ኑ፣ ተከተሉኝ
መጋቢት 2–8 (እ.አ.አ)። “እግዚአብሔር ያሸንፍ”: ዘፍጥረት 24–33


“መጋቢት 2–8 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔር ያሸንፍ’፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 2–8 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔር ያሸንፍ’፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

ዔሳው ብኩርናውን ለያዕቆብ በአንድ ሳህን ወጥ ሸጠ

ዔሳው ብኩርናውን ሸጠ፣ በግሌን ኤስ ሆፕኪንሰን (ዝርዝር)

መጋቢት 2–8 (እ.አ.አ)፡ “እግዚአብሔር ያሸንፍ”

ዘፍጥረት 24–33

ለራሳችሁ የእግዚአብሔርን በረከት እንዴት ታስጠብቃላችሁ? የአብርሃምና የሣራ የልጅ ልጅ የሆነው የያዕቆብ ታሪክ የዚህን ጥያቄ መልስ ያገኘ የአንድ ሰው ታሪክ ነው ማለት ትችላላችሁ። የበኩር ልጅ የብኩርና በረከት በሚቀበልበት ባህል፣ ያዕቆብ የመንታ ወንድሙን የኤሳውን ተረከዝ በመያዝ ሁለተኛ ሆኖ ተወለደ። “ያዕቆብ” የሚለው ስም “ምትክ”—የሌላን ሰው ቦታ የሚተካ ማለት ነው። ዔሳው ብቁ ባለመሆኑ ምክንያት ያዕቆብ የዔሳውን የብኩርና በረከትን ወራሽ በመሆን ለመተካት ከአንድ ጊዜ በላይ በመሞከር ይህን ስም አስጠብቋል (ዘፍጥረት 25፡30–3426፡34–3527፡36 ተመልከእቱ)። በቤተሰብ ውስጥ አለመግባባት ስላስከተለ ያዕቆብ ነፍሱን ለማዳን ወደ ምድረ በዳ መሸሽ ነበረበት።

ከዓመታት በኋላ ያዕቆብ ወደ ቤቱ እንዲመለስ እግዚአብሔር አዘዘው። ያዕቆብ በመንገድ ላይ ሳለ፣ በትህትና እንደገና ከእግዚአብሔር በረከትን ፈለገ። ቅዱሳት መጻህፍት ይህንን ለያዕቆብ “[የትግል]” ጊዜ ብለው ይገልጹታል፣ እሱም “ካልባርክኝ” (ዘፍጥረት 32፡26) አልለቅህም አለ። ከዚያም ትምህርቱ—እና በረከቱ መጣ። እግዚአብሔር የያዕቆብን ስም ወደ እስራኤል ለወጠው—ይህም ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ “እግዚአብሔር ያሸንፍ” ማለት ነው። እስራኤል የእግዚአብሔርን እጅግ ትልቅ ዋጋ ያላቸውን የቃል ኪዳኑን በረከቶች ለመቀበል፣ ሌላን ሰው መተካት አስፈላጊ እንዳልሆነ ተማረ። በረከቶቹ የሚገዙ ወይም የሚያዙ ወይም የምናሸንፋቸው አይደሉም። እግዚአብሔር በሕይወታቸው ያሸንፍ ዘንድ የእስራኤልን ስም ለሚጠብቁ ሁሉ በነጻ የሚሰጣቸው ነው።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 24

የቃልኪዳን ጋብቻ ለእግዚያብሄር ዘላለማዊ እቅድ አስፈላጊ ነው።

ዘፍጥረት 24ን በምታነቡበት ጊዜ፣ አብርሃም የልጁን የይስሐቅ ጋብቻ ለምን በጣም አስፈላጊ አድርጎ እንዳየ ራሳችሁን ጠይቁ። ጋብቻ ለእግዚያብሄር አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

