ኑ፣ ተከተሉኝ
ጥር 19–25 (እ.አ.አ)። የአዳም እና ሔዋን ውድቀት፥ ዘፍጥረት 3–4፤ ሙሴ 4–5


“ጥር 19–25 (እ.አ.አ)። የአዳም እና ሔዋን ውድቀት፥ ዘፍጥረት 3–4፤ ሙሴ 4–5፥ “.ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ጥር 19–25 (እ.አ.አ)። የአዳም እና ሔዋን ውድቀት፥ “ኑ፣ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)

አዳም እና ሔዋን

አዳም እና ሔዋን፣ በዳግላስ ኤም. ፍራየር

ጥር 19–25 (እ.አ.አ)፤ የአዳም እና ሔዋን ውድቀት

ኦሪት ዘፍጥረት 3-4ሙሴ 4–5

በመጀመሪያ የአዳም እና ሄዋን የውድቀት ታሪክ አሳዛኝ ሊመስል ይችላል፡፡ አዳም እና ሄዋን ከሚያምረው የኤደን የአትክልት ስፍራ ተባርረው ነበር፡፡ ህመም፣ ሃዘን እና ሞት ወዳለበት አለም ተባረሩ (ዘፍጥረት 3፥16–19ይመልከቱ)። እንዲሁም ከሰማያዊ አባታቸው ተለዩ። ነገር ግን በሙሴ መጽሃፍ የሚገኘው በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት የተመለሰው እውነት ስለ ውድቀት የተለየ እይታ ይሰጠናል።

በእርግጥ፣ የኤደን የአትክልት ስፍራ ያማረ ነበር። ነገር ግን አዳም እና ሄዋን ካማረ አካባቢ የበለጠ ነገር ያስፈልጋቸው ነበር። እኛ ሁላችንም እንደሚያስፈልገን ሁሉ የማደግ እድል አስፈልጓቸው ነበር። የኤደንን የአትክልት ስፍራ ለቆ መውጣት ወደ እግዚያብሄር ለመመለስ እና በመጨረሻም እንደ እርሱ ለመሆን አስፈላጊው የመጀመሪያ እርምጃ ነበር። ያም ማለት ተቃውሞን መጋፈጥ፣ ስህተትን መስራት፣ ንስሃ መግባትን መማር እና እድገትን እና “የመዳናቸችንን ደስታ“ (ሙሴ 5፥11) የሚቻል የሚያደርገውን የአዳኙን የሃጥያት ክፍያ ማመን ማለት ነበር። ስለዚህ ስለአዳም እና ሄዋን ውድቀት በምታስቡበት ጊዜ አሳዛኝ በሚመስለው ኩነት ላይ አታተኩሩ ነገር ግን በከፈታቸው እድሎች ላይ አተኩሩ—ትኩረታችሁን አዳም እና ሄዋን ባጡት ገነት ላይ ሳይሆን ምርጫቸው እንድንቀበል በፈቀደልን ክብር ላይ አድርጉ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ዘፍጥረት 3ሙሴ 4

ውድቀት የእግዚአብሔር እቅድ አስፈላጊ አካል ነበር።

የአዳም እና ሔዋን ምርጫ በምድራዊ ህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ብዙ ችግሮች ማስከተሉ እውነት ነው። ነገር ግን በምርጫቸው እንቆጫለን ማለት አይደለም። ዘፍጥረት 3 እና ሙሴ 4ን ስታነቡ፣ ውድቀት ለእግዚአብሔር እቅድ ለምን አስፈገ? በማለት ራስችሁን ትጠይቁ ይሆናል።

ሙሴ 5፡9-12 መሠረት አዳምና ሔዋን ስለ ውድቀት ምን ተሰምቷቸው ነበር? ቃላቶቻቸውን በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ ባላችሁ ልምድ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ? ከ2 ኔፊ 2፡19–25 ሌላ ምን ተማራችሁ?

