ኑ፣ ተከተሉኝ
የካቲት 16–22 (እ.አ.አ)። “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን“፡ ዘፍጥረት 12-17፤ አብርሃም 1–2


“የካቲት 16–22 (እ.አ.አ)። “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን“፡ ዘፍጥረት 12-17፤ አብርሃም 1–2፡ “.ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 16–22 (እ.አ.አ)። “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን“፡ “.ኑ፥ ተከተሉኝ 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

መልከጼዴቅ በረከት ለመስጠት በአብረሃም ራስ ላይ እጆቹን ጭኖ

መልከ ጼዴቅ አብርሐምን ባረከ፣ በዋልተር ሬን (ዝርዝር)

የካቲት 16–22 (እ.አ.አ)፡ “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን“

ኦሪት ዘፍጥረት 12-17አብርሃም 1–2

እግዚያብሄር ከእርሱ ጋር በገባው ቃል ኪዳን ምክንያት አብርሃም “የታማኞች አባት“ (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 138፥41) እና “የእግዚያብሄር ወዳጅ” (ያዕቆብ 2:23) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ዛሬ ሚልዮኖች እንደ ቀጥተኛ የዘር ሃረጋቸው ይቀበሉታል፣ እንዲሁም ሌሎች ወደኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመለወጥ እንደቤተሰቡ ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም አብርሃም ራሱ ቸግር ካለበት ቤተሰብ ነው የመጣው—እውነተኛውን የእግዚአብሄር አምልኮ ትቶ የነበረው አባቱ አብርሃምን ለሃሰት አማልክት ሊሰዋው ሞክሮ ነበር፡፡ ያም ቢሆን የአብርሃም ፍላጎት“ታላቅ የጽድቅ ተከታይ ለመሆን“ ነበር፤(አብርሃም 1፥2) እናም የህይወት ታሪክ ዘገባው እግዚአብሄር ፍላጎቱን እንዳከበረለት ያሳያል፡፡ የአንድ ሰው የቤተሰብ ታሪክ ምንም ይሁን ምን ወደፊቱ በተስፋ ሊሞላ እንደሚችል የአብርሃም ህይወት እንደምስክር ጎልቶ ይታያል፡፡

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አብርሀም 1፥1–19.

እግዚያብሄር ስለእምነቴ እና ስለጽድቅ ፍላጎቴ ይባርከኛል፡፡

ሽማግሌ ኒል ኤል አንደርሰን እንዲህ አስተምረዋል፥ “ሁላችንም በቤተሰቦቻችን [እና] በባህላችን ተጽዕኖ ይደረግብናል፣ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ እና በግል የምንቆጣጠረው እና የምንፈጥረው ነገር በውስጣችን እንዳለ አምናለሁ። … በጊዜ ሂደት፣ የውስጣችን ምኞት ህይወት በመዝራት በምርጫችን እና በድርጊታችን ውስጥ ይታያል።” (“Educate Your Desires, Elder Andersen Counsels,” ChurchofJesusChrist.org). አብርሃም 1፡1–19 ሽማግሌ አንደርሰን ያስተማሩትን እንዴት እንደሚያሳይ አስቡ። እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ:

  • አብርሃም ምን ፈለገ? ፍላጎቱ በድርጊቶቹ ይገለጡ የነበረው እንዴት ነበር? እግዚአብሔር ፍላጎቱን የደገፈው እንዴት ነው?

  • ፍላጎቶቻችሁ ምን ምን ናቸው? በድርጊታችሁ ውስጥስ እንዴት ይታያሉ? እግዚአብሔር እንዴት ይደግፋችኋል?

  • የቤተሰብ አባላቶቻቸው ጽድቅን ለማይፈልጉ እነዚህ ጥቅሶች ምን መልዕክት ይዘዋል?

ከአብርሃም እና ከሣራ ታላቅ ፍላጎቶች መካከል አንዱ የሆነው—ልጅ መውለድ—ለብዙ ዓመታት ሳይሳካ ቀርቶ ነበር (ዘፍጥረት 15፡1–6 ይመልከት)። አብርሃምና ሣራ ይህን ፈተና እንዴት እንደተቋቋሙ ከዕብራውያን 11:8–13 ምን ትማራላችሁ? አዳኙ የገባው ቃል “ሩቅ” ቢሆንም እንኳን “[እንድትቀበሉት]” የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም “Deliverance of Abraham” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

1:38

Deliverance of Abraham

ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1–313፥15–1615፥1–617፥1–8፣ 15–22አብርሃም 2፥6–11

የሴሚናሪ ምልክት
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንድገባ እና እንድጠብቅ ይፈልጋል።

