“የካቲት 23–መጋቢት 1 (እ.አ.አ)። ‘በውኑ ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር አለን?’ ዘፍጥረት 18–23፣”ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
“የካቲት 23–መጋቢት 1 (እ.አ.አ)። ‘በውኑ ለእግዚያብሄር የሚሳነው ነገር አለን?’፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ)
ሳራ እና ይስሃቅ፣ በስኮት ስኖው
የካቲት 23–መጋቢት 1 (እ.አ.አ): “በውኑ ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር አለን?“
ዘፍጥረት 18–23
እጅግ በሚያሳዝን እና እጅግ በሚያስደስት ኩነቶች የተሞላው የአብርሃም ህይወት በራዕይ ለተማረው እውነት ምስክር ነው—ይሄውም፣ ” [የእኛ] ጌታ እግዚአብሄር የሚያዘንን ነገሮች በሙሉ እንደ[ምንፈጽም] ለማየት ነው፡፡” (አብርሃም 3፧25)፡፡ አብርሃም እና ሳራ ታማኝነታቸውን ያረጋግጡ ይሆን? እድሜያቸው ገፍቶ ልጅ በሌላቸው ሰዓት ታላቅ ትውልድ ለመስጠት እግዚያብሄር በሰጠው የተስፋ ቃል ማመናቸውን ይቀጥሉ ይሆን? ይስሃቅም ከተወለደ በኋላ በእርሱ አማካኝነት ቃሉን እንደሚፈጽም እግዚያብሄር ቃል ገብቶ የነበረውን ያንኑ ልጅ እንዲሰዋ ሲታዘዙ እምነታቸው ሊታሰብ በማይችለው ውስጥ ሊጸና ይችል ይሆን?
አብርሃም እና ሣራ በእግዚአብሔር ታመኑ፣ እርሱም ይተማመንባቸው ነበር (ዘፍጥረት 15፡6፤ ሮሜ 4፡3 ይመልከቱ)። በዘፍጥረት 18–23 ውስጥ በእግዚያብሄር ተስፋዎች ለማመን ፈቃደኝነታችንን እንድናስብ ሊያነሳሱን የሚችሉ፣ ከክፋት ለመሸሽ፣ ደግሞም ወደ ኋላ ላለመመለስ እንዲሁም መስዋእትነቱ ምንም ይሁን ምን በእግዚያብሄር ለመታመን ከአብርሃም እና ከሌሎች ህይወት የተወሰዱ ታሪኮችን እናገኛለን፡፡ እኛን በመፈተንም እግዚአብሔር ያሳድገናል።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዘፍጥረት 18፧9-14፤ 21–7
ጌታ ተስፋዎቹን በራሱ ጊዜ ይፈጽማል፡፡
ጌታ ለሚታመኑት ታላቅ ተስፋዎችን ሰጥቷል፣ ነገረ ግን አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች እነዚያ ተስፋዎች እንዴት ሊፈጸሙ እንደሚችሉ እንድንጠይቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ አብርሃም እና ሳራ እንደዚያ ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ከእነሱ ተሞክሮዎች ምን ትማራላችሁ? ጥናታችሁን ጌታ ለአብርሃም ገብቶ የነበረውን ቃል ኪዳን በ ዘፍጥረት 17፥ 4፣15–22ውስጥ በመከለሰስ መጀመር የሚጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ኦሪት ዘፍጥረት 17፥23 [በ ዘፍጥረት17፥ 17ውስጥ፣ የግርጌ ማስታወሻ b]፤ ኦሪት ዘፍጥረት18፥ 9–12ን ይመልከቱ)፡፡ ጌታ በተስፋዎቹ የበለጠ እምነት እንዲኖራቸው ሊረዳቸው ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር? ዘፍጥረት 18፥ 14ን ይመልከቱ)፡፡
በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ እምነታችሁን የሚገነባ ምን ነገር ታገኛላችሁ? በራሳችሁ ወይንም በሌሎች ህይወት ውስጥ—ሌሎች ምን ተሞክሮዎች—ጌታ የሰጣችሁን ተስፋዎች በራሱ ጊዜ እና መንገድ እንደሚፈጽም እምነታችሁን አጠናክረዋል? እንዲሁም በዚህ ህይወት ቃል የተገባላቸው በረከቶች በማይፈጸሙበት ጊዜ እምነታችሁን እንዴት ማጽናት እንደምትችሉ ማሰብ ትችላላችሁ። በዕብራውያን 11፡8-13 እና በፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን መልእክት “ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመን ተራሮችን ያንቀሳቅሳል ውስጥ ምን ምክር ታገኛላችሁ? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 101–4)።
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥68ን ይመልከቱ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት 19፥12–29
ጌታ ሃጢያትን እንድሸሽ እና ወደ ኋላ እንዳልመለከት አዞኛል።
ስለ ሎጥ እና ስለ ቤተሰቡ ስታነቡ ከክፋት ስለመሸሽ ምን ትምህርት ትማራላችሁ? ለምሳሌ ሎጥ እና ቤተሰቡ ጥፋትን እንዲያመልጡ ለመርዳት መላዕክቱ ከተናገሩት እና ካደረጉት ምን ነገር ያስገርማችኋል?( ኦሪት ዘፍጥረት 19፥12–17ን ይመልከቱ)፡፡ እናንተ እና ቤተሰባችሁ በዚህ አለም ካሉ ክፉ ተጽዕኖዎች እንድትሸሹ ወይም ከለላ እንድታገኙ ጌታ እንዴት ይረዳችኋል? በአዳኙ ላይ እምነት በማድረግ ልትጠባበቁ ስትችሉ “ወደ ኋላ [ለመመልከት]” (ቁጥር 26) ልትፈተኑ የምትችሉባቸውን ሁኔታዎች አስቡ። 2 ኔፊ 9:62 በዚህ መርህ ላይ ባላችሁ ግንዛቤ ላይ ምን ይጨምራል?
በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 19፥9–15 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ይመልከቱ፡፡
ዘፍጥረት 19፥26
የሎጥ ሚስት ምን ጥፋት አጠፋች?
ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል:
“በግልጽ እንደሚታየው የሎጥ ሚስት ያጠፋችው ጥፋት ወደኋላ መመልከቷ ብቻ አልነበረም፤ በልቧ ወደኋላ ለመመለስ መፈለጓ ነበር፡፡ የከተማውን ድንበር እንኳን ለቃ ሳትወጣ ሰዶም እና ገሞራ ሲያቀርቡላት የነበረውን ነገር አስቀድማ እየናፈቀች የነበረ ይመስላል፡፡…
“የሎጥ ሚስት ጌታ ትታ እንድትሄድ በጠየቃት ነገር ምክንያት ቂም ይዛበት ወደኋላ ተመልክታ ሊሆን ይችላል። … ስለዚህ እሷ ወደ ኋላ ማየቷ ብቻ አይደለም፤ በናፍቆት ወደ ኋላ መመልከቷ ነው። ባጭሩ ካለፈው ነገር ጋር የነበራት ቁርኝት በወደፊቱ ላይ ካላት እምነት በልጦ ተገኘ። ያ በርግጥ የኃጢአቷ አካል ነበር።
“… ስላለፉት ቀናት እንዳታስቡ ወይም ትናንትናዎች ምንም መልካም ቢሆኑ በከንቱ እንዳትመኟቸው እለምናችኋለሁ። ካለፈው መማር እንጂ እዚያው ላይ መኖር የለብንም። ወደ ኋላ መለስ ብለን የምንመለከተው ከሚያበሩ ልምዶች ፍም እንጂ አመድ ለመፈለግ አይደለም። በተጨማሪ መማር ያለብንን ተምረን ያገኘነውን ምርጡን ተሞክሮ ይዘን ስንመጣ፣ ወደ ፊት በማየት እምነት ሁል ጊዜ ወደፊት እንደሚጠቁም እናስታውሳለን። …
“…ያለፉ ስህተቶችን ጨምሮ ባለፈው ህይወት መኖር ትክክል አይደለም! ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አይደለም። …
