ኑ፣ ተከተሉኝ
ጥር 12–18 (እ.አ.አ)። “በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“፥ ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 2–3፤ አብርሃም 4–5


“ጥር 12–18 (እ.አ.አ)። ‘በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ’፥ ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 2–3፤ አብርሃም 4–5 “ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ጥር 12–18 (እ.አ.አ)። “በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“፥ “ኑ፥ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)

ምድር እና ጨረቃ

ጥር 12–18 (እ.አ.አ)፥ “በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“

ኦሪት ዘፍጥረት 1–2ሙሴ 2–3አብርሃም 4–5

በዙሪያችን ያለው አለም በጣም ያማረ እና ሞገስ ያለው ስለሆነ ምድር “ባዶ እና አንዳችም ያልነበረባት“ “ባዶ እና ባድማ“ የነበረችበትን ጊዜ ለመገመት ያስቸግራል (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥2አብርሃም 4፥2)። የፍጥረት ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ነገር ቢኖር እግዚያብሄር ከአንድ ያልተደራጀ ነገር አንድ ታላቅ ነገር በጊዜ ሂደት መስራት እንደሚችል ነው፡፡ ህይወት ምስቅልቅል በሚመስልበት ጊዜ ያንን ማስታወሱ ይጠቅማል፡፡ ሰማያዊ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪዎች ናቸው፣ በእኛ ላይ ያላቸው የፈጠራ ስራ አላለቀም፡፡ በህይወታችን የጨለማ ጊዚያት ብርሃን እንዲፈነጥቅ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ባዶነታችንን በህይወት መተካት ይችላሉ። መሆን ወዳለብን መለኮታዊ ማንነት ሊቀይሩን ይችላሉ። ያ በእግዚያብሄር መልክ እና አምሳያ መፈጠር ማለት ነው (ዘፍጥረት 1፥26 ይመልከቱ)፡፡ እንደ እርሱ ከፍ ከፍ ያልን፣ የከበርን ሰማያዊ የመሆን አቅም አለን።

ስለኦሪት ዘፍጥረት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘፍጥረት“ የሚለውን ይመልከቱ፡፡

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥1–25ሙሴ 2፥1–25አብርሃም 4፥1–25

“በአንድያ ልጄ ፈጠርኩ”

ምንም እንኳን ዓለም እንዴት እንደተፈጠረ ሁሉንም ነገር ባናውቅም እግዚአብሔር ስለ ፍጥረት ሊገልጥ የመረጠውን ነገር ማወቅ ትኩረት የሚስብ ነው። በዘፍጥረት 1፡1-25ሙሴ 2:1-25፤ እና አብርሃም 4፡1-25 እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር ምን ያስተምራል? እነዚህን ነገሮች እንድታውቁ የሚፈልገው ለምንድነው? ስለእነዚህ ዘገባዎች ስታሰላስሉ፣ ስለሰማይ አባት፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለአለም እና ስለራሳችሁ የሚያስተምሩትን ነገር ግምት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።

ጥናትችሁን ለማዳበር፣ በእግዚአብሔር ፍጥረታት መካከል ስትሆኑ ወይም እንደ “All Creatures of Our God and King” (መዝሙሮች፣ ቁ. 62) ያለ መዝሙር እያዳመጣችሁ እነዚህን ጥቅሶች ማንበብን አስቡ። ለፈጣሪ አክብሮት እንዲሰማችሁ የሚረዱ የፍጥረቱን ሥዕሎች ማግኘት ትችላላችሁ። እነዚህን ምስሎች፣ ከምሥክርነታችሁ ጋር ለሌሎች ለማካፈል አስቡ።

ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥32–34።ይመልከቱ።

የኤደን ገነት ሥዕል

የኤደን ገነት፣ በግራንት ሮምኒ ክላውሰን

ዘፍጥረት 1፥26-27ሙሴ 2፥26–27አብርሃም 4፥26–27

የሴሚናሪ ምልክት
በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሬአለሁ።

ዘፍጥረት 1:26–27ሙሴ 2:26–27 እና አብርሃም 4፡26–27ን ስታነቡ በእግዚአብሔር “መልክ” ወይም “አምሳል”፣ ወንድና ሴት ሆኖ መፈጠር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን እውነቶች ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ለምሳሌ፣ እነዚህ እውነቶች ለራሳችሁ፣ ለሌሎች እና ለእግዚአብሔር ባላችሁ አመለካከት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? ስለራሳችሁ አሉታዊ የሆነ ስሜት ሲሰማችሁ እንዴት ሊረዷችሁ ይችላሉ?

