ኑ፣ ተከተሉኝ
የካቲት 2–8 (እ.አ.አ)። ”ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው”፥ ሙሴ 7


የካቲት 2–8 (እ.አ.አ)። ‘ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው’፥ ሙሴ 7 ፣”ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)

የካቲት 2–8 (እ.አ.አ)። ”ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው”፥ ኑ፣ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)

ሄኖክ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ እያየ

Enoch Sees the Meridian of Time, በጄኒፈር ጋጄት

የካቲት 2–8 (እ.አ.አ)፥ ”ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው”

ሙሴ 7

በመላው ታሪክ ውስጥ ሰዎች ሄኖክ እና ህዝቡ የደረሱበት ላይ ለመድረስ ሞክረዋል: ችግር እና ብጥብጥ የሌለበት በጣም ጥሩ ማህበረሰብ፡፡ እንደ እግዚያብሄር ህዝብ ይህንን ፍላጎት እንጋራለን፡፡ እርሱን ጽዮንን መገንባት ብለን እንጠራዋለን—ድሆችን ከመንከባከብ እና ሰላምን ከማራመድ በተጨማሪ—ቃልኪዳን መግባትን፣ በጽድቅ አብሮ መኖርን እና እርስ በርሳችን እና “ከጽዮን ንጉስ” ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን ያካትታል (ሙሴ 7፥53)፡፡ ዓለም፣ ማኅበረሰባችሁ ወይም ቤተሰባችሁ እንደምትፈልጉት ካልሆነ፣ ሄኖክና ሕዝቡ ይህን እንዴት ማድረግ ቻሉ ብሎ መጠየቁ ጠቃሚ ነው። ዙሪያቸው በሁከት የተሞላ ቢሆንም “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ“(ሙሴ 7፥18) እንዴት ሆኑ? ሙሴ 7 ስለጽዮን ከሚሰጠን ብዙ ዝርዝሮች መካከል ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን በተለይ ጠቃሚ የሆነው ይህ ሊሆን ይችላል: ጽዮን ከተማ ብቻ አይደለችም—የልብ እና የአዕምሮ ሁኔታ ነች፡፡ ጌታ እንዳስተማረው ጽዮን “ልበ ንጹህ“ ናት (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 97፥21)፡፡ ስለዚህ ምናልባት ጽዮንን ለመገንባት ከሁሉም የተሻለው መንገድ በራሳችን ልብ እና ቤት ውስጥ መጀመር ነው፡፡

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሙሴ 7፥16–21፣ 27፣ 53፣ 62–69

የሴሚናሪ ምልክት
ጽዮንን ለመገንባት መርዳት እችላለሁ።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ሄኖክ እና ስለ ቅድሱ ከተማው ለመጀመሪያ ጊዜ ባወቀ ጊዜ ተነሳስቱ ነበር። “እግዚአብሔር ጽዮንን በምድር ላይ የሚመሠርትበት ቀን እንደ ደረሰ አወቀ” (Saints1፡108–9) እንዲሁም ጽዮንን ለመገንባት የዕድሜ ልክ ጥረትን ጀመረ። ሙሴን 7 ማንበብ ጥረቱን ዛሬም እንድትቀጥሉ ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

“ጽዮን ምንድናት?” እና “ከሌላው አለም የምትለየው እንዴት ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች በመመርመር መጀመር ትችላላችሁ። ሙሴን 7ን በተለይም ቁጥር 16–21፣ 27፣ 53፣ 62–69 ስታጠኑ ወደ እናንተ የሚመጡ መልሶችን ለመዘርዘር አስቡ።

ለእነዚህ ጥያቄዎች የምትሰጧቸው መልሶች ጽዮንን ለመገንባት ገና ብዙ ሥራ እንደሚጠብቀን ግልጽ ሊያደርግልን ይችላል። ታዲያ ያንን እንዴት ማድረግ እንችላለን? ከአንድ ሰው ጋር “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ” እንደሆናችሁ የተሰማችሁን ጊዜ ማሰብ ሊረዳችሁ ይችላል (ሙሴ 7፡18)። ምናልባት በቅርንጫፍ፣ በቤተሰብ ወይም በቡድን ስራ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ሊሆን ይችላል። ሰዎች የጽድቅ አንድነትን ለመፍጠር ምን አደረጉ?

