“መጋቢት 23–29 (እ.አ.አ)። ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ”፡ ዘፀአት 1-6፡ “ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
“መጋቢት 23–29 (እ.አ.አ)። ‘ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ’፣”ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ) (2026)
ሙሴ እና የሚቃጠለው ቍጥቋጦ፣ በጄሪ ቶምሰን
መጋቢት 23–29 (እ.አ.አ)፡ “ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ”
ዘጸአት 1–6
በግብጽ ለመኖር የቀረበላቸው ግብዣ የያዕቆብን ቤተሰብ አድኖታል፡፡ ነገር ግን ከመቶዎች አመታት በኋላ የአነሱን ዘሮች “ዮሴፍን ባላወቀ“ አዲስ ፈርኦን በባርነት ወስዶ አሸበራቸው፡፡(ዘጸአት 1–6) እስራኤላውያን እግዚያብሄር ለምን በእነርሱ በቃልኪዳን ህዝቡ ላይ ይህ እንዲደርስባቸው እንደፈቀደ መጠየቃቸው ተፈጥሯዊ ይሆን ነበር፡፡ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አስታውሶ ነበር? አሁንም የእርሱ ህዝቦች ነበሩ? ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደነበር ማየት ይችል ነበር?
ተመሳሳይ ጥያቄዎችን የመጠየቅ ፍላጎት ያደረባችሁ ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ “እግዚያብሄር እያለፍኩበት ያለውን ሁኔታ ያውቃል?” የእርዳታ ልመናዬንስ ሊሰማ ይችላል?” ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸው እንዲህ ያለውን ጥያቄ ይመልሳል፡ እግዚያብሄር ህዝቡን አይረሳም፡፡ ከእኛ ጋር የገባቸውን ቃል ኪዳኖች ያስታውሳል እንዲሁም በራሱ ጊዜ እና መንገድ ይፈጽማቸዋል፡፡ “በተዘረጋ ክንድ አድናችኋለሁ።“ “ከተገዥነ[ታችሁም] ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚያብሄር ነኝ“(ኦሪት ዘጸአት 6፥6–7) ሲል ይናገራል፡፡
ስለኦሪት ዘጸአት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘጸአት“ የሚለውን ተመልከቱ፡፡
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዘፀአት 1–2
የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም እግዚአብሔር በእኔ በኩል ሊሰራ ይችላል።
በዘፀአት 1–2 ላይ ስላሉት ሴቶች ምን ያስደንቃችኋል? እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለውን እቅድ እንዲፈፅም የረዱት እንዴት ነው? ጥረታቸው በእግዚአብሔር ሥራ ስለማገልገል ምን ያስተምራችኋል?
ዘፀአት 1–31
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።
ዘፀአትን ማንበብ ከመጀመራችሁ በፊት፣ እያለፋችሁበት ስላለው፣ ጌታ እንደሚያድናችሁ ተስፋ ስለምታደርጉት ችግር አስቡ። በዘፀአት 1-3 ውስጥ ከመንፈሳዊ ምርኮ ጋር ወይም ዛሬ ከሚያጋጥሙን ሌሎች ነገሮች ጋር የሚመሳሰሉ ቃላት እና ሀረጎች የትኞቹ ናቸው? እንዲሁም የእስራኤል ልጆች ነጻ መውጣትን እንዴት እንደፈለጉ እና ጌታ እንዴት ምላሽ እንደሰጠ አስተውሉ (ለምሳሌ ዘጸአት 2፡23–25፤ 3፡7–8 ተመልከቱ)። ጌታ “[ያወጣችሁ ዘንድ የወረደው]” እንዴት ነው?
በዘፀአት መጽሐፍ ውስጥ ሙሉ፣ በሙሴ እና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከልም አንዳንድ መመሳሰሎችን ልታስተውሉ ትችላላችሁ (ዘዳግም 18፡18–19፤ 1 ኔፊ 22፡20–21 ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ በዘፀአት 1:22፤ 2፡1–10 እና ማቴዎስ 2፡13–16 ምን መመሳሰሎችን ታያላችሁ? ወይስ በዘጸአት 24፡18 እና በማቴዎስ 4፡1-2 መካከል? ጌታ ስለራሱ እና ስለ ኃይሉ እንድትረዱ የሚፈልገው ምን መስሎ ይሰማችኋል?
ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ምልክቶችን ፈልጉ። “በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በነቢያት እና በሌሎች ታማኝ ወንዶች እና ሴቶች ሕይወት ውስጥ ከአዳኙ ሕይወት ጋር ተመሳሳይነትን ልታገኙ ትችላላችሁ። [ይህን ማድረግ] ትኩረት በማጸጧቸው ቦታዎች ስለ አዳኙ ያሉ እውነቶችን ያሳያል” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 7 ይመልከቱ፤ እንዲሁም ሆሴዕ 12፡10ን)።
እምነት በውሃ ዳርቻ፣ በአኒ ማሪ ኦቦርን
ዘጸአት 3፥1–6
ለቅዱስ ነገሮች እና ቦታዎች አክብሮት ማሳየት እችላለሁ።
የሆነ ነገር በመገረም እና በመደነቅ የሞላችሁን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ? ምላሽ የሰጣችሁት እንዴት ነበር? የተሰማችሁን ስሜትስ እንዴት ትገልጹታላችሁ?
