ኑ፣ ተከተሉኝ
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች: ቃል ኪዳን


”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች: ቃል ኪዳን፣” ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) 2026 (እ.አ.አ)

“ቃል ኪዳኑ” ኑ፥ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)

የሀሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች

ቃል ኪዳን

በመላው ብሉይ ኪዳን ቃል ኪዳን የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ታነባላችሁ። ዛሬ አብዛኛውን ጊዜ ቃልኪዳኖችን ከእግዚያብሄር ጋር እንደተደረጉ የተቀደሱ የተስፋ ቃላት እናስባቸዋለን ነገር ግን በጥንት አለም ቃልኪዳኖች የሰዎች የእርስ በርስ መስተጋብር አስፈላጊ ክፍሎች ነበሩ። ለደህንነታቸው እና ለመኖር ሰዎች እርስ በርስ መተማመን አስፈለጋቸው እናም ቃልኪዳኖች ያንን እምነት የሚያረጋግጡባቸው መንገዶች ነበሩ።

ስለዚህ እግዚያብሄር ከኖህ፣ ከአብርሃም ወይም ከሙሴ ጋር ስለ ቃልኪዳን በተነጋገረ ጊዜ ከእርሱ ጋር መተማመን ያለበት ግንኙነት እንዲፈጥሩ እየጋበዛቸው ነበር። ይህንን ቃል ኪዳን ወይም የአብርሃም ቃል ኪዳን ብለን እንጠራለን—እግዚአብሔር ከአብርሃምና ከሣራ ጋር የገባውን ከዚያም ለዘሮቻቸው ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ (እስራኤል ተብሎም ከሚጠራው) ያደሰውን ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው። በብሉይ ኪዳን በቀላሉ “ቃል ኪዳን” ተብሎ ይታወቅ ነበር። ብሉይ ኪዳን በመሰረቱ ራሳቸውን የዚህ ቃል ኪዳን ወራሾች—የቃልኪዳን ህዝቦች አድርገው የሚያዩ ህዝቦች ታሪክ እንደሆነ ታያላችሁ።

የአብርሃም ቃል ኪዳን ዛሬም አስፈላጊ እንደሆነ ቀጥሏል፤ በተለይ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን። ለምን? ምክንያቱም በቀጥታ የአብርሃም፣ የይስሃቅ እና የያዕቆብ ዘሮች ብንሆን ወይም ባንሆን እኛም የቃል ኪዳኑ ህዝቦች ስለሆንን ነው። በዚህ ምክንያት የአብርሃም ቃል ኪዳን ምን እንደሆነ እና ለእኛም ዛሬ እንዴት እንደሚሆን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

የአብርሃም ቃል ኪዳን ምንድን ነው?

አብርሃም “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ ለመሆን“ ፈለገ።(አብርሃም 1፥2) አብርሃም ይህ ፍላጎት ሲያድርበት የመጀመሪያው አልነበረም፤ ቃልኪዳንም ለመቀበልም የመጀመሪያው አልነበረም። ከሁሉ በላይ ይህ ዘላለማዊ ቃልኪዳን ነበረ። አብርሃም “የአባቶችን በረከቶች“ (አብርሃም 1፥2)—ለአዳም እና ለሄዋን እንዲሁም ከዚያ በኋላ እነዚህን በረከቶች በትጋት ለፈለጉ በቃል ኪዳን የተሰጡ በረከቶችን ፈለገ።

እግዚያብሄር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን የአስደናቂ በረከቶችን ተስፋ ይሰጣል: የመሬት ውርስ፣ታላቅ ህዝብ፣የክህነት ስርዐቶችን መቀበለል እና በመጪው ትውልድ ሁሉ ክብር የሚሰጠው ስም። ነገር ግን የዚህ ቃል ኪዳን ትኩረት አብርሃም እና ቤተሰቡ በሚቀበሏቸው በረከቶች ላይ ብቻ አልነበረም ፤ነገር ግን ለተቀሩት የእግዚያብሄር ልጆች በሚሆኑት በረከት ላይ እንጂ። “ለበረከት ትሆናለህ “ አለ እግዚያብሄር “ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ“(ኦሪት ዘፍጥረት 12፥2–3)።

እነዚህ ቃል ኪዳኖች ለአብርሃም፣ለሳራ እና ለትውልዳቸው ከእግዚያብሄር ልጆች መካከል ልዩ የመብት ደረጃ ሰጥቷቸው ነበር? ሌሎችን የመባረክ መብት ከመሆኑ አንጻር ብቻ ነው፡፡ የአብርሃም ቤተሰብ “በደህንነት በረከቶች እንዲሁም ለዘላለም ህይወት በሆኑት የወንጌል በረከቶችን “ በማካፈል “ይህንን አገልግሎት እና ክህነት ለሁሉም ህዝቦች ይዘው መሄድ“ ነበረባቸው፡፡(አብርሃም 2፥9, 11) የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝብ በመሆናቸው ከሌሎች የተሻሉ ነበሩ ማለት ሳይሆን ሌሎች የተሻሉ እንዲሆኑ የመርዳት ግዴታ አለባቸው ማለት ነው።

