“ታህሳስ 29–ጥር 4 (እ.አ.አ)። የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ኪዳን፡ የብሉይ ኪዳን መግቢያ፣” .ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
የብሉይ ኪዳን መግቢያ፣” ኑ፥ ተከተሉኝ፦2026 (እ.አ.አ)
ታህሣሥ 29–ጥር 4 (እ.አ.አ)፦ የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ኪዳን
የብሉይ ኪዳን መግቢያ
በዚህ አመት ብሉይ ኪዳንን ማጥናት ስትታስቡ ምን ይሰማችኋል? ጉጉት? ጥርጣሬ? ፍርሃት? እነዚህን ሁሉ ስሜቶች መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ብሉይ ኪዳን በአለም እጅግ በጣም ጥንታዊ ከሆኑ የጽሁፍ ስብስቦች አንዱ ነው፤ ያ አስደሳችም አስፈሪም ሊያደርገው ይችላል። እነዚህ ጽሁፎች ባይተዋር እና አንዳንድ ጊዜ ያልተለመደ ብሎም የማይመች ሊመስል ከሚችል ከአንድ ጥንታዊ ባህል ነው የመጡት። ሆኖም በነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ሰዎች የተለመዱ የሚመስሉ ተሞክሮዎችን ሲለማመዱ እናያለን። የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮታዊ ባህርይ እና ወንጌሉን የሚመሰክሩ የወንጌል ጭብጦችን እንገነዘባለን። አዎን፣ እንደ አብርሃም፣ ሳራ፣ሃና እና ዳንኤል ያሉ ሰዎች የኖሩት ኑሮ በተወሰኑ መንገዶች ከእኛ በጣም የተለየ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ልክ እንደ እኛ እንደሁላችን የቤተሰብን ደስታና እና አለመግባባት፣ የእምነት እና የጥርጣሬ ጊዜያትን እንዲሁም ስኬትን እና ውድቀትን በተጨማሪ አሳልፈዋል፡፡ ከሁሉ በላይ እምነትን ተለማምደዋል፣ ንስሃ እንዲሁም ቃልኪዳኖችን ገብተዋል፣ መንፈሳዊ ልምምዶች ነበሯቸው እንዲሁም ስለ አዳኙ በተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ላይ ተስፋ አልቆረጡም ነበር። እግዚአብሔር በሕይወታቸው እንዴት እንደሰራ ስንማር፣ እርሱን በእኛ ውስጥም እናየዋለን፣ እንዲሁም ከዘማሪው ጋር “ህግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው። … ባሪያህም ወደደው” (መዝሙር 119:105፣ 140) እንላለን።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ብሉይ ኪዳን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የበለጸገ መንፈሳዊ ምግብ ማግኛ አንዱ መንገድ የሕይወት እንጀራ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በመፈለግ ነው (ዮሐንስ 6፡48 ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ በሚከተለው ውስጥ አዳኙን እንዴት ታዩታላችሁ?
-
መና (ዘጸአት 16:4፣ 11–15፤ ዮሐንስ 6:35)
-
የመሥዋዕቱ በግ (ዘጸአት 12፡3–5፤ ዮሐንስ 1፡29)
-
የነሃስ እባብ (ዘኁልቁ 21፥4–10፤ ዮሐንስ 3፥14)
-
ዮናስ (ዮናስ 1:4–17፤ ማቴዎስ 12:38–41)
እነዚህ ምሳሌዎች ስለ እርሱ ምን ያስተምራሉ? በብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠቀሰባቸውን የትኞቹን ሌሎች ማጣቀሻዎች አስቀድማችሁ ታውቃላችሁ?