በተጨማሪም ሞዛያ 3:19አልማ 12:21–37 እና ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 29:39–43ይመልከቱ።

ሔዋን ፖም ይዛ

ኤደንን ለቆ መሄድ በአኒ ሄንሪ ናደር

ዘፍጥረት 3፥1-7ሙሴ 4:22–315:4–15

ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋን እና ቤዛነትን ይሰጣል።

የአዳም እና ሔዋን ታሪክ በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ የተስፋ እና የቤዛነት ታሪክ ነው። ምክንያቱን ለመረዳት በዘፍጥረት 3፡1-7ሙሴ 4፡22-31 ላይ ውድቀት ያስከተለውን በመፈለግ መጀመር ትችላላችሁ እንዲሁም ያገኛችሁት ላይ ምልክት አድርጉ ወይም ዝርዝር አውጡ። እነዚህ ውጤቶች በእናንተ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራሉ? ከዚያም ሙሴ 5፡4-15ን ስታነቡ ከእነዚህ ውጤቶች እኛን ለማዳን እግዚአብሔር የነበረውን እቅድ ፈልጉ። አዳምና ሔዋን መልአኩ ከጎበኛቸው በኋላ “ደስተኛ” የሆኑት ለምንድነው? ስለ ሰማይ አባት እቅድ ከእነሱ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም “Because of Him” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

2:44

Because of Him

ኦሪት ዘፍጥረት 3፥16; ሙሴ 4፥22

አዳም በሄዋን ላይ “ገዥ“ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?

ይህ የቅዱስ ጽሁፍ ምንባብ አንዳንድ ጊዜ አንድ ባል ሚስቱን ደግነት በጎደለው ሁኔታ ቢይዝ ተገቢ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ሲወሰድበት ቆይቷል። በእኛ ጊዜ፣ የጌታ ነቢያት ባል እና ሚስት በቤተሰብ ውስጥ ያላቸውን መለኮታዊ ሀላፊነት ለመወጣት እርስ በርሳቸው እንደ እኩል አጋሮች መተያየት እንዳለባቸው አስተምረዋል (ቤተሰብ: ለአለም የተላለፈ አዋጅ” [የወንጌል ላይብረሪ] ይመልከቱ)። ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንላንድ እና እህት ሩት ላይበርት ረንላንድ ጻድቅ ባል “ማገልገል ይሻል፤፤ስህተቶችን ይቀበላል እንዲሁም ይቅርታን ይሻል፤ምስጋና ለማቅረብ ፈጣን ነው፤የቤተሰብ አባላት ምርጫዎችን ከግምት የሚያስገባ ይሆናል፤ለህይወት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማቅረብ እና ቤተሰቡን ለመጠበቅ ታላቅ የሃላፊነት ሸክም ይሰማዋል፤ሚስቱን በከፍተኛ ክብር እና ትህትና ይይዛታል። … ቤተሰቡን ይባርካል”(የመልከጼዴቅ የክህነት ስልጣን: ትምህርቱን መገንዘብ፣ መርሆዎቹን መኖር [2018(እ.አ.አ)]፣ 23)።

ሙሴ 4፥1–4

የሴሚናሪ ምልክት
ለማደግ የመምረጥ ነጻነት እና ተቃውሞ ያስፈልገኛል።

ሽማግሌ ዴል ጂ. ሬንሉድ “የሰማዩ አባታችን የወላጅነት አላማው ልጆቹ ትክክለኛውን ነገር እንዲያደርጉ ማድረግ አይደለም፤ ይልቁንስ የእርሱ ልጆች ትክክለኛውን ነገሮች እንዲመርጡ ማድረግ ነው” በማለት አስተምረዋል። (ዴል ጄ. ረንለንድ “Choose You This Day [ይህንን ቀን ምረጡ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018፣ (እ.አ.አ) 104) በሰማይ አባት እቅድ ውስጥ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ መምረጣችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

ሙሴ 4፡1–4ን ስታነቡ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የመምረጥ መብታችሁን—ነጻ ምርጫችሁን ለመጠበቅ ያደረጉትን ፈልጉ። የእነሱን የጥበቃ ኃይል እንዴት ማግኘት ትችላላችሁ? ሃሳብ ለማግኘት “Make inspired choices” የሚለውን በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን ለማድረግ መመሪያ (4-5።) ማጥናት ትችላላችሁ።