ይህን በአእምሯችን በመያዝ ዘጸአት 3:1–6ን አንብቡ። ስለ ሙሴ የሚያነሳሳ ተሞክሮ ምን ያስደንቃችኋል? ሙሴ ለእግዚአብሄር ያለውን አክብሮት ለማሳየት ምን አደረገ? በድርጊቶቹ እና ለተቀደሱ ነገሮች ባለው አክብሮት መካከል ምን ግንኙነቶችን ታያላችሁ?
እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ በህይወታችሁ ውስጥ ስላሉ ቅዱስ ነገሮች እና ቦታዎች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። እነዚህ ለእናንተ የተቀደሱ የሆኑት ለምንድነው? ከተለመዱት ነገሮች በተለየ መንገድ እንዴት ልታዩአቸው ትችላላችሁ? ማሰላሰላችሁን እንዲመራ፣ የሽማግሌው ዴቪድ ኤ. ቤድናር “Remembering the Promises” (ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 91–93) በሚለው መልእክት ውስጥ “Exceeding Great and Precious Promises” የሚለውን ክፍል መመልከት ትችላላችሁ። እንደ “I Stand All Amazed” (መዝሙሮች፣ ቁ. 193) ያለን መደነቅን የሚያነሳሳ መዝሙር መዘመር ወይም ማዳመጥ ከዚያም ስለ ወንጌል ምን እንደሚያስደንቃችሁ ማሰላሰል ትችላላችሁ።
በእርግጥ አስደናቂ መንፈሳዊ ልምምዶች ካጋጠሙንም በኋላ እንኳን፣ ስለተቀደሱ ነገሮች ከልክ በላይ ግድየለሽ የመሆን አደጋ አለ። ይህን እንዴት ማስወገድ ትችላላችሁ? ይህንን ጉዳይ የሚመለከቱ ሁለት መልዕክቶች እነዚህ ናቸው፣ አንዳቸውን ምረጡና የሚረዷችሁን ገለጻዎች ፈልጉ፡ ዩሊሴስ ሶአሬስ “In Awe of Christ and His Gospel” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 115–17)፣ ጄራልድ ኩዜ፣ “Is It Still Wonderful to You?” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 98–100)።
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6:10–12፤ 63:64 ይመልከቱ።
ኦሪት ዘፀአት 3–4
እግዚአብሄር ስራውን እንዲሰሩ ለሚጠራቸው ሰዎች ሃይልን ይሰጣል።
ዛሬ ሙሴን በታላቅ ነቢይነቱ እና መሪነቱ እናውቀዋለን። ነገር ግን ጌታ መጀመሪያ ሲጠራው ሙሴ ራሱን እንደዚያ አላየም ነበር። ዘፀአት 3–4ን በምታነቡበት ጊዜ የሙሴን ስጋቶች እና ጌታ ለእያንዳንዳቸው የሰጠውን ምላሽ ዘርዝሩ። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብቁ እንዳልሆናችሁ ሲሰማችሁ ሊያነሳሳችሁ የሚችል ምን ታገኛላችሁ? እግዚአብሔር እናንተ ወይም ሌሎች ሥራውን እንድትሠሩ ኃይልን ሲሰጥ ያያችሁት መቼ ነው?
በተጨማሪም የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ “The Church Gives Us Opportunities to Assist in God’s Work” የሚለውን በርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “የቤተ ክርስቲያን አደረጃጀት” ስር ተመልከቱ።
ኦሪት ዘፀአት 5–6
የጌታ አላማ በራሱ ጊዜ ይፈጸማሉ፡፡
የጌታን ፈቃድ ለማድረግ ስንጥር ነገር ግን የጠበቅነውን ውጤት ሳናገኝ ስንቀር፣ በጎ ለማድረግ የምናደርገው ከልብ የመነጨ ጥረት ሳይሳካ የቀረ በሚመስል ጊዜ ተስፋ አስቆራጭ ሊሆን ይችላል። ሙሴ ስላጋጠመው ተመሳሳይ ተሞክሮ ለማወቅዘጸአት 5:4–9፣ 20–23ን አንብቡ። ሙሴ ተስፋ የመቁረጥ ስሜቱን እንዲያሸንፍ ጌታ የረዳው እንዴት ነበር? (ዘጸአት 6፡1–13 ይመልከቱ)። ጌታ የእርሱን ፈቃድ እንድታደርጉ የረዳችሁ እንዴት ነው?
