“መጋቢት 9–15 (እ.አ.አ)። ‘ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ’፡ ዘፍጥረት 37–41 “ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
“መጋቢት 9–15 (እ.አ.አ)። ‘ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ’፣”ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ) (2026)
ዮሴፍ እና ወንድሞቹ፣ በሳም ሎውሎር
መጋቢት 9–15 (እ.አ.አ)፡ ”ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ”
ዘፍጥረት 37–41
እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምኑትን እና ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ሰዎችን እንደሚባርክ እናውቃለን። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እንደዚያ አይመስልም። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የሚታመን ሰው በቤተሰቡ አባላት ይበደላል እንዲሁም ይተዋል። አንዳንድ ጊዜ በድፍረት የንጽህና ህግን ለመጣስ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እንዳደረገ ተደርጎ በሐሰት ይከሰሳል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን በእግዚአብሔር ላይ ለመቆጣት ልንፈተን እንችላለን። “ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ሕይወትን ከባድ የሚያደርግ ከሆነ መሞከር ምን ያደርጋል?” ብለን እንጠይቅ ይሆናል።
የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ እንዲህ ብሎ ጠይቆ ሊሆን ይችላል። በአንድ ወቅት ይህ ታማኝ ሰው በልጽጎ ነበር፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ታማኝ በሆነ ቁጥር የበለጠ መከራ የሚገጥመው ይመስል ነበር። ነገር ግን ዮሴፍ ጌታን አልተወውም፣ ጌታም ዮሴፍን አልተወውም። ይህ ጌታ በዮሴፍ ላይ ክፉ ነገር እንዳይደርስበት ከልክሏል ማለት አይደለም ነገር ግን በዚህ ሁሉ “እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር [ነበረ]” (ዘፍጥረት 39፡3) ማለት ነው።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኦሪት ዘፍጥረት 37፧1-28፤ 39፤ 41:9–45
በመከራዬ ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል።
በተደጋጋሚ መልካም እድል ዮሴፍን የራቀው ይመስል ነበር፤ ነገር ግን ጌታ አልራቀውም። የዮሴፍን ታሪክ ስታነቡ እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች አሰላስሉ: ዮሴፍ ወደ ጌታ ለመቅረብ ምን አደረገ? ጌታ “ከእሱ ጋር” የነበረው እንዴት ነው? (ዘፍጥረት 39፤ 40፡1–19፤ 41፡9–45 ተመልከቱ)። ጌታ በህይወታችሁ ውስጥ መኖሩን እንድታውቁ የሚረዳችሁን ከዮሴፍ ታሪክ ምን ተማራችሁ?
ስለህይወታችሁ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ልትጠይቁም ትችላላችሁ፡፡ በመከራችሁ ጊዜያት ጌታ እንዳልተዋችሁ ምን ማስረጃ አይታችኋል? ለቤተሰብ አባላት እና ለመጪው ትውልድ ልምዳችሁን እንዴት ማካፈል እንደምትችሉ አስቡ ( 1 ኔፊ 5፧14ን ይመልከቱ)፡፡
እርግጥ ነው፣ ወደፊት ሌሎች ፈተናዎች ይገጥሟችኋል። እነዚህ ፈተናዎች ከጌታ እንዳያርቋችሁ አሁን ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ምንም ቢፈጠር ለእርሱ ቅርብ ሆናችሁ እንድትቆዩ ለማበረታታት ለወደፊቱ ራሳችሁ ደብዳቤ ለመጻፍ አስቡ። ከዮሴፍ ህይወት ወይም ከሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን “Our Relationship with God” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022፣ 78–81) መረዳቶችን ማከል ትችላላችሁ።
በተጨማሪም ዮሐንስ 14:18፤ ሮሜ 8:28፤ አልማ 36፡3፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፡7–8፤ “Abide with Me!,” መዝሙሮች፣ ቁ.166 ተመልከቱ።
ዘፍጥረት 37፧5-11፤ 40፤ 41፧1-38
ታማኝ ከሆኩኝ ጌታ ይመራኛል እንዲሁም ያነሳሳኛል።
ዮሴፍ ከጌታ የሚመጡ የህልም መዕእክቶችን የማወቅ ስጦታ ነበረው። ከዘፍጥረት 37፧5-11፤ 40፧5–8፤ 41፧14–25፣ 37–38 ከጌታ ራዕይን ስለመቀበል እና ስለመረዳት ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፣ መገለጥ ለመረዳት ከባድ መስሎ ሲታይ ከዮሴፍ ምሳሌ ምን ልትማሩ ትችላላችሁ? (ዘፍጥረት 40፧8፤ 41፧16ይመልከቱ)?