በተጨማሪ በ2 ኔፊ 2፡11–20፣ 25–30 ላይ ሌሂ ስለ ነጻ ምርጫ ያስተማረውን ለማንበብ አስቡ። ለነጻ ምርጫ ተቃውሞ የሚያስፈልገው ለምንድነው? ኢየሱስ ክርስቶስ “ለመምረጥ… ነፃ” ስላደረጋችሁ አድናቆታችሁን ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው? (2 ኔፊ 2፥27)።

በተጨማሪም ዳለን ኤች. አኦክስ፣ “Opposition in All Things፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 114-17፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Agency,” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Choose the Right,” መዝሙሮች፣ ቁ. 239።

ተሳትፎን ጨምሩ። ብዙ የመማርያ አክቲቪቲዎች እንደ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ ክፍል ወይም በትናንሽ ቡድኖች፤ ወይም ጥንድ ጥንድ በመሆን ሊደረጉ ይችላሉ። እድል ላይኖራቸው የሚችሉ ሰዎች እንዲሳተፉ ለማስቻል የተለያዩ መንገዶችን ተጠቀሙ። ለዚህ ተግባር አንድ ሰው ወይም ቡድን ሙሴ 4ን እና ለወጣቶች ጥንካሬ መመሪያን ሲያነብ ሌላው ቡድን ደግሞ በ2 ኔፊ 2 ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች ያጥና። ከዚያም በየክፍሉ የተማሩትን እርስ በርስ መማማር ይችላሉ።

ሙሴ 4:4–125:13–33

ሰይጣን እኔን “[ለማታለልና እናዳላይ ሊያደርግ]” ይፈልጋል።

ሙሴ 4፡4–125፡13–33ን ስታነቡ ሰይጣን አዳምና ሔዋንን እንዲሁም ልጆቻቸውን ሊፈትናቸው የሞከረባቸውን መንገዶች ለመዘርዘር አስቡ። ዛሬም እነዚህን ተመሳሳይ ነገሮች የሚሞክረው እንዴት ነው? የሰማይ አባት የሰይጣንን ማታለያዎች እንድትቋቋሙ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

ሙሴ 4:13–16፣ 27

“እኔ፣ እግዚአብሄር አምላክ… አለበስኳቸው።”

አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላ ራቁታቸውን ለመሸፈን ሞክረዋል። በኋላ ላይ፣ ጌታ አለበሳቸው። ሙሴ 4:13–16፣ 27ን ስታነቡ የሚከተለውን አስቡ።

  • በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ታቁት መሆን እና ልብስ ምን ሊወክሉ እንደሚችሉ አስቡ (ለምሳሌ፣ ራዕይ 7፡9፣ 13–152 ኔፊ 9፡14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፡22–26፣ 76 ይመልከቱ)። አዳምና ሔዋን ከራቁትነት እና ከመልበስ ጋር ካጋጠማቸው ነገር ምን ትማራላችሁ?

  • የቤተመቅደስ ቡራኬ ተቀብላችሁ ከሆነ አዳምና ሔዋን ስለ ቤተ መቅደስ ልብሳችሁ አስፈላጊነትና ስለሚወክሉት ነገር ምን ሊሏችሁ እንደሚችሉ አስቡ።

በተጨማሪም “Sacred Temple Clothing” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

4:12

Sacred Temple Clothing

ሙሴ 5፥4–9፣ 16–26

እግዚያብሄር መስዋዕቶቼን በፈቃደኛ እና ታዛዥ ልብ ካቀረብኳቸው ይቀበላል።

ሙሴ 5፥4–9፣ 16–26ን ስታጠኑ አዳምና ሔዋን እንዲሁም ልጆቻቸው ቃየን እና አቤል በመሥዋዕት ዙሪያ የነበራቸውን አመለካከት ልብ በሉ። ጌታ የአቤልን መስዋዕት ተቀብሎ የቃየን ሳይቀበል የቀረው ለምንድን ነው?

