“ጥር 5–1 (እ.አ.አ)። ‘ይህ ስራዬ እና ክብሬ ነው’፦ሙሴ 1፤ አብርሃም 3,” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ጥር 5–1 (እ.አ.አ)። ”ይህ ስራዬ እና ክብሬ ነው”፥ ኑ፣ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)
ጥር 5–1 (እ.አ.አ)፥ ”ይህ ስራዬ እና ክብሬ ነው”
ሙሴ 1፤ አብርሃም 3
መጽሃፍ ቅዱስ “በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“ በሚሉት ቃላት ይጀምራል።(ኦሪት ዘፍጥረት 1፥ 1) ነገር ግን ከዚህ “መጀመሪያ“ በፊት እዚያ ምን ነበር? እንዲሁም እግዚያብሄር ይህን ሁሉ ለምን ፈጠረ? በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ጌታ ለእነዚህ ጥያቄዎች ብርሃን ፈንጥቋል።
ለምሳሌ፣ አብርሃም ያየውን “አለም ከመመስረቱ በፊት“ በመንፈስ ህልውና እንደነበረን የሚያሳይ ራዕይን መዝገብ ሰጥቶናል (አብርሃም 3፥22–28ይመልከቱ)። በተጨማሪም ጌታ በመንፈስ ተነሳሽነት የተተረጎሙትን ወይም የተከለሱትን የሙሴ መጽሃፎች የሚባሉትን የዘፍጥረት የመጀመሪያ ስድስት ምዕራፎች ሰጥቶናል—ያ “በመጀመሪያ “ ብሎ አይጀምርም። ከዚያ ይልቅ ለዘፍጥረት ታሪክ የተወሰነ አውድ ከሚሰጠው ከሙሴ ተሞክሮ ይጀምራል። በአንድ ላይ፣ እነዚህ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጽሁፎች የብሉይ ኪዳን ጥናታችንን ለመጀመር ጥሩ ቦታዎች ናቸው፤ ምክንያቱም ንባባችንን መስመር ሊያሲዙ የሚችሉ አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ: እግዚያብሄር ማን ነው? እኛ ማን ነን? የእግዚያብሄር ስራ ምንድን ነው፣በዚያ ውስጥ የእኛ ቦታ ምንድን ነው? የኦሪት ዘፍጥረት የመክፈቻ ምእራፎች ለሙሴ ጥያቄ የጌታ መልሶች ሆነው ሊታዩ ይችላሉ: ”እግዚአብሔር ሆይ፣ ለአገልጋይህ ርህራሄ ይሰማህ፣ እና ስለዚህ ምድርና ኗሪዎቿ እናም ስለሰማያት ንገረኝ፣ ከዚያም አገልጋይህ ይረካል” (ሙሴ 1፥36)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
የእግዚያብሄር ልጅ እንደመሆኔ መለኮታዊ ፍጻሜ አለኝ።
“ጌታ በቀጥታ የሚያናግራችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እንድታውቁ የሚፈልገው የመጀመሪያው ነገር ስለ እውነተኛ ማንነታችሁን ነው” በማለት ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን አስተምረዋል) (“Choices for Eternity” [worldwide devotional for young adults, May 2022], የወንጌል ላይብረሪ)። ይህንንም ተከትሎ በዚህ ተመሳሳይ ጉዳይ ሰይጣን ግራ ሊያጋባችሁ ሊሞክር ይችላል። እግዚአብሔር ለሙሴ በላከው በሙሴ 1፡4፣ 6 መልእክት እና በሙሴ 1፡12 ባለው የሰይጣን መልእክት ውስጥ ያለውን ተመሳሳይነት ተመልከቱ። በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ስላለው ልዩነት ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተማራችሁ?
ፕሬዘደንት ኔልሰንም “ስለ ማንነታችሁ ያላችሁ አመለካከት በምትወስኗቸው ውሳኔዎች ሁሉ ማለት ይቻላል ተጽዕኖ ያሳድራል” በማለት አስተምረዋል” (“Choices for Eternity”)። የእግዚአብሔር ልጅ በመሆናችሁ፣ ማንነታችሁ ከሌሎች መለያዎች እንዲቀድም የምታደርጉባቸውን ምርጫዎች ዝርዝር ማውጣትን አስቡ።
በሙሴ 1 ውስጥ የትኞቹ ተጨማሪ ጥቅሶች ወይም ሀረጎች መለኮታዊ ዋጋችሁን እንድትገነዘቡ ይረዷችኋል? እንዲሁም በ“Choices for Eternity” ክፍል ውስጥ “First: Know the truth about who you are.” የሚለውን የፕሬዘዳንት ኔልሰንን መልእክት ማንበብ ትችላላችሁ። አስፈላጊው መለያችሁ የእግዚአብሔር ልጅነታችሁ እንዲሆን ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?
