ኑ፣ ተከተሉኝ
የካቲት 9–15 (እ.አ.አ)። “ኖኅ በጌታ ፊት ሞገስን አገኘ”: ኦሪት ዘፍጥረት 6–11፤ ሙሴ 8


“የካቲት 9–15 (እ.አ.አ)። ‘ኖኅ በጌታ ፊት ሞገስን አገኘ’፣ ኦሪት ዘፍጥረት 6-11፤” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)

“የካቲት 9–15 (እ.አ.አ)። ‘ኖኅ በጌታ ፊት ሞገስን አገኘ’ ኑ፣ ተከተሉኝ—2026 (እ.አ.አ)

እንስሳት መርከቧን ለቀው እየወጡ፣ ኖኅና ቤተሰቡ ደግሞ በዓለት ላይ ቆመው

ያህዌ የገባውን ቃል ይጠብቃል፣ በሳም ሎውለር

የካቲት 9–15 (እ.አ.አ)፡ ”ኖኅ በጌታ ፊት ሞገስን አገኘ”

ኦሪት ዘፍጥረት 6–11ሙሴ 8

በኋለኞቹ ቀናት እንደመኖራችን መጠን፣ ስለ ጥፋት ውሃ ታሪክ ትኩረት የምንሰጥበት ልዩ ምክንያት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአቱን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ባስተማረ ጊዜ ”በኖህ ዘመን እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል” (ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥ 41) ብሏል፡፡ በተጨማሪም እንደ “[የተበላሸች]”፣ “ግፍን የተሞላ[ች]“ የመሳሰሉ የኖህን ዘመን የሚገልጹ ሃረጎች በቀላሉ የኛን ጊዜ ሊገልጹ ይችላሉ (ዘፍጥረት 6፥12–13ሙሴ 8፥28)። በተጨማሪም የባበቢሎን ግንብ ታሪክ ትዕቢትን ተከትሎትም የመጣው ግራ መጋባት እና ክፍፍል ገለጻ ለኛም ዘመን የሚሰራ ይመስላል፡፡

እነዚህ ጥንታዊ ገለጻዎች ውድ የሆኑበት ምክንያት ክፋት በታሪክ ውስጥ ሁሉ እራሱን እንደሚደግም ስለሚያሳዩን ብቻ አይደለም፡፡ ከሁሉም ይበልጥ እነሱን በተመለከተ ምን ማድረግ እንደሚገባን ያስተምሩናል፡፡ ኖህ “በጌታ ፊት ሞገስን አገኘ” (ሙሴ 8:27)። የያሬድ ቤተሰብ እና ወንድሙ ወደጌታ ተመለሱ፣ በባቢሎንም ከነበረው ግራ መጋባት እና መከፋፈል ተጠበቁ ( ኤተር 1፥33–43ን ይመልከቱ)፡፡ ሃቀኘነት ከጎደለው እና ግፍን ከተሞላ ጊዜ ራሳችንን እና ቤተሰባችንን እንዴት እንጠብቃለን ብለን ከተጨነቅን በነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉት ታዋቂ ታሪኮች ብዙ የሚያስተምሩን ነገሮች አሉ፡፡

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 6ሙሴ 8

የሴሚናሪ ምልክት
የጌታን ነቢይ በመከተል መንፈሳዊ ደህንነት ይገኛል፡፡

የኖኅ ዘመን ገለጻ ውስጥ በእኛ ዘመን ካሉት ሁኔታዎች ጋር የሚመሳሰል ነገር ይታያችኋል? በተለይ በሙሴ 8፡15–24፣ 28 ላይ ተመልከቱ። ምን ገጽታዎች ሲደጋገሙ ታያላችሁ?

እናንተ ልታዩት የምትችሉት አንድ አስፈላጊ ተመሳሳይነት እግዚአብሔር ኖኅን ነቢይ አድርጎ እንደጠራው እና ዛሬም ነቢይ እንደሚጠራ ነው። ከሙሴ 8፡13–30 ስለ ነቢያት የተማራችሁትን እውነት ዝርዝር ለማውጣት አስቡ። በህይወት ያሉት ነቢያችን እንደ ኖህ የሆኑት እንዴት ነው? እርግጥ ነው፣ በዛሬው ጊዜ ያሉት የጌታ ነቢይ ስለ ጥፋት ውሃ እያስጠነቀቁን ወይም መርከብ እንድንሠራ እየጋበዙን አይደለም። ነገር ግን የሚያስጠነቅቁን ስለምንድን ነው? ምንስ እንድናደርግ እየጋበዙን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በወንጌል ላይብረሪ ከቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች ውስጥ በተለይ “ግብዣዎች እና ተስፋ የተሰጡ በረከቶች” የሚለውን ክፍል መከለስ ትችላላችሁ። ምናልባት ለእናንተ በጣም አስፈላጊ የሚመስል አንድ ማስጠንቀቂያ እና አንድ ግብዣ መምረጥ ትችላላችሁ።

ሽማግሌ አለን ዲ. ሃይኒ እንዲህ አስተምረዋል፣ “ፍፁም እና አፍቃሪ የሆነው በሰማይ ያለው አባት እውነትን በነቢይ በኩል ለልጆቹ የሚገልጥበትን መንገድ መርጧል።” (“A Living Prophet for the Latter Days,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 25)። የነቢይ መኖር የሰማይ አባት ፍቅር ምልክት ስለመሆኑ ምክንያቶችን በመፈለግ የሽማግሌ ሃይኒን መልእክት ለማጥናት አስቡ። የጌታን ነቢይ መከተል በኋላኛው ቀን ስለመኖር ደህንነት እንዲሰማችሁ የረዳችሁ እንዴት ነው?