“ለእያንዳንዱ ትውልድ ሁሉም [ህዝብ] እጣራለሁ፣‘የሎጥን ሚስት አስቧት‘[ሉቃስ 17፥32]፡፡ እምነት ለወደፊት ነው፡፡ እምነት የሚገነባው ባለፈው ነገር ላይ ነው ነገር ግን በዚያ ለመቆየት በፍጹም አይፈልግም፡፡ እምነት እግዚያብሄር ለእያንዳንዳችን ታላቅ ነገሮች እንዳሉት እንዲሁም ክርስቶስ በእውነት ‘ለሚመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህን ነው‘ ብሎ ያምናል (ዕብራውያን 9፥11)” (“The Best Is Yet to Be፣” ኢንዛይን፣ ጥር 2010(እ.አ.አ)፣ 24፣ 26)።
አብርሃም እና ይስሐቅ፣ በሃሮልድ ኮፒንግ
ኦሪት ዘፍጥረት 22፥1–19
አብርሃም ይስሃቅን ለመስዋዕት ለማቅረብ የነበረው ፈቃደኝነት ከእግዚያብሄር እና ከልጁ ጋር አምሳልነት ያለው ነው፡፡
አብርሃም ይስሀቅን እንደመስዋዕት እንዲያቀርብ እግዚያብሄር የጠየቀበትን ሁሉንም ምክንያቶች ባናውቅም በእግዚያብሄር ላይ ያለውን እምነት መፈተኛ እንደነበረ እናውቃለን። “ከእግዚያብሄር እና ከአንድያ ልጁ ጋር አምሳልነት ያለው“ እንደነበረም እናውቃለን (ያዕቆብ 4:5)፡፡ ዘፍጥረት 22፡1–19ን ስታነቡ፣ አብርሃም ለይስሐቅ ባቀረበው መስዋዕት እና አብ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕት ባደረገበት መንገድ ምልክቶችን ወይም ተመሳሳይነቶችን መፈለግ ትችላላችሁ። እንደዚህ ባለው ቻርት ላይ ያገኛችሁትን ለመጻፍ አስቡ፡
|
አብርሐም እና ይስሀቅ |
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ |
|---|---|
አብርሐም እና ይስሀቅ ይስሐቅ የአብርሃምና የሣራ አንድያ ልጅ ነበር (ዘፍጥረት 22፡2፤ በተጨማሪ ዕብራውያን 11፡17 ተመልከቱ)። | የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ የአብ አንድያ ልጅ ነው (ዮሐንስ 3፡16) |
አብርሐም እና ይስሀቅ ይስሐቅ በበግ ምትክ ሊሰዋ ነበር (ዘፍጥረት 22፡7-9) | የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር በግ ነው (ዮሐንስ 1፡29) |
ከአዳኙ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት ምን ምልክቶች ወይም ተመሳሳይነቶች የበለጠ ትርጉም ያላቸው ሆነው አገኛችሁ? የሰማይ አባት ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳይ መዝሙር ለመዘመር ወይም ግጥሙን ለማንበብ አስቡ፣ ለምሳሌ “God Loved Us, So He Sent His Son,” መዝሙሮች፣ ቁ. 187። እንዲሁም ስለ ሰማይ አባት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ስሜት እና ስላደረጉላችሁ መስዋዕትነት መመዝገብ ትችላላችሁ።
ስለ አዳኛችን መስዋዕትነት የበለጠ ማጥናት ከፈለጋችሁ፣ የፕሬዘዳንት ጄፍሪ አር. ሆላንድን “እነሆ የእግዚአብሔር በግ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 44–46) የሚለውን መልእክት ለማንበብ አስቡ። በግ የእግዚአብሔር ልጅ ኃይለኛ ምልክት የሆነው ለምንድነው? ፕሬዘደንት ሆላንድ ለሰማይ አባት ስጦታ ያላችሁን አክብሮት የሚጨምር ምን አስተማሩ?
