤ ሙሴ 6:31–36 ተመልከቱ።) ከእነዚህ ምሳሌዎች ምን ትማራላችሁ?
ሌሎችን እና ራሳችሁን በምታዩበት መንገድ የአዳኙን ምሳሌ መከተል የምትችሉት እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችሁ ከሌሎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል? ለአንድ ሰው በልቡ ስለምታዩት መልካምነት ለመንገር አስቡ።
እንዲሁም ዩሊሲስ ሶአሬስ፣ “Brothers and Sisters in Christ,” ፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2023፣ 70–73 ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
1 ሳሙኤል 8
ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሴ ነው።
-
1 ሳሙኤል 8ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ እስራኤላውያን ንጉሥ መፈለጋቸው መጥፎ ሐሳብ እንደሆነ ሳሙኤል የነገረበትን ምክንያት እንዲያገኙ እርዷቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን ንጉሣች ማድረግ የሚሻለው ለምንድነው? አንድ ላይ የወረቀት አክሊል በመስራትና ተራ በተራ በማድረግ ኢየሱስ ንጉሣችን እንዲሆን እንደምንፈልግ ለማሳየት ልናደርግ የምንችለውን ነገር ማካፈል ትችላላችሁ። (በተጨማሪም ኤርሚያስ 23፡5፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥59 ይመልከቱ።)
1 ሳሙኤል 8:6፤ 9:15–17፤ 10:1–24፤ 16:1–13
በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎች በእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው።
-
እግዚአብሔር ሳኦል እና ዳዊትን ንጉስ እንዲሆኑ የመረጣቸው ዘገባዎች ልጆቻችሁ ሰዎች ዛሬ ላይ በመገለጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለማገልገል እንዴት እንደሚጠሩ እንዲረዱ ይረዳቸዋል። እነዚህን ታሪኮች ለማስተማር፣ ከታሪኮቹ ላይ ክስተቶችን በወረቀት ላይ ጻፉ፣ ከዚያም ልጆቻችሁ የቅዱሳት መጻህፍት ምዕራፎችን ስታነቡ በትክክለኛው ቅደም ተከተል ማስቀመጥ ይችላሉ (በተጨማሪም በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ “ወጣቱ ዳዊት” የሚለውን 110–11 ይመልከቱ)። ከዚያም እግዚአብሔር አንድን ስራ ወይም ጥሪን እንድትፈጽሙ በመንፈሳዊ ሃይል ስለባረከበት ጊዜ ማውራት ትችላላችሁ (1 ሳሙኤል 10፡9–10 ይመልከቱ)።
1:16Young David
-
አምስተኛ የእምነት አንቀፅን ለልጆቻችሁ ለማስተማር ይህ ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ጥሪያችሁን እንዴት እንደተቀበላችሁ ንገሯቸው። በእግዚአብሔር እንደተጠራችሁ እንዴት አወቃችሁ?
ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊት በቤተልሔም የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ቀባው በባላጌ ባሎግ
1 ሳሙኤል 16:1–13
እግዚአብሔር ልብን ያያል
-
የተግባር ትምህርት ልጆቻችሁ በ1ሳሙኤል 16፡7 ያለውን መርህ እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። ለምሳሌ፣ ከትክክለኛ ይዘቱ ጋር የማይዛመድ ምግብ ወይም መጠቅለያ ወይም ሽፋን ያለው መጽሐፍ ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። 1 ሳሙኤል 16:7 እና ይህ የተግባር ትምህርት ለራሳችን እና ለሌሎች ሰዎች ሊኖረን ስለሚገባ አመለካከት ምን ይጠቁማሉ? እንደ “Love One Another” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 136) ያሉ ይህን መርህ የሚያጎሉ መዝሙሮችን ዘምሩ።
የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን ተጠቀሙ። ልጆቻችሁ ከወንጌል መርህ ጋር በተያያዘ የሚያዩትና የሚዳስሱት ነገር ሲኖራቸው፣ የማስታወስ ዕድላቸው ይበልጥ ሰፊ ነው። ለምሳሌ፣ 1 ሳሙኤል 16:7ን ከእነሱ ጋር ስታነቡ፣ “[ውጫዊ ገጽታ]” ላይ ተመስርቶ ከመፍረድ ይልቅ “ልብን [በማየት]” እንደ ጌታ ለመመልከት መሞከር ስለሚኖርብን ሃሳብ ለማስረዳት ለአይን ግራ የሚያጋቡ ፎቶዎችንአንዲያገኙ እርዷቸው።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ “ፊትን” (ቁጥር 7) ብቻ ሳይሆን ለምን “ልብን [መመልከት] እንዳለባችሁ የተማራችሁበትን ተሞክሮ ልታካፍሏችሁ ትችላላችሁ። እንዲሁም አንዳችሁ በሌላው ልብ ውስጥ ስለምታዩአቸው መልካም ባሕርያት ተራ በተራ ልታወሩ ትችላላችሁ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።