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? ምክንያቱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ቃል ኪዳን ማድረግ ስለሚፈልግ ነው። ይህ ቃልኪዳን በአብርሃም ትውልድ ወይም “ዘር“ ውስጥ እንደሚቀጥል እና “ይህን ወንጌል የተቀበሉት ሁሉ…እንዳንተ ዘር ይቆጠራሉ“ ሲል ቃል ገብቷል (አብርሃም 2፥10–11)። በሌላ አነጋገር፣ ስትጠመቁ እና የበለጠ በሙላት በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን ስትገቡ ቃል ኪዳኑ በእናንተ ውስጥ ይቀጥላል ማለት ነው (ገላትያ 3፡26–29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፡30–32 ይመልከቱ)።

በዚህ ምክንያት፣ አብርሃም 2፡6–11ን በማጥናት እግዚአብሔር በእርግጥ ለአብርሃምና ለሣራ የሰጠውን የተስፋ ቃል ዝርዝር ጻፉ (በተጨማሪም ዘፍጥረት 12፡1–313፡15–1615፡1–617፡1–8፣ 15–22 ተመልከቱ) እነዚህ በረከቶች ለእናንተም ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው?

ከእነዚህ ተስፋዎች አንዳንዶቹ ዘላለማዊ ተመሳሳይነት አላቸው። እንደ ውርስ ምድር ወይም ብዙ ዘር ያሉ ተስፋዎች ለዘላለም የሚፈጸሙት እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፡1–4132፡20–24፣ 28–32ተመልከቱ)

የበረከቶችን ተስፋ ከመስጠቱም በተጨማሪ እግዚአብሔር አብርሃምን “ለበረከት ሁን” ብሎታል (ዘፍጥረት 12፡2፤ አጽንዖት ተጨምሯል)። ይህ ምን ማለት ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? እናንተ በረከት መሆን የምትችሉት እንዴት ነው? (አብርሃም 2፡11 ይመልከቱ)።

ስለ ቃል ኪዳኖች ለማስተማር፣ ሽማግሌ ዴል ጂ. ሬንሉድ በአማዞን ወንዝ ውስጥ ስላለው ማዕበል፣ ፕሬዘደንት ኤሚሊ ቤሌ ፍሪማን ደግሞ በተሰበረ ቁርጭምጭሚት ድንጋያማ መንገድ ላይ ስለመራመድ ተናግረዋል (“Accessing God’s Power through Covenants,”ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 35–37ይመልከቱ፤ “Walking in Covenant Relationship with Christ,” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 76–79)። “እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደርግ የሚፈልገው ለምንድነው?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚረዱትን አንድ ወይም ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ከመልዕክቶቹ ፈልጉ።

ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲማማሩ ጋብዙ። ስለ ቃል ኪዳኖች ቤተሰባችሁን ወይም የቤተክርስቲያንን ክፍል የምታስተምሩ ከሆነ፣ እያንዳንዱ ሰው የሽማግሌ ረንለንድን ወይም የፕሬዘደንት ፍሪማንን መልእክት የተወሰነ ክፍል እንዲያጠና መስጠትን አስቡ። ከዚያም የተማሩትን ለቀሪው ቤተሰብ ወይም ለክፍሉ ማካፈል ይችላሉ። ይህ ሰዎች እንዲመሰክሩ እና እርስ በርሳቸው እንዲማማሩ ያስችላቸዋል፣ ይህም መንፈስን ይጋብዛል። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር] 26ን ይመልከቱ።)

እንዲሁም ርዕሶች እና ጥያቄዎችን፣ “የአብርሃም ቃል ኪዳን”፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ በዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ ”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፡ ቃል ኪዳኑ” ተመልከቱ።

አብርሐም እና ሣራ

የአብርሃም ቃል ኪዳን፣ በዲሊን ማርሽ (ዝርዝር)

ዘፍጥረት 14:18–19የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፡25–40

“መልከ ጼዴቅ የእምነት ሰው ነበር”

መልከ ጼዴቅን ከማያውቀው ሰው ጋር እያስተዋወቃችሁ እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡ። ምን ልትሉ ትችላላችሁ? በየጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፡26–27፣ 33–38 (በመጽሐፍ ቅዱስ አባሪ) ውስጥ ያሉትን ሃሳቦች ፈልጉ፤ አልማ 13፡13–19ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፡1–4። በእነዚህ የመልከጼዴቅ ገለጻዎች ውስጥ ምን ዓይነት የክርስቶስ ዓይነት ባሕርያትን ታገኛላችሁ? የመልከ ጼዴቅን ህይወትን ማጥናታችሁ የመልከ ጼዴቅን ክህነትን በምትመለከቱበት መንገድ ላይ ምን ተጽእኖ ያሳድራል?