ሃሳቦችን እና መነሳሳትን ለማግኘት ማሰስ የምትችሏቸው አንዳንድ ሌሎች ግብዓቶች እነዚህ ናቸው። ለማጥናት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን ምረጡ እና ጽዮንን ለመገንባት ያነሳሳችሁን ፃፉ፡

በቡድን ክፍል ውስጥ ጓደኛሞች አንዳቸው ሌላውን እያጽናኑ

እግዚአብሔር ሕዝቡ “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ “ እንዲሆን ይፈልጋል (ሙሴ 7፥18)፡፡

ሙሴ 7:53

ኢየሱስ ክርስቶስ “የጽዮን ንጉሥ” ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሳችሁ መሆኑ ለእናንተ ምን ማለት ነው? በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያሉትን የኢየሱስ ክርስቶስን ሌሎች የማዕረግ ስሞች ተመልከቱ። ስለ እርሱ ምን ያስተምሯችኋል? “በበሩ ገብተው ወደ [እርሱ] የሚወጡት” ሲባል ምን ማለት ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

በተጨማሪም “Come, O Thou King of Kings፣” መዝሙሮች፣ ቁ. 59. ይመልከቱ።

ሙሴ 7፥28–69

እግዚአብሔር ስለልጆቹ—ያነባል—ደስም ይለዋል።

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሄር በእኛ ላይ የሚሆነው ነገር ስሜታዊ ተጽዕኖ እንደማያሳድርበት እሩቅ አካል አድርገው ያዩታል፡፡ በሙሴ 7 ላይ ከተጻፈው ራእይ ሄኖክ ስለ እግዚአብሔር የተለየ እይታን አግኝቷል። በቁጥር 28-40 ስለ እግዚአብሔር ምን ተማረ—እናንተስ ምን ተማራችሁ? ሄኖክ እግዚአብሔር ሲያነባ አይቶ የተገረመው ለምን ይመስላችኋል? እርሱ ይህን እንደሚያደርግ ማወቃችሁ ለእናንተ ለምን የሚያስፈልግ ይመስላችኋል?

ራእዩ ሲቀጥል ሄኖክም እንዳነባ እናያለን። እግዚአብሔር ግን እሱ ደስ ሊሰኝ የሚችልበትን ምክንያት ነግሮታል። በሙሴ 7፡41–69 ፈልጓቸው። በህይወታችሁ ውስጥ “[ምሬት]” ቢሰማችሁም “[ልባችሁን እናድታነሱ እና እንድትደሰቱ]” የሚረዳችሁን ከሄኖክ ራእይ ምን ተማራችሁ (ቁጥር 44)?

በተጨማሪም ዮሐንስ 17፤ ጄፍሪ አር. ሆላንድ “The Grandeur of God፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2003 (እ.አ.አ)፣ 70–73 ይመልከቱ።

ሙሴ 7፥59–67

ኢየሱስ ክርስቶስ በኋላኛው ቀን ዳግም ይመጣል።

የሄኖክ ራዕይ፣ በተለይም በሙሴ 7፡59–67 ላይ የተመዘገበው፣ ስለ አዳኙ ምጽአት በታሪክ የመጀመሪያ ከሆኑ ትንቢቶች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ ጥቅሶች የኋላኛውን ቀን ስለሚገልጹበት መንገድ የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው? ለምሳሌ፣ በቁጥር 62 ላይ ያሉት ትንቢቶች እየተፈጸሙ ስለመሆናቸው የሚሰማችሁን አስቡ። እነዚህ ሃረጎች ስለኋለኛው ቀናት የእግዚአብሔር ሥራ ምን ያስተምሯችኋል?

በተጨማሪም ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Sisters in Zion,” ሊያሆና፣ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 67–69 ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሙሴ 7፥16–21፣ 62–63፣ 68–69

እግዚያብሄር “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ“ እንድንሆን ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ ስለ ሄኖክ እና ጽዮን እንዲማሩ ለመርዳት በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች (19-21) ላይ “ነቢዩ ሄኖክ” ወይም “Follow the Prophet” (Children’s Songbook፣ 110–11) ሁለተኛውን አዝማች መጠቀም ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ ታሪኩን በራሳቸው አገላለጽ እንደገና እንድትናገሩ እንዲረዷችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉት የሄኖክ ሥዕሎች ሊረዱ ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ “አንድ ልብና አንድ አእምሮ” (ሙሴ 7፡18) ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ የምታግዙበት አንዱ መንገድ እዚህ ይገኛል፡ ለእያንዳንዱ ልጅ ከወረቀት ላይ የልብ ቅርጽ ቆርጣችሁ በማውጣት ስጡ። በወረቀታቸው ላይ ስማቸውን እንዲጽፉ እና ልቦቹን አንድ ላይ እንዲያያይዙ በአንድነት ይስሩ። ይህን በሚያደርጉ ጊዜ፣ ስለእያንዳንዱ ልጅ የምትወዱትን ነገሮች ማውራት ትችላላችሁ።