ለጠንካራ ትዳርና ቤተሰብ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የርብቃን የትኞቹን ባሕርያት አግኝታችኋል? (በተለይ ቁጥር 15–28፣ 57–61 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም Topics and Questions፣ “ንስሐ፣” የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 25፥29–34

ከጊዜያዊ ነገሮች ይልቅ ለዘላለማዊ ነገሮች ዋጋ መስጠት እችላለሁ።

በይስሐቅና ርብቃ ባሕል፣ ቤተሰቡን ከመንከባከብ ትልቅ ኃላፊነት ጋር የበኩር ልጅ ትልቅ ውርስ የሆነውን ብኩርና ይቀበላል። ዘፍጥረት 25፥29–34ን ስታነቡ ኤሳው ለምን ለምግብ ሲል ብኩርናውን ለመተው ፈቃደኛ እንደነበረ አስቡ፡፡ በዚህ ዘገባ ውስጥ ለራሳችሁ ምን ትምህርት አገኛችሁ? ሁለት ዝርዝሮችን ማውጣት ሊጠቅም ይችላል፡(1) እግዚአብሔር ሊሰጣችሁ የሚፈልጋቸው ዘላለማዊ በረከቶች እና (2) ትኩረታችሁን ሊሰርቁ የሚችሉ ዓለማዊ ነገሮች። ከዚያም “ብኩርና”ን ከመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ፣ “ወጥ”ን ደግሞ ከሁለተኛው ዝርዝር በሆነ ነገር በመተካት ጥቅሶቹን ማንበብ ትችላላችሁ። በአዳኙ እና በወንጌሉ ዘላለማዊ በረከቶች ላይ እንዴት ትኩረት ታደርጋላችሁ?

በተጨማሪ ማቴዎስ 6:19–33፤ ኤም. ሩሰል ባላርድ፣ “በጣም አስፈላጊ የሆነውን አስታውሱ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 105–7።

ያዕቆብ በቤቴል

ያዕቆብ በቤቴል፣ በጄምስ ስመታም

ዘፍጥረት 28

የሴሚናሪ ምልክት
የጌታ ቤት ቃል ኪዳኖች የእግዚአብሔርን ኃይል ወደ ሕይወቴ ያመጣሉ።

ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ ሳለ ህይወቱን የሚቀይር ህልም አየ። እጅግ የተቀደሰ ተሞክሮ ስለነበር ያዕቆብ “በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው” (ዘፍጥረት 28፡16) በማለት ቦታውን ቤቴል ወይም “የእግዚአብሔር ቤት” ብሎ ሰየመው።

ዘፍጥረት 28ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ለያዕቆብ ይህን ተሞክሮ ቅዱስ ያደረገው ምን እንደሆነ ራሳችሁን ትጠይቁ ይሆናል። በወቅቱ በምን አይነት ሁኔታ እያለፈ ነበር? ምንስ ተሰምቶት ሊሆን ይችላል? እንዲሁም የጌታን ቤት የሚያስታውሱ ቃላትን እና ሀረጎችን ከቁጥር 10-22 መፈለግ ትችላላችሁ። ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ቤቱ እና ስለ ቃል ኪዳኖቹ ምን አይነት ግንዛቤ ታገኛላችሁ?

በዚህ ንድፍ መጨረሻ ላይ የያዕቆብን ሕልም የሚያሳይ ሥዕል አለ፤ በምታነቡበት ጊዜ ልትጠቀሙት ትችላላችሁ። ስለ ሕልሙ የራሳችሁን ሥዕላዊ መግለጫ ብትፈጥሩ ምን ታደርጉ ነበር? ከታሪኩ ውስጥ የትኞቹን እውነቶች ለማሳየት ትሞክራላችሁ?

