ኑ፣ ተከተሉኝ
ጥር 26–የካቲት 1 (እ.አ.አ) “እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር“፥ ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6


“ጥር 26–የካቲት 1 (እ.አ.አ) ‘እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር’፥ ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6”ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 ( እ.አ.አ)]

“ጥር 26–የካቲት 1 (እ.አ.አ) ‘እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር’፥ ” ኑ፣ ተከተሉኝ: 2026 (እ.አ.አ)

አዳም እና ሔዋን

ከገነት የተሻለ፣ በኬንዳል ሬይ ጆንሰን

ጥር 26–የካቲት 1 (እ.አ.አ)፥ “እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር“

ኦሪት ዘፍጥረት 5ሙሴ 6

አብዛኛው ዘፍጥረት 5 ከአዳም እና ሄዋን እስከ ኖህ ያሉት የትውልዶች ዝርዝር ነው፡፡ ብዙ ስሞችን እናነባለን ነገር ግን ስለእነርሱ ብዙ አንማርም፡፡ ከዚያም ይህን ትኩረት የሚስብ ነገር ግን ያልተብራራ ጥቅስ እናነባለን፡ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚያብሄር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚያብሄር ወስዶታልና“ (ዘፍጥረት 5፥24)፡፡ በርግጠኝነት ከዚያ ጥቅስ ጀርባ አንድ ታሪክ አለ፡፡ ነገር ግን ያለምንም ማብራሪያ የትውልዶች ዝርዝሩ ካቆመበት ይቀጥላል፡፡

በሚያስደስት ሁኔታ፣ ሙሴ 6 የሄኖክን ታሪክ በዝርዝር ይገልጻል—እናም ትልቅ ታሪክ ነው፡፡ ስለሄኖክ ትህትና፣ ስጋቶች፣ እግዚያብሄር በውስጡ ስላየው አቅም እና እንደ እግዚአብሄር ነብይ ስለሰራው ታላቅ ስራ እንማራለን፡፡ በትውልዶች እያደገ ሲሄድም ስለአዳም እና ሄዋን ቤተሰብ ጠራ ያለ ምስል እናገኛለን፡፡ ስለ ሰይጣን “ታላቅ ስልጣን” እናነባለን ነገር ግን ልጆችን “የእግዚአብሔርን መንገድ”(ሙሴ 6፡15፣ 21) ስለሚያስተምሩ ወላጆችም እናነባለን። በተለይም እነዚህ ወላጆች ያስተማሩት ትምህርት የከበረ ነው፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፣ ንስሃ መግባት፣ ጥምቀት እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል (ሙሴ 6፥50–52ን ይመልከቱ)፡፡ ያ ትምህርት አብሮት ካለው ክህነት ጋር “በመጀመሪያ ነበረ [እናም] እስከ አለም መጨረሻም ይኖራል“ (ሙሴ 6:7)።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሙሴ 6፥26–36

ሃጢያት የእግዚአብሄርን ነገር እንዳይሰማኝ፣ እንዳላይ እና እንዳልሰማ ያደርገኛል።

ሙሴ 6፥26–36ን ስታጠኑ፣ ስለሚያስከትላቸው ውጤቶች ምን ተማራችሁ? እነዚህን ውጤቶች እንዴት አያችሁ? ሄኖክ እነዚህን ውጤቶች እንዲያሸንፍ ያገዙት የትኞቹ ባሕርያት ነበሩት? በዚህም ምክንያት እግዚአብሄር እንዴት ባረከው?

ሙሴ 8፥26–47

የሴሚናሪ ምልክት
ጉድለቶች ቢኖሩብኝም እግዚያብሄር ስራውን እንድንሰራ ይጠራኛል።

ጌታ እንድትሰሩ በጠራችሁ ነገር ከተጨነቃችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም። ጌታ ነቢይ እንዲሆን በጠራው ጊዜ ሄኖክም እንደዛ ተሰምቶት ነበር። ሙሴ 6፥26–36፣ ን ስታነቡ ኢዮብ ለምን የመጨነቅ ስሜት እንደተሰማው እና ጉብዝና እንዲሰማው ጌታ ምን እንዳለው ፈልጉ።

ቁጥር 37–47 ውስጥ ጌታ ሄኖክን የረዳበትን እና ስራውን እንዲሰራ ሃይል የሰጠበትን መንገዶች መፈለግ ትችላላችሁ (በተጨማሪም ሙሴ 7፥13ን ይመልከቱ)። የሄኖክን ተሞክሮዎች እንደሙሴ ( ዘጸአት 4፥10–16ን ይመልከቱ)፣ ኤርሚያስ ( ትንቢተ ኤርሚያስ 1፥4–10ን ይመልከቱ)፣ ኔፊ ( 2 ኔፊ 33፥1–4ን ይመልከቱ)፣ እና ሞሮኒ ( ኤተር 12፥23–29ን ይመልከቱ)ካሉ ብቃት እንደሌላቸው ከተሰማቸው ከሌሎች ነቢያት ጋር ልታነጻጽሩ ትችላላችሁ። ከነዚህ ቅዱሳን ጽሁፎች እግዚያብሄር እንድትሰሩት ስለሰጣችሁ ስራ ምን እንድትማሩ የሚፈልግ ሆኖ ይሰማችኋል?