በተጨማሪም “Akedah (The Binding)” የሚለውን ቪዲዮ የወንጌል ላይብረሪ ላይ ተመልከቱ።
Akedah (The Binding)
ለማስተማር የሚታዩ ነገሮች ተጠቀሙ። በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የተለያዩ ነገሮችን ለመጨመር በዘፍጥረት 18-23 ያሉትን ታሪኮች ስታጠኑ፣ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ካሉት ሥዕሎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ እናንተ እና ቤተሰባችሁ ወይም ክፍላችሁ በአብርሃም እና በይስሐቅ ሥዕሎች ላይ ያሉ ነገሮችን ማየት ትችላላችሁ። እነዚህ ነገሮች ለታሪኩ ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ ተናገሩ፣ እንዲሁም እነዚህን በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ አግኟቸው። የእግዚአብሔር ልጅ መስዋዕትነት ምልክት ታሪክ እንዴት ያጎላሉ?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘርጥረት 17:15–21፤ 18:14፤ 21:1–7
እግዚአብሔር የገባውን ቃል እንዲፈጽም ማመን እችላለሁ።
-
አብርሃምና ሣራ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ላይ ያላቸውን እምነት ለማወቅ ልጆቻችሁ በጣም የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት መጠበቅ ስለነበረባቸው ጊዜ ማውራት ትችላላችሁ። ከዚያም በዚህ መግለጫ መጀመሪያ ላይ የሳራን እና የይስሐቅን ምስል መመልከት እና እግዚአብሔር ለእሷ እና ለአብርሃም ስለገባው ቃል ኪዳን መናገር ትችላላችሁ (በተጨማሪም “አብርሃም እና ሳራ” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 28–31 ይመልከቱ)። ታማኝ ከሆንን እግዚአብሔር ቃል ስለገባልን ነገሮች ልጆቻችሁ እንዲያስቡ እርዷቸው። ትዕግስት እንዲኖራቸው እና እግዚአብሔር የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እንዲያምኑ አበረታቷቸው።
2:20Abraham and Sarah
-
በዘፍጥረት 18:14 ላይ ያለውን ጠቃሚ እውነት ልጆቻችሁ እንዲማሩ ለመርዳት ከጥቅሱ የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር ላይ እያንዳንድ ቃል በተለያየ ወረቀት ላይ መጻፍ ትችላላችሁ። ከዚያም ወረቀቶቹን ቀላቅሉና ልጆቻችሁ ቃላቱን በትክክለኛው ቅደም ተከተል እንዲያስቀምጡ ጋብዟቸው። ጌታ የማይቻል የሚመስለውን ነገር ያስቻለበትን ምሳሌ ለማግኘት እናንተ እና ልጆቻችሁ ዘፍጥረት 17፡15–21፤ 21፡1–7ን ማንበብ ትችላላችሁ። ምንም እንኳን የማይቻሉ ቢመስሉም ወይም ረጅም ጊዜ ቢወስዱም ጌታ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ያላችሁን እምነት ለልጆቻችሁ አጋሩ።
ዘፍጥረት 19:15–26
ክፋትን መሸሽ እችላለሁ።
-
አንድ ሰው ትክክል እንዳልሆነ የሚያውቁትን ነገር እንዲያደርጉ ሊጋብዛቸው የሚችልበትን ሁኔታዎች ልጆቻችሁን ጠይቋቸው። እነዚህን ሁኔታዎች እንዴት “[እንሸሻለን]”? የሎጥ ቤተሰብ በጣም ክፉ በሆነች ከተማ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር እና መላእክቱ ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋቸው እንደነበር ዘፍጥረት 19፡15-26ን በማጠቃለል ተናገሩ። እናንተ እና ልጆቻችሁ ከቁጥር 15–17፣26 አብራችሁ ስታነቡ፣ ዛሬ ከክፋት “[ሸሽተን ማምለጥ]” እና “ወደ ኋላ [አለመመልከት]” (ቁጥር 17) ለእኛ ምን ትርጉም እንዳለው ጠይቋቸው።
ሰዶም፣ በጁሊየስ ስክኖር ቮን ካሮልስፈልድ
ዘፍጥረት 22:1–14
አብርሃም ጌታን ታዘዘ።
-
የአብርሃምንና የይስሐቅን እንዲሁም የስቅለትን ሥዕሎች መጠቀም (የወንጌል አርት መጽሐፍ ቁ. 9፣ 57 ይመልከቱ) ልጆቻችሁ በዘፍጥረት 22 ላይ ያለውን ታሪክ ከአዳኙ መሥዋዕት ጋር እንዲያነጻጽሩ ሊረዳ ይችላል (ማቴዎስ 27፡26-37 ይመልከቱ)። ስለሰማይ አባት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብርሃም እና ከይስሐቅ እና ከስቅለቱ ምንባብ ምን እንማራለን? (በተጨማሪም “አብርሃምን እና ይስሐቅ” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 34–37 ይመልከቱ)
2:0Abraham and Isaac
-
ከልጆቻችሁ ጋር መመሪያዎችን እንዲከተሉ የሚጠይቅ ቀላል ጨዋታ ማሰብ ትችላላችሁ? ምናልባት መመሪያዎቹ ወደተሰወረ የአዳኙ ምስል ሊመሩ ይችላሉ። ጨዋታው የሰማይ አባት ከእርሱ እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደገና መኖር እንድንችል እንድናደርግ ስላዘዘን ነገሮች ውይይትን ሊያነሳሳ ይችላል። እንደ “Keep the Commandments” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 146–47) ያለ መዝሙር ለመዘመር አስቡ። የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽም ሊረዳ ይችላል።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።