በተጨማሪ ጄፍሪ አር. ሆላንድን፣ “Waiting on the Lord,” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 115–17 ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።
ዘፀአት 1–2
የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም እግዚአብሔር በእኔ በኩል ሊሰራ ይችላል።
-
እስራኤልን ከባርነት ነጻ በማውጣት ረገድ ሙሴ ትልቅ ሚና ነበረው። ነገር ግን እናቱ፣ እህቱ፣ የፈርዖን ሴት ልጅ እና ሌሎች ታማኝ ሴቶች ባይጠብቁት እና ባይንከባከቡት ኖሮ ይህን ማድረግ አይችልም ነበር። በዘፀአት 1፡15–20፤ ዘጸአት 2፡2–10 (በተጨማሪም ዘኍልቍ 26፡59 ተመልከቱ) እና ዘጸአት 2፡16–21 ልጆቻችሁ ስለእነዚህ ሴቶች እንዲማሩ እርዷቸው። እንዲሁም የዚህን ሳምንት የአክቲቪት ገጽ እና “ሕፃኑ ሙሴ” (በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 61-63) ታሪኮቻቸውን ለመንገር መጠቀም ትችላላችሁ። እነዚህ ሴቶች የእግዚያብሄርን እቅድ ለመፈጸም የረዱት እንዴት ነው? በትንሽ እና ቀላል መንገዶች ጨምሮ በእግዚአብሔር ስራ ስለሚረዱ ስለምታደንቋቸው ሌሎች ሰዎች እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ። የእነርሱን ምሳሌ መከተል እንዴት እንችላለን?
1:36Baby Moses
ዘጸአት 3፡1-5
የተቀደሱ ቦታዎችን ማክበር እችላለሁ።
-
ዘፀአት 3፡1–5ን አንድ ላይ ካነበባችሁ በኋላ፣ ልጆቻችሁ እነዚህን ጥቅሶች በራሳቸው ቃል እንዲያጠቃልሉ ጠይቋቸው (“ነቢዩ ሙሴን” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 64–66 ላይ ተመልከቱ)። ሙሴ በጌታ መገኘት ውስጥ አክብሮቱን ያሳየው እንዴት ነበር? ጌታ አክብሮት እንድናሳይ የሚፈልገው እንዴት ነው? እንዲሁም ልጆቻችሁ እኛ አክብሮ ልናሳይ የሚገባንን የተቀደሱ ቦታዎችን ወይም የአክቲቪቲዎች ሥዕሎችን እንድታገኙ (ወይም እንድትስሉ) እንዲረዷችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። ቤታችንን የተቀደሰ ስፍራ ለማድረግ ምን ማድረግ እንችላለን?
1:26Moses the Prophet
-
እንደ “Reverence Is Love” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 31–13) አይነት ስለ አክብሮት አንድ መዝሙር ዘምሩ። ይህን ስታደርጉ፣ ልጆቻችሁ አክብሮት ምን ማለት እንደሆነ የሚገልጹ ቃላትን ወይም ሀረጎችን ማግኘት ይችላሉ። ጓደኛችን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ብታመጡት፣ አክብሮት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት እናብራራለን?
ሙሴ እና አሮን ለህዝቡ ተናገሩ፣ በጄምስ ጄ. ቲሶት
ዘፀአት 3–4
ጌታ አንድ ነገር እንዳደርግ ሲጠይቀኝ፣ ያንን እንድሰራ ይረዳኛል።
-
በዘፀአት 3 ፣ 4፡1–17፣ ውስጥ ያለውን ታሪክ በመጠቀም ልጆቻችሁ ሙሴ ሆነው እንዲተውኑ አድርጉ። እንደ የእጅ ባትሪ ያሉ ቁሶችን ወይም የወረቀት ቅርጻቅርጾችን እንዲሁም የሚቃጠለውን ቁጥቋጦ የሚወክል ተክል ማካተት አስደሳች ሊሆን ይችላል። ሙሴ እግዚአብሔር ስለሰጠው ሥራ ምን እንደተሰማው ልጆቻችሁ እንዲያውቁ እርዷቸው (ዘጸአት 3:11፤ 4:1፣ 10 ተመልከቱ)። ምናልባት ተመሳሳይ ስሜት ተሰምቷችሁ ስለነበረ ጊዜ አንዳችሁ ለሌላችሁ ማካፈል ትችላላችሁ። ሙሴን ለመርዳት ምን አይነት ምክር እናካፍል? በዘጸአት 3፡12፤ 4:2–9፣ 11–12ጌታ ሙሴን እንዴት እንዳበረታው አንብቡ። ጥሪያችሁን እንድትፈጽሙ፣ መነሳሳትን እንድትከተሉ ወይም ለእናንተ ከባድ የሆነን ሌላ ነገር እንድታደርጉ አዳኙ እንዴት እንደረዳችሁ ለልጆቻችሁ ተናገሩ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።