“Jesus Christ Is the Treasure,” በተሰኘው መልእክታቸው፣ ሽማግሌ ዳሌ ጂ ሬንሉድ “ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ እና በእርሱ ላይ እንድናተኩር” (ሊያሆና፣ ህዳር 2023፣ 98) አበረታተውናል። ኢየሱስ ክርስቶስን በብሉይ ኪዳን ብቻ ሳይሆን በሕይወታችሁም ጭምር ለማግኘት ልታደርጉ የምትችሏቸውን ነገሮች በመፈለግ መልእክቱን ለማንበብ አስቡ።
በተጨማሪም “Types or Symbols of Christ” በቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ”፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “Seek the Lord Early,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 108 ተመልከቱ።
ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ምልክቶችን ፈልጉ። “ሁሉም ነገሮች ተምሳሌት አላቸው፣ … ሁሉም ነገሮች የፈጠርኳቸው እና የሰራኋቸው ስለ እኔ እንዲመሰክሩ ነው” (ሙሴ 6፡63) በማለት ጌታ አዳምን አስተምሮታል። እያጠናችሁም ሆነ እያስተማራችሁ ቢሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማተኮር በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ትርጉም እንድታገኙ እና ለእሱ ያላችሁ ፍቅር እና እምነት እንዲጨምር ሊረዳችሁ ይችላል። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 7ን ተመልከቱ።)
ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ ነው።
“አብ አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን እና ቤዛችን አስተዋወቀ እንዲሁም ‘እርሱን [እንድንሰማው]’ ትእዛዝ ሰጠን። ከዚህ አቅጣጫ በመነሳት ‘እግዚአብሄር’ ወይም ‘ጌታ’ የተናገራቸው የቅዱሳን ጽሑፎች መዛግብት ሁልጊዜ የያህዌ፣ ከሞት የተነሣው ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ናቸው ማለትም ይቻላል” (“The Teachings of Jesus Christ,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ) 102)።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ስለ ማንነቱ ሲሞግቱት፣ “አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ” በማለት ተናግሯል። እነዚህ ቃላት ኢየሱስን የሰሙትን ሰዎች አስደንግጠው ስለነበር ሊወግሩት ተዘጋጅተው ነበር (ዮሐንስ 8፡58–59 ይመልከቱ)። አንዳንድ አይሁዶች ኢየሱስ በተናገረው ነገር የተቆጡበትን ምክንያት ለማወቅ Exodus 3:13–15፤ 6:3–5ን ለማንበብ አስቡ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ያህዌ መሆኑን ማወቁ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው?
ጌታ በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ብዙ “ግልጽ እና ውድ የሆኑ ነገሮችን” መልሷል።
የመጽሐፍ ቅዱስን መምጣት “ብዙ ግልጽ እና የከበሩ ነገሮች” ከእሱ እንደሚወሰዱ በማብራራት ጌታ ለኔፊ በራእይ አሳይቶታል። ጌታ እንዴት “የተወሰዱትን ግልጽ እና የከበሩ ነገሮችን እንዲታወቁ” እንዳቀደ በመፈለግ 1 ኔፊ 13፡21–29፣ 38–42ን ለማንበብ አስቡ። በ2 ኔፊ 3፡12 መሰረት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፈ ሞርሞን እንዴት አብረው ይሰራሉ?
በዚህ ዓመት ብሉይ ኪዳንን በምታጠኑበት ጊዜ፣ ኔፊ አስቀድሞ ያያቸውን አንዳንድ “ሌሎች መጽሃፍትን” ልታጠኑ ትችላላችሁ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
-
የጆሴፍ ስሚዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አካል የሆነውን የሙሴ መጽሐፍ። አሁን ላይ ባለው በዘፍጥረት 1-6 ላይ የማይገኙ እውነቶችን እና ዘገባዎችን ይመልሳል።
-
ጆሴፍ ስሚዝ የጥንቱን የግብፅ ፓፒረስ ሲመረምር የተገለጠለት የአብርሃም መጽሐፍ (ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “የአብርሃም መጽሐፍ፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)።
-
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተለያዩ ጽሁፎች፣ አንዳንዶቹ በግርጌ ማስታወሻዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አባሪ እና የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ ውስጥ ይገኛሉ።
በጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተመለሱት የብሉይ ኪዳን ዘገባዎች አንዳንድ ምሳሌዎች እነዚህ ናቸው፡ የሄኖክ ጽዮን ከተማ (ሙሴ 7፥18–19)፣ በሰማይ ስላለው ምክር የአብርሃም ራእይ (Abraham 3:22–28) እና የመልከ ጼዴቅ አገልግሎት (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፡25–40)። እነዚህ ዘገባዎች ለእናንተ “ግልጽና የከበሩ” የሆኑት ለምንድን ነው?