ስለእነዚህ ጥያቄዎች ለማሰብ እንዲረዳችሁ፣ እንዲህ ያለውን ዓረፍተ ነገር ለመሙላት ሞክሩ፡- “በእግዚአብሔር መልክ እንደተፈጠርኩ ስለማውቅ፣… እመርጣለሁ” “አካላችሁ ቅዱስ ነው [Your body is sacred]” የሚለውን በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ውሳኔዎችን የማድረግ መመሪያ (ገጽ 22–29) መከለስ ይረዳል። ሰውነታችሁ የተቀደሰ መሆኑን እንደምታውቁ ለእግዚአብሔር ለማሳየት የምታደርጉትን ነገር ለመምረጥ አስቡ።

“God’s Greatest Creation” (ወንጌል ላይብረሪ) በተሰኘው ቪዲዮ ውስጥ፣ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለ ተአምረኛው የሰው አካል ምስክርነት ሰጥተዋል። ይህን ቪዲዮ ስትመለከቱ፣ “የሰማይ አባት ስለ ሰውነቴ ምን እንዲሰማኝ ይፈልጋል?” በማለት ራስችሁን ጠይቁ። ይህስ ከምትሰሙት ሌሎች መልእክቶች የሚለየው እንዴት ነው?

2:51

God's Greatest Creation

አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠር ማለት ሀሳባችን፣ ስሜታችን እና ፍላጎታችን በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው እንዲሁም ማሻሻል አያስፈልገንም (ወይም አንችልም) ይሉ ይሆናል። ለዚህ ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ? ከሞዛያ 3፡19 እና ኤተር 12፡27 ምን ግንዛቤ አገኛችሁ?

በተጨማሪ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “አካላችሁ፡ ለመንከባከብ ታላቅ ስጦታ [Your Body: A Magnificent Gift to Cherish]፣” ሊያሆና፣ ነሃሴ 2019 (እ.አ.አ)፣ 50–55 ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥27–282፥18–25ሙሴ 3፥18፣ 21–24አብርሃም 5፥14–18

በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

አዳም እና ሄዋን በትዳር የተጣመሩት በዘላለማዊ የክህነት ስልጣን ሃይል ለዚህ ህይወት እና ለዘላለም ነው፡፡“Lessons from Eveኢንዛይን፣ ህዳር 1987(እ.አ.አ)፣ 87)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1፥27–282፥18–25ሙሴ 3፥18, 21–25፤ እና አብርሃም 5፥14–19ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ፡፡ እግዚያብሄር በሰጠው ቅድስና ትዳርን እንዴት መያዝ ትችላላችሁ?

1 ቆሮንቶስ 11:11፤ “ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥28ሙሴ 2፥28አብርሃም 4፥28

የእግዚአብሔርን ፍጥረታት የመንከባከብ ኃላፊነት አለብኝ።

ዘፍጥረት 1:28ሙሴ 2:28 እና አብርሃም 4፡28 በእግዚአብሔር ፍጥረታት ላይ ስላለን ኃላፊነት ምን ይጠቁማሉ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፡16–21 እና 104፡13–18 በመረዳታችሁ ላይ ምን ይጨምራሉ?

እንዲሁም ጄራልድ ኩሴን፣“Our Earthly Stewardship,” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 57–59፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Environmental Stewardship and Conservation,” የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 2፥2-3ሙሴ 3፥2-3አብርሃም 5፥2-3

እግዚአብብሄር የሰንበትን ቀን ባረከው እና ቀደሰው፡፡

እግዚአብብሄር የሰንበትን ቀን ቀድሶታል እኛም እንቀድሰው ዘንድ ይጠይቀናል። ዘፍጥረት 2:2–3ሙሴ 3:2-3አብርሃም 5፡2-3ን ስታነቡ ለእናንተ ሰንበትን ምን “[የተባረከ]” እንደሚያደርግ አስቡ

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፡9–13፤ ፤ “The Sabbath Is a Delight” (video),“(ቪዲዮ)፣ በወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