ጌታ መሥዋዕት እንድታደርጉ ምን እየጠየቃችሁ ነው? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለእነዚያ መስዋዕቶች ያላችሁን አመለካከት የሚቀርጽ ነገር አለ?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘፍጥረት 3ሙሴ 45:8–15

ኢየሱስ ክርስቶስ ከውድቀት ያድነናል።

  • ልጆቻችሁ የአዳምን እና የሔዋንን ውድቀት በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ለመርዳት፣ ከ“አዳም እና ሔዋን” (በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 13-16) ያሉትን ሥዕሎች ኮፒ ማድረግ እና መቁረጥ ትችላላችሁ። ከዚያም የአዳም እና የሄዋንን ተሞክሮዎች ስትወያዩ ምስሎቹን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ አብራችሁ መስራት ትችላላችሁ። ይህን ስታደርጉ፣ በሰማይ አባት እቅድ አዳምና ሔዋን ከኤደን ገነት መውጣታቸው ለምን አስፈላጊ እንደነበር ተናገሩ።

  • ልጆቻችሁ የውድቀትን ውጤት እንዴት እንደሚያሸንፉ ሲረዱ ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምስጋና ሊሰማቸው ይችላል። በአንድነት ሙሴ 4:256:48ሮሜ 5:122 ኔፊ 2፡22–23፣ ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ ይህንን ዓረፍተ ነገር የሚያጠናቅቁባቸውን መንገዶች እንዲያገኙ እርዷቸው፡ “በውድቀት ምክንያት፣ እኔ…” ከዚያም ሙሴ 5፡8–11፣ 14–156:59አልማ 11፡42 አብራችሁ ስታነቡ፤ ይህንን ዓረፍተ ነገር ሊያጠናቅቁ ይችላሉ፡- “በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ እኔ…።” ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስጋና አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ሙሴ 4፥1–4

ትክክለኛውን መምረጥ እችላለሁ።

  • የነጻ ምርጫን መርህ ለማስተዋወቅ አንድ ቀላል የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገር ትምህርትን አስቡ፡ ልጆቻችሁ የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ እንዲቀቡ ጋብዟቸው ነገር ግን አንድ ቀለም ብቻ እንዲጠቀሙ አድርጓቸው። ምርጫዎች ቢኖሩ የተሻለ የሚሆነው ለምድነው? ከዚያም ሙሴ 4፡1–4ን አብራችሁ አንብባችሁ እግዚአብሔር ለምን ትክክለኛውን ትክክል ካልሆነው መምረጥ እንድንችል እንደሚፈልግ መነጋገር ትችላላችሁ። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሩ ምርጫዎችን እንድናደርግ የሚረዱን እንዴት ነው?

  • ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ሊያደርጉ የሚችሉትን መልካም ምርጫዎች እንዲያስቡ እና እንዲስሉ እርዷቸው። ወይም እንደ “Choose the Right Way” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 160–61) አይነት ጥሩ ምርጫዎችን ስለማድረግ አንድ መዝሙር አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ። ጥሩ ምርጫ ስላደረጋችሁበት ጊዜ፣ ከዚያም በኋላ ምን እንደተሰማችሁ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

አዳም እና ሔዋን

ውድቀት፣ በሮበርት ቲ ባሬት

ሙሴ 5፥4፣ 8

ወደ ሰማይ አባት መጸለይ እችላለሁ።

  • አዳምና ሔዋን ከኤደን ገነት ከወጡ ጊዜ ጀምሮ ከሰማይ አባት ጋር መሆን አልቻሉም ነበር። ሙሴ 5:4፣ 8ን ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ እና አዳምና ሔዋን ወደ እርሱ ለመቅረብ እና እሱን ለመስማት ያደረጉትን ነገር እንዲያገኙ እርዷቸው። በጸሎታችን ውስጥ ለሰማይ አባት ልንነግረው የምንችላቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

አዳምና ሔዋን ከመሥዋዕት በግ ጋር በመሠዊያ ላይ

In Similitude of the Sacrifice of the Only Begotten of the Father, በማይክ ማልም (ሙሴ 5፡5–9 ይመልከቱ)

የልጆች አክቲቪቲ ገጽ፥ የአዳምና ሔዋን ውድቀት