በተጨማሪም “I Am a Child of God,” Hymns (1985), no. 301; “Our True Identity” (video), Gospel Library; Topics and Questions, “Children of God,” Gospel Library ይመልከቱ።
Our True Identity
በጌታ እርዳታ ሰይጣንን መቃወም እችላለሁ።
ሙሴ 1 በግልጽ እንደሚያሳየው፣ ኃይለኛ መንፈሳዊ ልምዶች ስለገጠሙን ብቻ እንደገና አንፈተንም ማለት አይደለም። እንዲያውም፣ ከሰይጣን ዘዴዎች መካከል አንዱ እነዚህን ልምዶች እንድንጠራጠር መፈተን ነው። በ ቁጥር 12–26ውሰጥ ሙሴ ለሰይጣን የሰጠውን መልስ ስታነቡ፣ ለተቀበላችሁት ምስክርነት ታማኝ ሆናችሁ እንድትጸኑ የሚረዳችሁ ምን ትማራላችሁ? ሙሴ በመጨረሻ ሰይጣንን እንዲያሸንፍ ያገዘው ምንድን ነው?
ከሙሴ ተሞክሮ ሌላ የምናገኘው ትምህርት ሰይጣን የሚፈትነን የእግዚአብሔርን እውነትና ኃይል በመዋሸት ነው። እንደ ሰው ሰራሽ ተክል ወይም የልጆች አሻንጉሊት ያሉ አንዳንድ ሰው ሰራሽ ነገሮች አስቡ። የውሸት መሆናቸውን እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ? ዛሬ ሰይጣን እናንተን ለመፈተን የሚጠቀምባቸውን ውሸቶች አስቡ። ከሙሴ 1፡13–18 ውሸቶቹን ስለማወቅ እንዲሁም ስላለመቀበል ምን ትማራላችሁ? ጌታ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል? ( ሙሴ 1፡24–26 ይመልከቱ)።
በተጨማሪም ማቴዎስ 4፥1–11፣ ጋሪ ኢ.ስቲቨንሰን፣“Deceive Me Not፣“ ሊያሆና ህዳር 2019 (እ.አ.አ)93–96፤ “I Am a Son of God” (video), የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።
I Am a Son of God
በቤት ውስጥ መማር ሊታቀድ የሚችል ሲሆን ነገር ግን ድንገተኛ መሆንም ይችላል። “በቤተሰብ ውስጥ የማስተማር እድሎች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱት መደበኛ ባልሆኑ የእለት ተእለት ጊዜያት ነው—ምግብ በምትመገቡበት ጊዜ፣ የቤት ውስጥ ስራዎችን ስትሠሩ፣ ጨዋታ ስትጫወቱ ወይም ስትጓዙ”(በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 31)። ለምሳሌ፣ በሙሴ 1 ውስጥ ሙሴ ሰይጣንን እንዴት እንደተቃወመው ከማንበብ በተጨማሪ፣ በእራት ሰዓት የጠላትን ተፅእኖ እንዴት እንደተቋቋማችሁ እንደቤተሰብ በመነጋገር ጥቂት ደቂቃዎችን ማሳለፍ ትችላላችሁ።
የእግዚያብሄር ስራ እና ክብር ዘላማዊ ህይወት እንዳገኝ መርዳት ነው፡፡
የእግዚያብሄርን ፍጥረቶች በራእይ ከተመለከተ በኋላ ሙሴ “እባክህ ንገረኝ እንዴት እነዚህ ነገሮች እንዲህ ሆኑ“ ሲል ለጌታ ጥያቄ አቀረበ (ሙሴ 1፥30)። በ ሙሴ 1፥31–39ውስጥ ስላለው የጌታ ምላሽ ያስገረማችሁ ምንድነው? ባለመሞት እና በዘላለማዊ ህይወት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? (በርዕሶችን እና ጥያቄዎች፣ “የዘላለም ሕይወት፣” የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱንም ለማድረግ የሚረዳው እንዴት ነው? አብርሃምም በ አብርሃም 3ውስጥ የተመዘገበ የራእይ ተሞክሮ ነበረው፡፡ ከ ቁጥር 24-26 ውስጥ የሙሴን ጥያቄ ለመመለስ መርዳት የሚችል ምን ታገኛላችሁ?
በምድር ላይ ከመወለዴ በፊት እንደ መንፈስ እኖር ነበር።
ስለ ቅድመ ምድር ህይወታችን የምናውቀው በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን አብዛኛው የምናውቀው በአብርሃም 3፡22-28 ካለው የአብርሃም ራዕይ የመጣ ነው። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ ስለራሳችሁ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያሉ እውነቶችን ጨምሮ ያገኛችሁትን እውነቶች ዝርዝር ጻፉ። እነዚህ እውነቶች ለእናንተ ዋጋ ያላቸው የሆኑት ለምንድን ነው? በሕይወታችሁ ውስጥ ምን ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ?