ይህ ቃል ኪዳን አብርሃም ሲጠብቀው የኖረው በረከት ነበር፡፡ ከተቀበለው በኋላ አብርሃም በልቡ “ አገልጋይህ በትኩረት ፈልጎህ ነበር አሁን አገኘሁህ“ አለ፡፡(አብርሃም 2፥12)

ያ የሆነው ከሺህ አመታት በፊት ነበር፤ ነገር ግን ይህ ቃልኪዳን በእኛ ዘመን ዳግም ተመልሷል። እናም በአሁኑ ጊዜ በእግዚያብሄር ህዝቦች ህይወት እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ የእግዚያብሄር ስራ በአለም ዙሪያ ያሉ ቤተሰቦችን እየባረከ እያደገ ሲሄድ በርግጥ የቃል ኪዳኑ ፍጻሜ በኋለኞቹ ቀናት እየተፋጠነ ነው፡፡ ማንም እንደአብርሃም ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን ቢፈልግ፣ ማንም ጌታን በትጋት ቢፈልግ የእዚህ አካል መሆን ይችላል፡፡

ቤተሰብ በቤተመቅደስ ፊት ለፊት

የአብርሃም ቃል ኪዳን ለእኔ ምን ማለት ነው?

እናንተ የቃል ኪዳኑ ልጆች ናችሁ። ስትጠመቁ እና ቅዱስ ቁርባን ስትካፈሉ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ትገባላችሁ። የቃል ኪዳኑን ሙላት ደግሞ ከቤተመቅደስ ቅዱስ ስርዓቶች ትቀበላላችሁ።

በእነዚህ ቃል ኪዳኖች እና ስርአቶች አማካኝነት የእግዚያብሄር ህዝቦች እንሆናለን፡፡ ከእርሱ ጋር “በዘላለም ትስስር” እንታሰራለን። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አስተምረዋል፣ “አንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ከገባን በኋላ ገለልተኝነትን ለዘለአለም እንተዋለን። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዲህ ያለውን ግንኙነት የፈጠሩትን አይተውም። በርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገቡ ልዩ የሆነ ፍቅር እና ምህረትን ማግኘት ይችላሉ። ከእግዚአብሔር ጋር በገባነው ቃል ኪዳን ምክንያት እኛን ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት አይታክትም እንዲሁም ለእኛ ያለውን የምሕረት ትዕግሥትም አንጨርሰውም። ይህንን በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ህዝብ ታሪክ ውስጥ እንዲሁም በራሳችሁ ህይወት እንደ አንድ የእርሱ የቃል ኪዳን ልጆች ታዩታላችሁ።

ኢየሱስ በውሃ ላይ እጁን ዘርግቶ ቆሞ

አትፍሩ፣ በዳን ዊልሰን

ይህ የአብርሃም ቃል ኪዳን በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ዳግም በመመለሱ ምክንያት ለእኛ የተሰጠን ውድ እውቀት ነው። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለቃል ኪዳን ስታነቡ እግዚያብሄር ከአብርሃም፣ከይስሃቅ እና ከያዕቆብ ጋር ብቻ ስለነበረው ግንኙነት አታስቡ፡፡ ከናንተ ጋር ስላለውም ግንኙነት አስቡ፡፡ እንደምድር አሸዋ ስለሚሆኑት ዘሮች ስታነቡ ዛሬ አብርሃምን አባታችን ስለሚሉት ስለሚልዮኖቹ ብቻ አታስቡ፡፡ በተጨማሪም እግዚያብሄር ለእናንተ የገባውን የዘላለማዊ ቤተሰብ እና የዘላለማዊ እድገት ቃልኪዳንን አስቡ። ስለውርስ ምድር ቃል ኪዳን ስታነቡ ለአብርሃም ቃል ኪዳን ስለተገባለት ምድር ብቻ አታስቡ፡፡ በተጨማሪም የምድርን ሰማያዊ እጣ ፈንታ አስቡ—“እግዚያብሄርን ተስፋ [ለ]ሚያደርጉ” “የዋሆች” ቃል የተገባውን ውርስ (ማቴዎስ 5:5መዝሙር 37:9፣ 11)። እናም የእግዚያብሄር የቃል ኪዳን ህዝቦች “የምድርን ቤተሰቦች ሁሉ“ (አብርሃም 2፥11) ይባርካሉ ስለሚለው ስታነቡ ስለአብርሃም አገልግሎት ወይም ከእርሱ የዘር ሃረግ ስለመጡት ነቢያት ብቻ አታስቡ፡፡ እንደኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተከታዮች—በዙሪያችሁ ላሉ ቤተሰቦች በረከት ለመሆን—ምን ልታደርጉ እንደምትችሉም አስቡ፡፡