ዘፍጥረት 14:18–24የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፡36–40

አብርሃም አስራት ከፍሏል።

ዘፍጥረት 14፡18–24 እና የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፡36–40 (በመጽሐፍ ቅዱስ አባሪ) አብርሃም ስለ ሀብት ስላለው አመለካከት ምን ተማራችሁ? ለምሳሌ በዘፍጥረት 14፡23 ላይ ለሰዶም ንጉሥ የሰጠውን ምላሽ ልብ በሉ። የአሥራትን ሕግ ማክበር ለገንዘብ ባላችሁ አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

ዘፍጥረት 16

እግዚአብሔር ይሰማኛል።

ዘፍጥረት 16ን ስታነቡ በአጋር እንደደረሰው ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እየተስተናገዳችሁ እንደሆነ የተሰማችሁን ጊዜ ታስቡ ይሆናል። “እስማኤል” ማለት “እግዚአብሔር ይሰማል” ማለት እንደሆነ አስተውሉ። እግዚአብሔር እንደ ሰማችሁ ያሳያችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም “Secret Prayer,” መዝሙር፣ ቁጥር. 144 ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አብርሐም1:182:8

ኢየሱስ ክርስቶስ እጆቼን ይዞ ይመራኛል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ አብርሃም 1:18 እና 2:8ን ስታነቡ በሁለቱም ጥቅሶች ላይ የተጠቀሰውን የአካል ክፍል እንዲያዳምጡ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ምናልባት አንድ ልጅ ዓይኖቹን የሚጨፍንበት ከዚያም የልጁን እጅ ይዛችሁ አንድ ቦታ የምትመሩበትን ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ። ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ እጃችንን ይዞ ሲመራን ወይም ሲጠብቀን ምን እንደሚሰማን መናገር ትችላላችሁ።

ዘፍጥረት 13:5–12

አስታራቂ መሆን እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ በዘፍጥረት 13፡5-12 የሚገኘውን ታሪክ አብርሃምን፣ ሎጥን እና እረኞቹን መስለው መተወን ያስደስታቸው ይሆናል። ለቤተሰባችን ወይም ለጓደኞቻችን አስታራቂ በመሆን ረገድ የአብርሃምን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? መልሶቻቸውን ተራ በተራ ለመተወን ሞክሩ።

አብርሃም ሎጥን እያናገረው

የሎጥ ምርጫ፣ በዊልያም ፍሬድሪክስ © ፕሮቪደንስ ስብስብ/ ከgoodsalt.com የተፈቀደ

ዘፍጥረት 13:16ዘፍጥረት 15:1-617:1–8አብርሃም 2፡9-11

እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንድገባ ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁን በእቃ ውስጥ ያለን አሸዋ፣ በሌሊት የሰማይ ከዋክብትን ወይም በዚህ ዝርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ምስል ለማሳየት አስቡ። ይህ በዘፍጥረት 13፡1615፡1–6 የእግዚአብሔርን ተስፋዎች እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። የእግዚአብሔር ተስፋዎች የማይቻሉ በሚመስሉበት ጊዜ እንኳን እንዴት ማመንን እንደተማራችሁ ተናገሩ።

  • ልጆቻችሁን ስለ ቃል ኪዳኖች ለማስተማር፣ ቃል ስለገቡበት ወይም አንድ ሰው ቃል ስለገባላቸው ጊዜ እንዲነግሯችሁ ጠይቋቸው። የሚረዳችሁ ከሆነ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በጥምቀት ወቅት ወይም በቤተመቅደስ ውስጥ የገባችሁትን ቃል ኪዳን ጨምሮ የራሳችሁን አንዳንድ ምሳሌዎችን አካፍሉ። ቃል ኪዳኖቻችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ባላችሁ ግንኙነት ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት ነው? ከዘፍጥረት 15፡1–617:1–8አብርሃም 2፡9–11 የተወሰኑ ሀረጎችን በመምረጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም እና ለሣራ የገባላቸውን አንዳንድ በረከቶች አካፍሉ።

  • ልጆቻችሁ ሲጠመቁ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት እንዲዘጋጁ ለመርዳት፣ በአባሪ ሀ ወይም አባሪ ለ ላይ ከተጠቆሙት የተወሰኑ የአክቲቪቲ ሀሳቦችን መጠቀም ትችላላችሁ።

አብርሃም 1:12–17; ዘፍጥረት 16:7–11

እግዚአብሔር ይሰማኛል።

  • የአብርሃም ሕይወት አደጋ ላይ በነበረበት ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ጠራ። አጋር ደግሞ ብቻዋን በምድረ በዳ በነበረች ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ሰማት አወቀች። እነዚህን ሁለት ታሪኮች ለልጆቻችሁ ለማካፈል አስቡ፡- “አብርሃም እና ሳራ” እና “አጋርየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 28–31፣ 32–33። ከእነዚህ ታሪኮች ስለእግዚያብሄር ምን እንማራለን? ከዚያም እግዚአብሔር እንደሰማችሁ የተሰማችሁን ጊዜ ልምድ አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እንደ “A Child’s Prayer” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 12–13) ያለ መዝሙር ይህን መርሆ ያጠናክራል።

2:20

Abraham and Sarah

1:23

Hagar

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ሳራ ከዋክብትን ቀና ብላ እያየች።

የእግዚያብሄርን ተስፋ ማሰላሰል፣ በ ከርትኒ ማትዝ

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንድገባ ይፈልጋል