በተጨማሪም Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች] “የቅድመ ምድር ህይወት፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ።
-
በሙሴ 1፡4 ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ ያለውን መልእክት አንድ ላይ ካነበባችሁ በኋላ፣ ልጆቻችሁ በመስታወት ራሳቸውን እንዲመለከቱ አድርጉና “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” የሚለውን ተመሳሳይ መልእክት ለራሳቸው እንዲነግሩ አድርጉ። ከዚያም “የእግዚአብሔር ልጅ ነህ/ነሽ” የሚለውን መልእክት እርስ በርሳቸው ሊባባሉ ይችላሉ። የተለያዩ ሰዎችን ሥዕል ልታገኙና ልጆቻችሁ እያንዳንዳቸው ላይ በመጠቆም “ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” እንዲሉ ልትጋብዙ ትችላላችሁ። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችሁን በማወቃችሁ ለምን ደስ እንደሚላችሁ አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ። ይህ እውቀት እናንተ ራሳችሁን እና ሌሎችን የምትይዙበትን መንገድ እንዴት ይለውጣል?
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ በሙሴ 1፡4 ላይ ያለውን እግዚአብሔር መልእክት በverse 12 ላይ ካለው የሰይጣን መልእክት ጋር ልታነጻጽሩ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ እግዚአብሔር ለእነሱ የላከውን መልእክት ሰይጣን ከሚልከው መለየት እንዲችሉ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው?
ሙሴ ያህዌን አየ፣ በጆሴፍ ብሪኪ (ዝርዝር)
እግዚአብሔር እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።
-
ሙሴ 1:6ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ እግዚአብሔር ለሙሴ ስለነበረው “ሥራ” ልትነግሯቸው ትችላላችሁ። የወንጌል ጥበብ መጽሐፍ፣ ቁ. 13–16፣ ወይም የብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ ገጽ 64–84፣ ልጆቻችሁ ሙሴ በሰማይ አባት እርዳታ ያከናወነውን እንዲያዩ ለመርዳት ለመጠቀም አስቡ። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ሥራ ምንድን ነው? (ለምሳሌ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፡20 ይመልከቱ)።
የሰይጣንን ፈተናዎች መቋቋም እችላለሁ።
-
ሙሴ 1፡12–26ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታጠኑ፣ ሰይጣንን ለመቃወም ሙሴ ያደረገውን እንዲያውቁ እርዷቸው (ቁጥር 13፣ 15፣ 18፣ 20–22፣ 26 ይመልከቱ)። ፈተናን ለመቋቋም ማድረግ የሚችሏቸውን ነገሮች (እንደ መጸለይ፣ ትቶ መሄድ፣ ወይም እርዳታ መጠየቅ) መተወን ለእነሱ አስደሳች ሊሆን ይችላል።
በምድር ላይ ከመወለዴ በፊት እንደ መንፈስ እኖር ነበር።
-
ስለቅድመ ምድር ህይወታችን ማወቅ ልጆቻችሁ በዘላለማዊ እውነት ላይ ተመስርተው ምርጫ እንዲያደርጉ ሊያነሳሳቸው ይችላል። ስለእሱ እንዲማሩ ለመርዳት በአብርሃም 3፡22-28 ውስጥ እንደ “ዓለም ከመመስረቱ በፊት”፣ “ነፍሶች”፣ “ምድርን እንሰራለን” እና “እንፈትናቸዋለን” ያሉ አንዳንድ ቁልፍ ቃላትን እና ሀረጎችን ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። የሰማይ አባት እኛን ወደ ምድር ስለላከበት ምክንያት እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል?
-
እንደ “I Will Follow God’s Plan” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 164–65) ያለ መዝሙር አብርሃም 3 የሚያስተምረውን ሊያጠናክር ይችላል። ምናልባት ልጆቻችሁ ከቃላቶቹ ጋር የሚሄዱ ስዕሎችን እንዲስሉ ልትጋብዙ ትችላላችሁ።
-
ልጆቻችሁ እግዚአብሔር የጠየቃቸውን ለማድረግ ወይም ላለማድረግ መምረጥ ሊኖርባቸው ስለሚችሉ ሁኔታዎች እንዲያስቡ እርዷቸው (አብርሃም 3፡25 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም ለወጣቶች ጥንካሬ፡ ምርጫ ማድረግ መመሪያን ይመልከቱ)። ለእነዚህ ሁኔታዎች ሊሆኑ የሚችሉ መልሶችን እንዲለማመዱ አድርጉ። የተሳሳተ ምርጫ ስናደርግ አዳኙ ሊረዳን የሚችለውእንዴት ነው?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።