አዳምና ሔዋን መስዋዕት እያቀረቡ፣ በኪዝ ላርሰን (ዝርዝር)
ብሉይ ኪዳን ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን የቃል ኪዳን ግንኙነት እንድረዳ ያግዘንኛል።
ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በቃል ኪዳን በኩል “የተመረ[ጥን] ርስት” ሊያደርገን እንደሚፈልግ የሚያሳይ ታሪክ ነው (ዘጸአት 19፡5)። በዚያም ምክንያት፣ ብሉይ ኪዳንን ለማንበብ ለመዘጋጀት ስለ ቃል ኪዳኖች መማር የተሻለ መንገድ ነው—በተለይም እግዚአብሔር ለቀደሙት ነቢያት እንደ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ እና ለትውልዳቸው ያቀረበውን ዘላለማዊ ኪዳን። እንዲሁም ስለ ቃል ኪዳኖች ለመማር ጥሩ መንገድ የፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “The Everlasting Covenant” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 4-11) መልእክት ማጥናት ነው።
በምታነቡበት ወቅት፣ ቃል ኪዳኖች ለእኔ ለምን አስፈላጊ ናቸው? በማለት ራሳችሁን ጠይቁ። ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን ስጠብቅ ከእግዚአብሔር ምን አይነት “ልዩ የሆነ ፍቅር እና ምህረት” እቀበላለሁ? በዚህ ዓመት ብሉይ ኪዳንን ስታነቡ፣ ከእርሱ ጋር ስላላችሁ የቃል ኪዳን ግንኙነት እግዚአብሔር ሊያስተምራችሁ የሚፈልጋቸውን ነገሮች አስተውሉ።
በተጨማሪም ኤርምያስ 31፡31–34 ተመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
በብሉይ ኪዳን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መማር እችላለሁ።
-
የብሉይ ኪዳን ቃላቶች እንዲሁም ባሕል ለልጆች ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በምልክቶች እና በታሪኮች ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያዩት መርዳት ትችላላችሁ። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ነቢዩ ኢሳይያስ የክርስቶስን ልደት በትንቢት ተናገረ የሚለውን ከታች ያለውን ምስል መመልከት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የሚያዩትን ነገር ዝርዝር እንዲጠቁሙ አድርጉ። በተለይም ትኩረታቸው ሕፃኑ ኢየሱስ ላይ እንዲሆን አድርጉ። ከዚያም ኢሳይያስ ስለ አዳኙ ልደት በኢሳይያስ 7፡14፤ 9፡6 የጻፈውን ከእነርሱ ጋር ማንበብ ትችላላችሁ። በዚህ አመት በብሉይ ኪዳን ውስጥ አዳኙን ስለመገለግ የሚሰማችሁን ለልጆቻችሁ አካፍሉ።
ኢሳይያስ ስለ ክርስቶስን ልደት ጻፈ (ነቢዩ ኢሳይያስ የክርስቶስን ልደት ተነበኡየ)፣ በሃሪ አንደርሰን
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ መዝሙር 23ን ወይም ኢሳያስ 53፡3–9ን ማንበብ እና ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያስታውሱ ቃላትን ማግኘት ትችላላችሁ። እነዚህ ቃላት ስለ ህይወቱ እና ስለኃጢያት ክፍያው ምን ያስተምሩናል?
የሰማይ አባት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን ማድረግ ይፈልጋል።
-
ቃል ኪዳኖች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ዋና ጭብጥ ናቸው። ይህንን ጭብጥ ለልጆቻችሁ ለማስተዋወቅ፣ ለቤተሰብ ወይም ለጓደኞቻቸው ስለሚገቡትና ስለሚጠብቁት ቃል እንዲሁም የገቡትን ቃል መጠበቃቸው ለምን አስፈላጊ እንደሆነ መነጋገር ትችላላችሁ። ከዚያም የጥምቀትን ምስል መመልከት እና ስንጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር ስለምንገባው ቃል ወይም ቃል ኪዳን መነጋገር ትችላላችሁ (ሞዛያ 18፡10፣ 13 ይመልከቱ)። በተጨማሪ የቤተመቅደስን ምስል በማሳየት እዚያ ስለምንገባቸው ቃል ኪዳኖች ያላችሁን ስሜት ማካፈል ትችላላችሁ።
-
የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ልጆቻችሁ ከሰማይ አባት ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት እና ለመጠበቅ እንዲጓጉ ሊረዳቸው ይችላል። እንዲሁም ቃል ኪዳኖችን ስለመግባት እንደ “When I Am Baptized” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 103) ያለ መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ ነው።
-
ልጆቻችሁ በተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ስም የሚጠሩት ሰዎችን ያውቃሉ? ምናልባት አንድ ወላጅ ወይም አስተማሪ በሥራ ቦታ፣ በቤት እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ መንገድ ሊጠራ ይችላል። ስለ እነዚያ ስሞች ተነጋገሩ፣ ከዚያም ዘፀአት 6፡3ን አብራችሁ ስታነቡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት የሚታወቅባቸውን ስሞች እንዲያገኙ ልጆቻችሁን ጋብዟቸው (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻ ሐ ይመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።