ሄኖክ እየጸለየ

ጌታ ባለራእይ አስነስቷል (ሙሴ 6፡36)፣ በኢቫ ቲሞቲ

ብዙ የዘመናችን ሐዋርያት እና ነቢያት ጥሪያቸውን ሲቀበሉ የተሰማቸው ስሜት ሄኖክ ከተሰማው ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ ገልጸዋል። ለምሳሌ፣ “Prophets Speak by the Power of the Holy Spirit (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018፣ 98–99) ውስጥ የሽማግሌ ዩሊሰስ ሶሬስን ምስክርነት ተመልከቱ።

ከእነዚህ ነቢያትና ሐዋርያት ስለ እናንተ ብቁ ያለመሆን ስሜት ምን ትማራላችሁ? ከባድ ነገሮችን እንድታደርጉ ሲጠይቃችሁ የአዳኙ እርዳታ የተሰማችሁ መቼ ነው? ወደፊት በአዳኙ እርዳታ መታመን ሊያስፈልጋችሁ የሚችልበትን ጊዜ ጥቂት ሁኔታዎችን መጻፍን አስቡ። እነዚህን ሁኔታዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መጋፈጥ የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር “Abide in Me, and I in You; Therefore Walk with Me,ሊያሆና 2023 (እ.አ.አ)፣ 123–25 ይመልከቱ፤ “I’ll Go Where You Want Me to Go,” መዝሙሮች ቁ.270።

ሙሴ 6፥48–68

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ተሰብኳል።

የሙሴ መጽሃፍ ስላለን እግዚያብሄር ልጆቹን ከመጀመሪያው ጀምሮ ደህንነትን እንዴት እንደሚያገኙ ሲያስተምር እንደነበረ እናውቃለን። ሙሴ 6፥48–68ን ስታጠኑ፣ ለመቤዠት ምን ማወቅ እና ማድረግ እንዳለብን ፈልጉ? በክፍል 53 ላይ ያለውን የአዳምን ጥያቄ አስተውሉ። ይህን አስባችሁ ታውቃላችሁ? በቁጥር 53–65 ካለው የጌታ መልስ ምን ተማራችሁ? እነዚህን ጥቅሶች በአዳም የጥምቀት አገልግሎት ላይ እንደ ጌታ መልእክት አድርጋችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ። ከመልእክቱ ስለ ጥምቀት ምን ትማራላችሁ? ጥምቀትን “በድጋሚ [ከ]መወለድ” (ቁጥር 59) ጋር ያነጻጸረው ለምን ይመስላችኋል? በህይወታችሁ ሙሉ “በድጋሚ መወለድ” እንድትቀጥሉ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ምልክቶችን ፈልጉ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ ቁሶች ወይም ክስተቶች መንፈሳዊ እውነቶችን በተለይም ስለ አዳኙ እውነት ሊወክሉ ወይም ሊያመለክቱ ይችላሉ በአዳኙ መንገድ ማስተማር7)። እነዚህ ምልክቶች ስለ እሱ እና ስለ ትምህርቱ ያላችሁን ግንዛቤ ሊያበለጽጉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ በሙሴ 6፡27 ካለው የልብ እና የጆሮ፣ በሙሴ 6፡35 ውስጥ ካለው የዓይን እና የሸክላ ወይም በሙሴ 6፡59-60 ውስጥ ካለው የውሃ ምልክት ምን ትማራላችሁ?

ሙሴ 6፥51–62

“እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር።“

ሙሴ 6፡51-63 ላይ ጌታ አዳምን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እውነት ካስተማረ በኋላ ለቀጣይ ትውልድ እንዲያስተምር ነገረው። የእነዚህን እውነቶች ዝርዝር ማዘጋጀትን አስቡ። (ጽሁፉን ወደ ትንንሽ ቁጥሮች መከፋፈል ሊረዳችሁ ይችላል፣ ለምሳሌ ቁጥር 51–5253–5758–6061–63)። ዛሬ በማደግ ላይ ላለው ትውልድ እነዚህ እውነቶች ጠቃሚ የሚሆኑት ለምንድን ነው? በሞዛያ 4፡14–15 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፡25–2893፡40–50 ከጌታ ለወላጆች ከሰጠው መመሪያ ሌላ ምን መማር ትችላላችሁ?