Nearer, My God, to Thee፣” የሚለው መዝሙር (መዝሙር፣ ቁጥር 100) በያዕቆብ ህልም አነሳሽነት የተጻፈ ነው። በዚህ መዝሙር እና በዘፍጥረት 28፡10-22 መካከል ምን ግንኙነት ታያላችሁ? ቤተመቅደስ ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ የመቅረብ ስሜት እንዲሰማችሁ የሚረዳችሁ እንዴት ነው? ለዚህ ጥያቄ ከፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “The Temple and Your Spiritual Foundation” (ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 93–96) መልእክት ውስጥ መልስ ለማግኘት አስቡ። እንዲሁም ቃል ኪዳኖችን እና የጌታን ቤት በረከቶችን በአጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ27.2 (የወንጌል ላይብረሪ) ላይ መከለስ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። እነዚህን ቃል ኪዳኖች መጠበቅ የእግዚአብሔርን ሃይል ወደ ህይወታችሁ እንዴት አድርጎ ሊያመጣ ይችላል?

አዲስ ነገር ፈጣሪ ሁኑ። ቅዱሳት መጻህፍትን ለመማር ከማንበብ በተጨማሪ ብዙ መንገዶች አሉ። አንዳንድ ሰዎች የምንባቦቹ ሥዕል በመሳል ቅዱሳን መጻህፍትን በተሻለ ሁኔታ ይረዳሉ። ሌሎች ደግሞ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር በተገናኘ የተቀደሰ መዝሙር ውስጥ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ያገኛሉ። ራሳችሁን በአንድ የመማሪያ መንገድ አትገድቡ፤ የተለያዩ መንገዶችን ለመሞከር ዝግጁ ሁኑ።

ዘፍጥረት 29፧31-3530፧1-24

ጌታ በመከራዎቼ ያስታውሰኛል።

ዘፍጥረት 29፥31-35 እና 30፥1–24ን ስታነቡ፣ እግዚያብሄር ለራሄል እና ለሊያ የነበረውን ይቅርታ የሚገልጹ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። እግዚአብሄር እንዴት “መከራችሁን እንደሚያይ“ እና “እንደሚያስታውሳችሁ“ አሰላስሉ (ዘፍጥረት 29፥3230፥22)።

ኦሪት ዘፍጥረት 32–33

አዳኙ ቤተሰቤን መፈወስ ይችላል።

ያዕቆብ ወደ ከነአን በተመለሰ ጊዜ ኤሳው እንዴት እንደሚቀበለው “ፈርቶ እና ተጨነቆ“ ነበር (ዘፍጥረት 32፥7)። ዘፍጥረት 32–33ን በምታነቡበት ጊዜ የራሳችሁን የቤተሰብ ግንኙነት—ምናልባትም ፈውስ የሚያስፈልገውን አስቡ። ምናልባት ይህ ታሪክ ለአንድ ሰው መልካም ነገር ለማድረግ ጥረት እንድታደርጉ የሚያነሳሳችሁ ሊሆን ይችላል። እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ንባባችሁን ሊመሩ ይችላሉ:

  • ያዕቆብ ኤሳውን ለመገናኘት እንዴት ተዘጋጀ?

  • ኦሪት ዘፍጥረት 9–12ውስጥ ካለው የያዕቆብ ጸሎት ለናንተ ምን ጎልቶ ይታያችኋል?

  • ከኤሳው ምሳሌነት ስለ ይቅርባይነት ምን ትማራላችሁ?

  • አዳኙ የቤተሰብ ግንኙነታችንን እንድንጠግን የሚረዳን እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘፍጥረት 24:10–21

ለሌሎች ደግ መሆን እችላለሁ።

  • የርብቃን አስደናቂ የደግነት ምሳሌ ለማሳየት በዘፍጥረት 24፡10–21 ያለውን ታሪክ በማጠቃለል ከታች ያለውን ሥዕል ወይም የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆቻችሁ ልታሳዩ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ታሪኩን በመተወን ሊደሰቱ ይችላሉ። ይህ እናንተ እና ልጆቻችሁ ስላያችሁት የደግነት ተግባር እንድትወያዩ ሊያመራችሁ ይችላል።

  • እንደ “Kindness Begins with Me” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 145) አይነት ስለ ደግነት አንድ ላይ ለመዘመር አስቡ። ልጆቻችሁ “ደግነት” የሚለውን ቃል (ወይም ተመሳሳይ ቃል) ማዳመጥ እና ሲሰሙ መቆም ይችላሉ። ይበልጥ እንደ ርብቃ ደግ ልትሆኑ የምትችሉት እንዴት ነው?

