”ብሉይ ኪዳንን ስናነብ ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፥ ብሉይ ኪዳንን ማንበብ” .ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ብሉይ ኪዳንን ማንበብ” .ኑ፥ ተከተሉኝ፥ 2026 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች
ብሉይ ኪዳንን ማንበብ
ኔፊ ወንድሞቹ በጌታ እንዲታመኑ ለማነሳሳት በፈለገ ጊዜ፣ የሙሴን ታሪክ እና ከኢሳይያስ ትምህርቶችን አካፍሎ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ የጥንት ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ለማበረታታት በፈለገ ጊዜ ስለ ኖኅ፣ ስለ አብርሃም፣ ስለ ሣራ፣ ስለ ረዓብ እንዲሁም ስለ ሌሎች እምነት አሳሰባቸው። ኢየሱስ ክርስቶስም የአይሁድ መሪዎችን “ስለ እኔ [ይመሰክራሉና]” (ዮሃንስ 5፥39) “[መጻሕፍትን መርምሩ]” በማለት ሲነግራቸው የነበረው ብሉይ ኪዳን ስለምንላቸው ጽሑፎች ነበር።
በሌላ አነጋገር፣ ብሉይ ኪዳንን ስታነቡ፣ የእግዚአብሔርን ሰዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ያነሳሱ፣ ያጽናኑ እና ያበረታቱ ቃላትን እያነበባችሁ ነው።
ነገር ግን ከረጅም ጊዜ በፊት የተጻፈ ነገር ለዛሬ ችግሮች መፍትሔ እንድታገኙ በእውነት ሊረዳችሁ ይችላል? አዎን፣ ይችላል! በተለይ ብሉይ ኪዳን ስለ ማን እንደተጻፈ ካስታወሳችሁ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት
እናንተን እና ቤተሰባችሁን የሚያጋጥሟችሁ ፈተናዎች ምንም ይሁን ምን መልሱ ሁል ጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መልስ ለማግኘት እርሱን ፈልጉት። ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም። በትዕግስት ማሰላሰል እና መንፈሳዊ መመሪያን መፈለግ ሊኖርባችሁ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ስለእርሱ የሚናገሩት ጥቅሶች በኢሳይያስ ገለጻ ውስጥ እንዳለው ግልጽ ይመስላሉ፣ “ህጻን ተወልዷልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና: …ስሙም የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“(ኢሳይያስ 9፥6)። በሌሎች ቦታዎች አዳኙ የተወከለው ቀጥታ ባልሆኑ ምልክቶች እና ምስስሎች ነው—ለምሳሌ፣ በእንስሳት መስዋዕት ገለጻ በኩል ወይንም ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር በሚልበት እና ከረሃብ በሚታደጋቸው ዘገባ አማካኝነት።
የአለም ብርሃን፣ በስኮት ሳምነር
በአዳኙ ላይ ታላቅ እምነት አንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ ታገኙታላችሁ። ምናልባት በዚህ አመት የጥናታችሁ ግብ ይህ ሊሆን ይችላል። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርቧችሁን ምንባቦች፣ ታሪኮች እና ትንቢቶች እንድታገኙ እና በእነሱም ላይ እንድታተኩሩ መንፈሱ እንዲመራችሁ ጸልዩ።
በአምላክ ተጠብቆ የቆየ
ብሉይ ኪዳን የሰው ልጆችን የተሟላ እና ትክክለኛ ታሪክ እንዲያቀርብላችሁ አትጠብቁ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ጸሃፊዎች እና አጠናቃሪዎች ሊፈጥሩ የሞከሩት ያንን አይደለም። የእነሱ ትልቅ ጉዳይ ስለእግዚያብሄር—ለልጆቹ ስላለው እቅድ፣ የእርሱ የቃል ኪዳን ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት ስለመሆኑ እንዲሁም በቃል ኪዳናችን መኖር ሳንችል ስንቀር ቤዛ እንዴት እንደምናገኝ አንድ ነገር ማስተማር ነበር። አንዳንድ ጊዜ ከታላላቅ ነቢያት ህይወት የተገኙ ታሪኮችን በጨምሮ ታሪካዊ ኩነቶችን እነሱ እንደገባቸው በመግለጽ አድርገውታል። ልክ መጽሃፈ ኢያሱ፣ መጽሀፈ መሳፍንት እና መጽሃፈ ነገስት ቀዳማዊ እና ካልዕ እንደሆኑት ሁሉ ኦሪት ዘፍጥረት የዚህ አንድ ምሳሌ ነው። ነገር ግን ሌሎች የብሉይ ኪዳን ጸሃፊዎች ታሪክ-ነክ ለመሆን በጭራሽ አላለሙም። ከዚያ ይልቅ እንደ ግጥም እና ስነጽሁፍ ባሉ የስነ-ጥበብ ስራዎች አማካኝነት አስተምረዋል። መዝሙረ ዳዊት እና መጽሃፈ ምሳሌ በዚህ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ። ከዚያም ከኢሳይያስ ጀምሮ እስከ ሚልክያስ ለጥንት እስራኤላውያን የእግዚያብሄርን ቃል የተናገሩ—እንዲሁም በመጽሃፍ ቅዱስ ተዐምራት አማካኝነት ዛሬም የሚናገሩን የነቢያት ውድ ቃላት አሉ።