የአዳም እና ሄዋን ቤተሰብ ያዘጋጀውን “የመታሰቢያ መጽሃፍ“ ማንበብ የራሳችሁን ወይም የቤተሰባችሁን የመታሰቢያ መጽሃፍ እንድታዘጋጁ ሊያነሳሳ ይችላል። ጌታ ምን እንድታካትቱ የሚፈልግ መስሎ ይሰማችኋል? ከመታሰቢያ መጽሃፋችሁ መረጃዎችን ወደ FamilySearch.orgለማከል አስቡ።

በተጨማሪም ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍን፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የወላጆች ብርታት ነው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 55-59፤ “Parenting: Touching the Hearts of Our Youth,” “But Why?” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን በአንድ ላይ እያነበቡ

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሙሴ 6:26–34

እግዚአብሔር ከባድ ነገሮችን እንዳደርግ ሊረዳኝ ይችላል።

  • ሄኖክ ወንጌልን ለመስበክ በተጠራበት ጊዜ ሳይሳካለት እንዳይቀር ሰግቶ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ረዳው። ይህንን ታሪክ በአንድነት በሙሴ 6፡26–34 ውስጥ አንብቡ (በተጨማሪም “ነቢዩ ሄኖክ” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 19–21 ይመልከቱ)። ሄኖክ ወንጌልን መስበክ እንደማይችል ሆኖ የተሰማው ለምንድን ነው? (ሙሴ 6፡31 ይመልከቱ)። እግዚአብሔር ሄኖክን የረዳው እንዴት ነው? (ሙሴ 6:32–347:13 ይመልከቱ)።

  • ልጆቻችሁ ሰዎች አስቸጋሪ ነገሮችን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር የረዳቸውን ሌሎች ምሳሌዎችን በማካፈል ወይም በመተወን ሊደሰቱ ይችላሉ—ለምሳሌ ኖኅ፣ ዳዊት፣ አሞን፣ ወይም ላማናዊው ሳሙኤል (የወንጌል አርት መጽሐፍቁ. 71978፣ 81)። በተጨማሪም የራሳችሁን ተሞክሮ ማካፈል እና ልጆቻችሁ ከባድ ነገሮችን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚረዳቸው እንዲናገሩ ማድረግ ትችላላችሁ።

ሙሴ 6፥50–62

በክርስቶስ ማመን፣ ንስሃ መግባት፣ መጠመቅ እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ወደ እግዚአብሔር እንድመለስ ያዘጋጀኛል።

  • እግዚአብሔር ወደ እርሱ ለመመለስ ምን ማድረግ እንዳለብን አዳምን አስተምሮታል—በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፣ ንስሀ መግባት፣ መጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል። ልጆቻችሁ በሙሴ 6፡52፣ 57 ውስጥ እነዚህን መርሆች እንዲያገኙ እርዷቸው። ከዚያም ስለ አንዱ መርህ አጭር ንግግር እንዲጽፉ መርዳት ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ንግግር የሙሴ 6ን ጥቅስ፣ ልምድ እና ምስክርነት ሊያካትት ይችላል። ንግግራቸውን አንዳቸው ለሌላው ያካፍሉ።

  • እንዲሁም የመጀመሪያ የወንጌል መርሆችን የሚወክሉ ሥዕሎችን ማሳየት ትችላላችሁ (አራተኛ የእምነት አንቀጽ ይመልከቱ)። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል በሚወስድ መስመር ላይ አስቀምጧቸው። ሙሴ 6:52ን ስታነቡ ልጆቻችሁ ሥዕሉን የሚወክሉትን ቃላት ሲሰሙ ከሚዛመደው ሥዕል አጠገብ መቆም ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ በሙሴ 6፡52 ውስጥ ያሉትን መርሆችን የሚያስተምሩ እንደ “Faith [እምነት],” “When I Am Baptized,” እና “The Holy Ghost” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 96–97፣ 103፣ 105) ያሉ መዝሙሮችን በመዘመር ሊደሰቱ ይችላሉ። በሙሴ 6፡52 ውስጥ እነዚህን መርሆች እንዲያገኙ እርዷቸው።

ሙሴ 8፥57–58

የሰማይ አባት ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ የወንጌል አስተማሪዎች የሆኑትን ወላጆቻቸውን እንዲደግፉ ለማበረታታት፣ አንድ ልጅ ሙሴ 6፡58 እንዲያነብ እና እግዚአብሔር ለወላጆች የሰጠውን ትዕዛዝ እንዲለዪ ጠይቁ። ከዚያም አዳምና ሔዋን ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ የሚያሳይ ሥዕል (በዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ እንዳለው) በማስየት ልጆቻችሁ በሥዕሉ ላይ ስለሚያዩት ነገር እንዲናገሩ ማድረግ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው ቅዱሳት መጻህፍት ሲያነቡ፣ ሲጸልዩ ወይም ሲጫወቱ የሚያሳይ ስዕል መሳል ይችላሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

አዳምና ሔዋን ልጆቻቸውን ከዛፍ ሥር እያስተማሩ

አዳም እና ሔዋን ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ፣ በዴል ፓርሰን

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ የሰማይ አባት እንዴት መመለስ እንዳለብኝ ያስተምረኛል