የርብቃ  ስዕል

የብሉይ ኪዳን ጀግኖች፣ በዲሊ ማርሽ (ዝርዝር)

ዘፍጥረት 25:21-34

ከዓለማዊ ነገሮች ይልቅ ዘላለማዊ ነገሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

  • ዘፍጥረት 25፡21–34 ላይ ያለውን ታሪክ ልጆቻችሁ እንዲረዱ ለመርዳት “ያዕቆብ እና ኤሳው”ን (በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 38-41) ለመጠቀም አስቡ። ምናልባት ልጆቻችሁ ኤሳው ብኩርናውን በወጥ መለወጥ ይኖርበት እንደሆነ ምክራቸውን እንደጠየቀ አድርገው ሊያስቡ ይችላሉ። ለእሱ ምን ሊሉት ይችላሉ?

    2:5

    Jacob and Esau

  • ለእናንተ እና ለልጆቻችሁ ለዘላለም አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ምንድናቸው? ምናልባት ልጆቻችሁ እነዚህን ነገሮች የሚወክሉ ምስሎችን ወይም ዕቃዎችን ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል። እነዚህ ነገሮች ለእኛ አስፈላጊ እንደሆኑ ለጌታ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ዘፍጥረት 28:10–22

ቃል ኪዳኖች ወደ የሰማይ አባት እንድመለስ ሊረዱኝ ይችላሉ።

  • ዘፍጥረት 28፡10–22ን አንድ ላይ ስታነቡ፣ ቃል ኪዳኖቻችን እንደ መሰላል እንዴት እንደሆኑ ለመነጋገር መሰላልን ወይም ደረጃን (ወይም በዚህ ንድፍ መጨረሻ ላይ እንዳለው አይነት ምስል) መጠቀም ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ መሰላል ላይ እየወጡ እንደሆነ በማስመሰል በእያንዳንዱ እርምጃ ለምሳሌ ስንጠመቅ፣ ቅዱስ ቁርባን ስንወስድ ወይም ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ቃል ስለምንገባበት ጊዜ ተናገሩ። ቃልኪዳኖቻችን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡን እንዴት ነው?

ዘፍጥረት 32:6–1133:1–4

የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቤን እንድወድ ሊረዱኝ ይችላሉ።

  • እነዚህን ጥቅሶች ለማስተዋወቅ ከብዙ አመታት ከባድ ስሜት በኋላ ያዕቆብ ከኤሳው ጋር እንደገና ሊገናኘው እንደሆነ ማስረዳት ትችላላችሁ። ዘፍጥረት 32:6–11ን አንድ ላይ አንብቡ። ያዕቆብ ምን ተሰማው? እርዳታ ለማግኘት ምን አደረገ? እግዚአብሔር የያዕቆብን ጸሎት እንዴት እንደመለሰ ለማወቅ ዘፍጥረት 33:1–4ን አብራችሁ አንብቡ። ያዕቆብ እና ኤሳው ዛሬ ቢያነጋግሩን በቤተሰባችን ውስጥ አለመግባባት በሚኖርበት ጊዜ የሚረዳንን ምን ሊሉን ይችላሉ?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ያዕቆብ መሰላል እና መላእክት ከሰማይ ሲወርዱ እያለመ

የያዕቆብ፣ በኬን ስፔንሰር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፦ለሌሎች ደግ መሆን እችላለሁ