እንዲሁም በርዕሶች እና ጥያቄዎች “ነቢያት፣”ን የወንጌል ላይብረሪ፤ “Why Do We Have Prophets?” (ቪዲዮ) በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

1:37

Why Do We Have Prophets?

ዘፍጥረት 6:5-13

የጥፋት ውኃው የእግዚአብሔር የምሕረት ተግባር ነበር።

አንዳንድ ሰዎች የጥፋት ውሃን “ሰው[ን] [ለማጥፋት]” በመላኩ ምክንያት ስለ እግዚአብሔር ፍትሃዊነት ይጠራጠራሉ (ዘፍጥረት 6፡7)። ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል በጥፋት ውሃው ጊዜ፣ “የሃቀኝነት መጥፋት መንፈሶች በፍትህ ወደዚህ ሊላኩ ወደማይችሉበት ደረጃ ማድረሱን” ገልጸዋል (We Will Prove Them Herewith [1982]፣ 58)። በተጨማሪም የጥፋት ውኃው እንዴት የምሕረት ተግባር እንደሆነ ልታስቡ ትችላላችሁ። በዘፍጥረት 6፡5-13 ላይ የጌታን ርኅራኄ እና ለሰዎች ያለውን ፍቅር የሚያሳይ ምን ታገኛላችሁ?

ኦሪት ዘፍጥረት 9፥8–17

ምልክቶች ወይም መታሰቢያዎች ከጌታ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እንዳስታውስ ይረዱኛል።

ዘፍጥረት 9፥8–17መሰረት፣ ቀስተ ደመና ምን እንድታስታውሱ ሊያደርጋችሁ ይችላል? የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 9፥21–25 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ምን ግንዛቤ ይጨምርላችኋል? እንዲሁም ቃል ኪዳኖቻችሁን እንድታስታውሱ እግዚአብሔር የሰጣችሁን የሌሎች ነገሮች (እንደ ምልክቶች፣ ቁሶች ወይም ሌላ ማንኛውም ነገር) ዝርዝር ለማውጣት ልታስቡ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች ምን ያስተምሯችኋል? ለማስታወስ የሚረዷችሁስ እንዴት ነው?

እንዲሁም ጌሪት ደብሊው ጎንግ፣ “Always Remember Him,” ሊያሆና, ግንቦት 2016(እ.አ.አ)፣ 108-11 ይመልከቱ፤ “Reverently and Meekly Now,” መዝሙሮች, ቁ. 185.

ወንዶች ግንብ ላይ በገመድ እና በደረጃ እየወጡ

የባቢሎን ግንብ በዴቪድ ግሪን

ኦሪት ዘፍጥረት 11፥1–9

ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ወደ ሰማይ አባት የሚኬድበት ብቸኛው መንገድ ነው።

የባቢሎን ሰዎች ግንብ የገነቡበት ታሪክ ባለፈው ሳምንት ካጠናችሁት ሄኖክ እና ወገኖቹ ጽዮንን የገነቡበት ታሪክ ጋር ትኩረት የሚስብ ተቃርኖ አለው። ሁለቱም ቡድኖች በተለያየ መንገድ ወደ ሰማይ ለመድረስ እየሞከሩ ነበር። የጽዮን ሰዎች ሰማያትን እንዴት አገኙ? (ሙሴ 7፡18–19፣ 53፣ 62–63፣ 69ን ይመልከቱ)። ከዘፍጥረት 11፡1–9 እና ሔለማን 6፡26–28 ስለ ባቢሎን ሰዎች ምን ተማራችሁ? ይህ ወደ እግዚአብሔር መገኘት ለመመለስ ስለምናደርገው ጥረት ምን ያስተምረናል? “ወደ ሰማይ [እንድንደርስ]” ይረዳን ዘንድ እግዚአብሔር ምን አዘጋጅቶልናል? (ዘፍጥረት 11:4፣ በተጨማሪም ዮሓንስ 3:16 ይመልከቱ)።

በንቃት ተማሩ። መማር ከማንበብ ወይም ከማዳመጥ የበለጠን ነገር ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ፣ ስለ ባቢሎን ግንብ ስትማሩ፣ እናንተ እና ቤተሰባችሁ ወይም ክፍላችሁ ከእግዚአብሔር የሚያርቁንን ነገሮች በወረቀት ላይ ልትጽፉ ትችላላችሁ። ከዚያም፣ በሌላ ብጣሽ ወረቀት ላይ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡንን ነገሮች ትጽፋላችሁ። የመጀመሪያውን የወረቀት ስብስብ በኝብ ቅርጽ፣ የሁለተኛውን ደግሞ በቤተመቅደስ ቅርጽ አደራጁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘፍጥረት 6:14–227–8ሙሴ 8:16–24