እነዚህ ሁሉ ነቢያት፣ ገጣሚያን እና አቀናባሪዎች ቃላቶቻቸው ከሺዎች አመታት በኋላ በአለም ዙሪያ በሚገኙ ሰዎች ይነበቡ እንደሆን ያውቁ ነበር? አናውቅም። ነገር ግን የሆነው በትክክል ይህ ስለሆነ እንደነቃለን። መንግስታት ተነስተው ወድቀዋል፣ ከተሞች ድል ተነስተዋል፣ ነገስታት ኖረዋል ሞተዋል ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ከጸሃፊ እስከ ጸሃፊ ከትርጉም እሰከ ትርጉም ሁሉንም አልፎ ዘልቋል። በርግጥ አንዳንድ ነገሮች ጠፍተዋል ወይም ተቀይረዋል ሆኖም ብዙዎቹ በተዐምራዊ መንገድ ተጠብቀዋል።
የብሉይ ኪዳን ነቢይ በ ጁዲት ኤ.መህር (detail)
በዚህ አመት ብሉይ ኪዳንን ስታነቡ እነዚህ ማስታወስ የሚገባችሁ ጥቂቶች ነገሮች ናቸው። እግዚያብሄር እነዚህን የጥንት ጽሁፎች የጠበቃቸው እናንተን እና በምን አይነት ሁኔታዎች ውስጥ እያለፋችሁ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። አናንተን ወደእርሱ የሚያቀርብ እንዲሁም በእቅዱ እና በተወዳጅ ልጁ ላይ ያላችሁን እምነት ለመገንባት በእነዚህ ቃላት ውስጥ ለናንተ መንፈሳዊ መልእክት አዘጋጅቷል። ምናልባት አንድ የምታውቁትን ሰው ወደሚባርክ ወደ አንድ ምንባብ ወይም ማስተዋል ይመራችኋል—ለጓደኛችሁ ለቤተሰባችሁ አባል ወይም ከቅዱሳን ለአንዱ ልታጋሩት ወደምትችሉት አንድ መልዕክት። ብዙ አማራጮች አሉ። ስለዚያ ማሰብ አያስደስትም?
ኔፊ “ነፍሴ በጌታ ነገሮች ትደሰታለች” (2 ኔፊ 4:15) በማለት ተናግሯል። ምናልባት አሁን ብሉይ ኪዳን የምንለውን ኔፊ ያነበበውን ብዙ ተመሳሳይ ቃላት ስታነቡ ተመሳሳይ ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ መጻህፍት
በብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን የክርስቲያን እትሞች ውስጥ መጽሃፎቹ የተደራጁት መጀመሪያ ወደ አንድ ስብስብ ሲቀናበሩ ከተስተካከሉበት በተለየ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ የዕብራይስጡ መጽሃፍ ቅዱስ መጽሃፎቹን በሶስት ምድቦች ሲመድብ—ህግ፣ ነቢያት እና ጽሁፎች—አብዛኛዎቹ የክርስቲያን መጽሃፍ ቅዱሶች መጽሃፎቹን በአራት ምድቦች ይመድባሉ: ህግ (ኦሪት ዘፍጥረት እና ኦሪት ዘዳግም)፣ ታሪክ (መጽሃፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ–መጽሃፈ አስቴር)፣ የግጥም መጻህፍት (መጽሃፈ ኢዮብ–መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን) እና ነቢያት (ትንቢተ ኢሳይያስ–ትንቢተ ሚልክያስ)።
እነዚህ ምድቦች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ምክንያቱም የምታጠኑትን የመጽሃፍ አይነት ማወቃቹሁ እንዴት እንደምታጠኑት እንድታውቁ ሊረዳችሁ ስለሚችል ነው፡፡
“ህግን“ ወይም የብሉይ ኪዳንን የመጀመሪያ አምስት መጽሃፎች ስታነቡ ልታስታውሱ የሚገባችሁ ነገር እነሆ። ከሙሴ ጋር የሚያያዙት እነዚህ መጽሃፎች በጊዜ ሂደት ምናልባት በብዙ ጸሃፍት እና አጠናቃሪዎች እጆች ተላልፈዋል። ባለፉት ክፍለ ዘመናት፣ “ግልጽና እጅግ የከበሩ ብዙ ክፍሎች” ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተወገዱ እናውቃለን (1 ኔፊ 13፡23–26 ይመልከቱ)። አሁንም የሙሴ መጻህፍት በተነሳሽነት የተጻፉ የእግዚያብሄር ቃላት ናቸው፤ ምንም እንኳን—እንደማንኛውም በሟቾች አማካኝነት የተላለፉ ሌሎች የእግዚያብሄር ስራዎች—ለሰዎች እንከኖች የተጋለጡ ቢሆኑም። ሙሴ 1፥41፤ የእምነት አንቀጾች 1፥8)። በማዘጋጀት ስለረዳበት ስለተቀደሰው የመጽሃፈ ሞርሞን መዝገብ “ስህተቶቸ ካሉ ስህተቶቹ የሰዎች ስህተቶች ናቸው ፤ስለዚህ የእግዚያብሄር የሆኑትን አትኮንኑ“ ሲል የተናገራቸው የሞሮኒ ቃላት እዚህ ይረዳሉ። (የመጽሃፈ ሞርሞን የርዕስ ገጽ)። በሌላ አነጋገር፣ አንድ የቅዱስ መጽሃፍ የእግዚያብሄር ቃል ለመሆን ከሰው ስህተት ነጻ መሆን አይጠበቅበትም።