ጌታ ፍላጎቱን እንዴት እንደገለጸላችሁ እንደሆነ አሰላስሉ? ጌታ በሰጣችሁ መገለጥ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ምን እያደረጋችሁ ነው? ተጨማሪ ምሪት ከእርሱ የምትሹት እንዴት ነው?
የጠጅ አሳላፊውን እና የእንጀራ አበዛውን ህልም እየፈታ፣ በፍራንኮ ጄራርድ
ዘፍጥረት 39:1–20
በጌታ እርዳታ ከፈተና መሸሽ እችላለሁ።
ዮሴፍ ዝሙት ለመፈጸም የሚደርስብንን ፈተና እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ምክር ቢሰጥ ምን የሚል ይመስላችኋል? በዘፍጥረት 39 ላይ ስለገጠመው ስታነቡ ይህንን አስቡ። ለምሳሌ፣ ዮሴፍ ለሚከተሉት አይነት ጥያቄዎች ምን ምላሽ እንደሚሰጥ አስቡ፡
-
እኔ የማደርገውን ማንም የማያውቅ ከሆነ ምን ችግር አለው? (ቁጥር 8-9 ይመልከቱ)።
-
ለመቋቋም እሞክራለሁ ነገር ግን ፈተናው የሚቆም አይመስልም (ቁጥር 10 ይመልከቱ)።
-
ፈተና ጠንካራ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ስሆን ምን ማድረግ አለብኝ? (ቁጥር 12 ይመልከቱ)።
የንጽህና ህግን መታዘዝ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እንዴት ታብራራላችሁ? (ለወጣቶች ጥንካሬ፡ ምርጫ የማድረግ መመሪያ፣ 23–28 ይመልከቱ)።
የዮሴፍ ምሳሌ በእርግጥ በሌሎች የፈተና ዓይነቶች ላይም ሊሠራ ይችላል። የዮሴፍን ምሳሌ በእምሯችሁ ይዛችሁ ፈተናን ለማስወገድ እና ለመቋቋም እቅድ ማውጣትን አስቡ፡፡ ለምሳሌ አንድን ፈተና በማሰብ የሚፈታተኑ ሁኔታዎችን ለማስወገድ እና ፈተናው በሚመጣበት ጊዜ እንዴት “[መሸሽ]” እንደምትችሉ መፃፍ ትችላላችሁ።
|
ፈተና | |
|
ሊወአገዱ የሚገባቸው ሁኔታዎች | |
|
ምላሽ መስጫ እቅድ |
ለእቅዳችሁ ጥቆማ ሊሰጡ የሚችሉ አንዳንድ ሌሎች ጥቅሶች እዚህ ይገኛሉ። አዳኙ ፈተናን ለመቋቋም እንዴት እንደሚረዳችሁ ከእያንዳንዱ ምን ትማራላችሁ? ማቴዎስ 4:1-11፤ 1 ቆሮንቶስ 10:13፤ 1 ኔፊ 15፡23–24፤ 3 ኔፊ 18፡17–18።
እቅዳችሁን ስታዘጋጁ፣ ከዚህ ቀደም ፈተናን በተሳካ ሁኔታ የተቋቋማችሁበትን ወይም የተቃወማችሁበትን ጊዜ ማሰብም ሊጠቅም ይችላል። አዳኙ እንዴት ረዳችሁ? (2 ኔፊ 4፡18–33ይመልከቱ)።
ዘፍጥረት 41:15-57
ጌታ ሊመጡ ለሚችሉ ችግሮች እንድዘጋጅ ይረዳኛል።
ዮሴፍ የፈርዖንን ህልም መተርጎሙ ከረሃብ ለመዳን ጥበብን እና ተግባራዊ ምክሮችን አስገኝቷል (ዘፍጥረት 41፡15–57 ይመልከቱ)። በዚህ ታሪክ ውስጥ ጌታ ለእናንተ ምን ዓይነት መንፈሳዊ መልእክቶች ሊኖረው እንደሚችል አስቡ። ወደፊት ለሚገጥማችሁ ችግር እንዴት እንድትዘጋጁ እንደሚፈልግ ይሰማችኋል?
በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “We Will Prove Them Herewith [ዚህ እንፈትናቸዋለን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 8–11 ተመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘፍጥረት 37
ለቤተሰቤ ደግ መሆን እችላለሁ።
-
በዮሴፍ ቤተሰብ ውስጥ ስለነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ማንበባችን የቤተሰብ አባላትን እንዴት መንከባከብ እንዳለብን እንድንወያይ ሊያነሳሳን ይችላል። በዘፍጥረት 37 ላይ ያለውን የዮሴፍን እና የወንድሞቹን ታሪክ ለመንገር፣ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች ወይም “የዮሴፍ የተመሳሱ ሕልሞች” (በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 47–51) ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች መጠቀም ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ስለ ታሪኩ የሚያውቁትን ዝርዝሮች እንዲያካፍሉ አድርጓቸው። በዮሴፍ ቤተሰብ ውስጥ እንዳሉ አድርገው ልጆቻችሁ እንዲያስቡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በቤተሰብ ውስጥ አስታራቂ ለመሆን ምን ይናገሩ ወይም ያደርጉ ነበር? ለምሳሌ በቤተሰባችን ውስጥ “በሰላም [መናገር]” ሲባል ምን ማለት ነው? (ቁጥር 4) ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ አስታራቂ የሆነው እንዴት ነው?
2:17Joseph’s Inspired Dreams
ዘፍጥረት 37:18–28፤ 39:20–23; 41:38
መጥፎ ነገሮች ሲከሰቱ እግዚአብሔር ሊረዳኝ ይችላል።
-
ልጆቻችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥማቸው፣ ጌታ ከዮሴፍ ጋር እንደነበረው ሁሉ ከእነሱም ጋር እንደሚሆን ማወቅ አለባቸው። ልጆቻችሁ በዮሴፍ ላይ የደረሰውን ከባድ ነገር እንዲዘረዝሩ ልትረዷቸው ትችላላችሁ (ዘፍጥረት 37፡23–28፤ 39፡20፤ ወይም “የዮሴፍ የተነሳሱ ሕልሞች” እና “ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 47–51፣ 52–56 ተመልከቱ)። ልጆቻችሁን ከሚያገኙት ከእያንዳንዱ ችግር በኋላ፣ “እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበር” (ዘፍጥረት 39፡2) እንዲሉ አድርጉ።
2:17Joseph’s Inspired Dreams
2:50Joseph in Egypt
-
ልጆቻችሁ ዘፍጥረት 39፡1-3፣ 20–23ን “እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ” ለሚለው እና ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ ሐረጎች ምሳሌ ይፈልጉ። ይህ ሐረግ ምን ማለት እንደሆነ ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ አድርጉ። ጌታ ከእኛ ጋር መሆኑን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? በአስቸጋሪ ጊዜ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር በነበረ ጊዜ የተሰማችሁን ስሜት እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።
የግብፁ ዮሴፍ በእስር ቤት፣ በጄፍ ዋርድ (ዝርዝር)
ዘፍጥረት 39:7-12
በጌታ እርዳታ ከፈተና መሸሽ እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁን ከጲጥፋራ ሚስት በመሸሽ ረገድ የዮሴፍን ምሳሌ እንዲከተሉ የሚረዳ የተግባር ትምህርት እዚህ ይገኛል፡ ኢየሱስ ክርስቶስንና ሰይጣንን ለመወከል ሁለት ማግኔቶችን ተጠቀሙ። እኛን ለመወከል እንደ የወረቀት ክሊፕ ያለን ትንሽ ብረት ተጠቀሙ። ከዚያም ልጆቻችሁ ብረቱን ወደ ማግኔቱ ሲያስጠጉ በብረቱ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ እንዲመለከቱ አድርጉ። በዘፍጥረት 39፡7-12 ላይ ያለው የዮሴፍ ገጠመኝ ይህንን እውነት የሚያሳየው እንዴት ነው? ከኃጢአት ለመራቅ እና ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ ምን ማድረግ እንችላለን? በዚህ ውይይት “Temptation Fades as We Seek Christ in Every Thought” (የወንጌል ላይብረሪ) እና እንደ “I Need Thee Every Hour” (መዝሙሮች ቁ. 98) ያለ መዝሙር ሊረዳ ይችላል።
2:58Temptation Fades as We Seek Christ in Every Thought
ሙዚቃን ተጠቀሙ። መዝሙሮች እና ሌሎች ቅዱስ ዘፈኖች ልጆች የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማቸው፣ መንፈስ እንዲሰማቸው እና የወንጌል እውነታዎችን እዲማሩ ሊረዷቸው ይችላሉ። ዜማዎች፣ ሪትሞች እና ቀላል ግጥሞች ልጆች የወንጌልን እውነቶች ለአመታት እንዲያስታውሱ መርዳት ይችላል። ከልጆች ጋር ስትዘምሩ፣ በመዝሙሩ ውስጥ የሚማሩትን መርሆዎች እንዲያገኙ እና እንዲረዱ አግዟቸው።(በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 32)።
-
ልጆቻችሁ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ፈተናዎች እንዲያስቡ እርዷቸው። ከእነዚህ ፈተናዎች እንዴት “መሸሽ” እንደሚችሉ እንዲተውኑ አድርጓቸው።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።