0:50

Highlight: The Sabbath Is a Delight

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥1–25ሙሴ 2፥1–25አብርሃም 4፥1–25

ኢየሱስ ምድርን ፈጠረ።

  • ስለ ፍጥረት መማርን ለልጆቻችሁ የሚያዝናና ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? በእያንዳንዱ የፍጥረት ቀን ውስጥ የተፈጠሩ ነገሮችን ለማግኘት ወደ ውጭ ልትወስዷቸውና እንዲፈልጉ ማድረግ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ኢየሱስ የፈጠራቸውን ነገሮች ሥዕሎችም ሊመለከቱ ይችላሉ (“የምድር አፈጣጠር”ን በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 8-12 ይመልከቱ)። ከዚያም እናንተና ልጆቻችሁ ስለ ፍጥረት ካነበባችሁ በኋላ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሚሰማችሁ መናገር ትችላላችሁ።

  • ስለ ውብ አለማችን እንደ “My Heavenly Father Loves Me” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29) ያለ መዝሙር አንድ ላይ ለመዘመር አስቡ። ምናልባት ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማቸው የሚረዷቸውን ሌሎች የፈጠራቸውን ነገሮች በመዝሙሩ ላይ ሊጨምሩ ይችላሉ።

ልጆች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ እርዱ። “ልጆች ከወንጌል መርሆ ጋር የሚዛመድን ነገር እንዲስሉ፣ እንዲገነቡ፣ ቀለም እንዲቀቡ ወይም የሆነ ነገርን እንዲፅፉ ስትጋብዙ፣ መርሆውን የበለጠ እንዲገነዘቡት ትረዷቸዋላችሁ እና ስለተማሩት ነገር ተጨባጭ ማስታወሻን ትሰጧቸዋላችሁ” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣፣ 32)።

ዘፍጥረት 1፥26-27ሙሴ 2፥26–27አብርሃም 4፥26–27

የተፈጠርኩት በእግዚአብሔር አምሳል ነው።

  • ልጆቻችሁ ሁላችንም በእግዚአብሔር አምሳል እንደተፈጠርን ሲያውቁ ለራሳቸው እና ለሌሎች ሰውነት የክብር እና የአድናቆት ስሜት ሊያዳብሩ ይችላሉ። ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ ለማገዝ ሙሴ 2፡26–27ን ስታነቡላቸው ልጆቻችሁ የራሳቸውን ፎቶ ወይም በመስታወት ራሳቸውን እንዲመለከቱ ማድረግ ትችላላችሁ። ትንንሽ እንስሳት ብዙውን ጊዜ በወላጆቻቸው “አምሳል” እንዴት እንደተፈጠሩ ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ (ለምሳሌ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያለውን ሥዕል ይመልከት)። ይህ እናንተ በሰማይ አባት አምሳል እንደተፈጠራችሁ ማወቃችሁ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ወደ ውይይት ሊያመራ ይችላል።

    ድብ እና ግልገሎች
  • እናንተ እና ልጆቻችሁ የሰውን አካል በመሳል ከዚያም ስዕሎቹን ወደሚገጣጠም እንቆቅልሽ መቁረጥ ያስደስታችሁ ይሆናል። ልጆቻችሁ የመገጣጠም ጨዋታቸውን ሲገጣጥሙ የሰማይ አባትን ስለለሰውነታቸው የሚያመሠግኑ መሆናቸውን ስለሚያሳዩባቸው መንገዶች ማውራት ትችላላችሁ።

ኦሪት ዘፍጥረት 2፥2-3ሙሴ 3፥2-3አብርሃም 5፥2-3

የሰንበት ቀን ቅዱስ ነው።

  • ሙሴ 3፡2–3ን ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ያደረገውን እንዲሰሙ ጠይቁ። ልጆቻችሁ የሰንበት እለትን ለመቀደስ እና ከሌሎች ቀናት የተለየ ለማድረግ መተግበር የሚችሏቸውንን ነገሮች እንዲፈልጉ ወይም እንዲስሉ እርዷቸው። የሰንበትን ቀን ማክበር ለእናንተ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

  • ልጆቻችሁ የሰማይ አባትን እና ኢየሱስን የሚያከብሩ ነገሮችን በእሁድ ቀን ለማድረግ ለምን እንደሚመርጡ ለጓደኛቸው እያስረዱ እንደሆነ አድርገው እንዲተውኑ እርዷቸው። ዘፍጥረት 2፡2-3ን በማብራሪያቸው ላይ እንዲጠቀሙ ጠቁሙ። የሰንበትን ቀን ማክበር ለሰማይ አባት እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

ያህዌ በሚያደራጀው ዓለም እጁን በደመና ውስጥ በማድረግ ቆሞ

ፍጥረት፣ ምስል በአኒ ሄንሪ ናደር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፥ ኢየሱስ ምድርን ፈጠረ