የጌታን ነብይ መከተል እኔን እና ቤተሰቤን ይባርካል።

  • አብዛኞቹ ልጆች የኖህን እና የመርከቧን ታሪክ ይወዳሉ። ልጆቻችሁ ስለዚህ የሚያውቁትን እንዲያካፍሉ እድል ለመስጠት አስቡ። እነሱን ለመርዳት፣ በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙትን ሥዕሎች፣ “ኖኅ እና ቤተሰቡ” በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች (22–25)፣ “Follow the Prophet” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 110–11) ሦስተኛውን አዝማች መጠቀም ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የታሪኩን ክፍሎች መተወን ያስደስታቸው ይሆናል፤ ለምሳሌ፡- መርከቡን ለመሥራት መሣሪያ እየተጠቀሙ እንደሆነ በማስመሰል ወይም ወደ መርከቡ ውስጥ እንደሚገቡ እንስሳት በመራመድ።

  • በአንድነት ስለ ኖህ ስታወሩ ልጆቻችሁ ዛሬ ላይ የእግዚአብሔር ነቢይ መኖሩ ምን ያህል በረከት እንደሆነ እንዲያዩ እርዷቸው። የጌታ ነቢያት ዛሬም የሚያስተምሩትን ኖህ ያስተማራቸውን ነገሮች ለማግኘት ልጆቻችሁ ሙሴ 8፡16-24 ላይ እንዲፈልጉ እርዷቸው። እነዚህን ትምህርቶች ስንታዘዝ እንዴት እንባረካለን?

ዘፍጥረት 9:15–16

እግዚአብሔር የገባልኝን ቃል ይጠብቃል።

  • እናንተ ምን እንደሚወክል ስትነጋገሩ ትንንሽ ልጆች ቀስተ ደመና መሳል ወይም ማቅለም ሊያስደስታቸው ይችላል (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 9፥21–25 [የመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ] ይመልከቱ)። እግዚአብሔር፣ ኖኅና ቤተሰቡ ቀስተ ደመና በተመለከቱ ቁጥር ምን እንዲያስቡ ፈልጎ ነበር?

  • በህይወታችሁ ውስጥ አንድ አስፈላጊ ነገርን የሚያስታውሷችሁን ለምሳሌ እንደ የጋብቻ ቀለበት፣ ስዕል ወይም ማስታወሻ ደብተር ያሉ ነገሮችን ለልጆቻችሁ ማሳየት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የራሳቸውን ምሳሌዎች እንዲያካፍሉ አድርጉ። ይህም ቃል ኪዳኖቻችንን እንድናስታውስ ስለሚረዱን ነገሮች፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የጥምቀት ቃል ኪዳናችንን እንድናስታውስ ስለሚረዳን እንደ ቅዱስ ቁርባን ያለ ነገር ውይይት ሊመራ ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75–79ይመልከቱ)።

ድርብ ቀስተ ደመና

ቀስተ ደመናው “በእኔና በእናንተ መካከል… የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት” ይሆናል በማለት እግዚአብሔር ለኖኅ ቤተሰብ ተናግሯል (ዘፍጥረት 9፡12)።

ዘፍጥረት 11፥1–9

ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚወስደው ብቸኛው መንገድ ነው።

  • ከልጆቻችሁ ጋር ከብሎኮች ወይም ከሌሎች ነገሮች ግንብ መገንባት አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይህን ስታደርጉ የባቢሎን ሰዎች ረጅም ግንብ በመገንባት ወደ መንግሥተ ሰማያት መድረስ እንደሚችሉ አስበው እንደነበር አስረዱ። ከዚያም የአዳኙን ሥዕል በአንድነት መመልከት እና ወደ መንግሥተ ሰማያት እንድንገባ እንዴት እንደሚረዳን ልጆቻችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ከዚያም አዳኙን ለመከተል ልታደርጉ ስለምትችሏቸው ነገሮች እርስ በርስ መነጋገር ትችላላችሁ።

  • ዘፍጥረት 11፡1-9 ላይ ያለውን የባቢሎን ግንብ ታሪክ ከማንበብ በተጨማሪ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ሄለማን 6፡28ን ማንበብ ትችላላችሁ። በዚህ ጥቅስ መሠረት የባቢሎን ሰዎች ግንብ የገነቡት ለምንንድነው? ይህንን ግንብ መገንባት ወደ ሰማይ ለመድረስ የተሳሳተው መንገድ የነበረው ለምን ነበር? ከዚያም ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ ትክክለኛውን መንገድ ለማግኘት 2 ኔፊ 31፡20–21ን እና ሔለማን 3፡28ን ማንበብ ትችላላችሁ። ለባቢሎን ሰዎች ምን አይነት ምክር ትሰጣላችሁ?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

የኖህ መርከብ

የኖህ መርከብ በአዳም ክሊንት ዴይadamdayart.com

የልጆች አክቲቪቲ ገጽ፥ ነብዩን መከተል እኔን እና ቤተሰቤን ይባርካል