እናት ልጇን አቅፋ
  • ሙሴ 7፡18–21፣ 62–63፣ 68–69 ላይ “ጽዮን” የሚለው ቃል ስንት ጊዜ እንደተገለጸ ልጆቻችሁ እንዲቆጥሩ እርዷቸው። ቃሉን ባገኙ ቁጥር ጥቅሱ ስለ ጽዮን የሚናገረውን እንዲያውቁ አግዟቸው (በተጨማሪም የቅዱሳን ጽሑሃፍት መመሪያ፣ “ጽዮን”፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዳሉት ሰዎች ይበልጥ እንዴት መሆን እንችላለን?

የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን አበረታቱ። ቤተሰባችሁን በቤት እያስተማራችሁ ሆነ በእሁድ ቀን በክፍል፣ ሌሎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ዘላቂ እምነት እንዲገነቡ ከምትረዱበት ምርጥ መንገዶች መካከል አንዱ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር የግል ልምዶችን የመፈለግ ልማድ እንዲኖራቸው መርዳት ነው። ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ያላችሁን ተሞክሮዎች አካፍሉ እንዲሁም ቤተሰብ ወይም የክፍል አባላት ልምዳቸውን እንዲካፈሉ አበረታቷቸው። ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ እንዴት ሌሎችን እየባረከ እንደሆነ ስንሰማ፣ ብዙ ጊዜ እነዚህን ተመሳሳይ በረከቶች ከጌታ እንድንፈልግ እንነሳሳለን። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር25ን ይመልከቱ።)

ሙሴ 7:32–33

የሰማይ አባት እርሱን ለመከተል እንድመርጥ ይፈልጋል።

  • ሙሴ 7፡32–33ን ለልጆቻችሁ ለማስተዋወቅ፣ በቅርቡ ማድረግ ስለነበረባቸው ምርጫ ልታናግሯቸው ትችላላችሁ። ከዚያም የሰማይ አባት እንድንመርጥ የሚፈልገውን ለማወቅ ጥቅሶቹን በአንድነት ማንበብ ትችላላችሁ። እርሱን እንደምንመርጥ ለማሳየት ምን ምርጫዎችን ማድረግ እንችላለን? ምናልባት ልጆቻችሁ ከእነዚህ ምርጫዎች ውስጥ አንዱን በምልክት ሊያሳዩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ድርጊቱ ምን እንደሚወክል ሊገምቱ ይችላሉ።

ሙሴ 7፥59–67

ኢየሱስ ወደ ምድር ተመልሶ ይመጣል።

  • ሙሴ 7፡59 ሄኖክ ጌታን አንድ ጥያቄ ጠይቆት ነበር። ልጆቻችሁን እንዲያገኟቸው ጋብዟቸው እንዲሁም መልሱን ቁጥር 60 ላይ እንዲያገኙ ጠይቋቸው። በተጨማሪም አንድ ሰው ወደ ቤት እስኪመለስ ጠብቀው ስለነበረበት ጊዜ ከእነሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ። ምን እንደተሰማቸው እና ለመዘጋጀት ምን እንዳደረጉ ጠይቋቸው። ለኢየሱስ ምጽአት እንዴት መዘጋጀት እንችላለን?

  • አዳኙ ለሰዎች የተገለጠበትን ጊዜ (እንደ የወንጌል አርት መጽሐፍቁጥር 608283፣ እና 84 ያሉትን) ምስሎችን ለማሳየት አስቡ። በምስሎቹ ላይ ሰዎች ምን እያደረጉ ነው? ኢየሱስን ሲያገኙት ሰዎቹ ምን ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል? እንዲሁም ስለ አዳኙ ምጽአት ለምሳሌ “When He Comes Again” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 82–83) የመሰሉ መዝሙሮችን ዘምሩ፣ ልጆቻችሁ ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ምን ሊመስል እንደሚችል ያላቸውን ሃሳብ ጠይቋቸው። ልጆች ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ማየት ምን አይነት ስሜት ሊያሳድርባቸው እንደሚችል እንዲያካፍሉ አድርጓቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ሄኖክ እና የጽዮን ከተማ ሰዎች ሲለወጡ

የጽዮን ከተማ ተለውጣ፣ በዴል ፓርሰን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ እግዚአብሔር እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ይፈልጋል