መጋቢት 16–22 (እ.አ.አ)። ‘እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”፡ ዘፍጥረት 42-50 “ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
መጋቢት 16–22 (እ.አ.አ)። “እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”፡ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ)
ይቅርታ በሜጋን ሪከር
“መጋቢት 16–22 (እ.አ.አ): “እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”
ዘፍጥረት 42–50
ዮሴፍ በወንድሞቹ ወደ ግብጽ ለባርነት ከተሸጠ 22 አመት ገደማ ሆነው። በሃሰት መከሰስን እና መታሰርን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን ዮሴፍ አሳልፏል። በመጨረሻም ወንድሞቹን እንደገና ባያቸው ጊዜ ዮሴፍ ከፈርዖን ቀጥሎ በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ነበረ። በቀላሉ ሊበቀላቸው ይችል ነበረ፣ በዮሴፍ ላይ አድርገውት የነበረው ግምት ውስጥ ሲገባ በቂ ምክንያት ያለውም ሊመስል ይችል ነበር። ሆኖም ዮሴፍ ይቅር አላቸው። ያ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን በስቃዩ መለኮታዊ አላማን እንዲያዩ ረዳቸው። “እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”(ኦሪት ዘፍጥረት 50፥20)ሲል ነገራቸው ምክንያቱም “የአባቱን ቤተሰዎች ሁሉ“ኦሪት ዘፍጥረት 47፥12ከርሃብ ለማዳን የሚያስችል ቦታ ላይ አስቀምጦታልና።
በብዙ መንገዶች ዮሴፍ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። ምንም እንኳን ሃጢያታችን በኢየሱስ ላይ ታላቅ ስቃይ አስከትሎበት የነበረ ቢሆንም ከርሃብ ከከፋ እጣ ፈንታ ሁላችንንም በማውጣት ይቅር ይለናል። ይቅርታ መቀበልም ሆነ መስጠት ቢያስፈልገን—የሆነ ጊዜ ሁላችንም ሁለቱንም ማድረግ ያስፈልገናል—የዮሴፍ ምሳሌ እውነተኛ የፈውስ እና የእርቅ ምንጭ ወደሆነው ወደአዳኙ ይጠቁመናል።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዘፍጥረት 45:5–7፤ 47:12
“እግዚያብሄርም አድናችሁ ዘንድ ከናንተ በፊት ላከኝ።“
በዮሴፍ ሕይወት እና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ተልዕኮ መካከል ተመሳሳይነትን አስተውላችኋል? የእነዚህን መመሳሰሎች አንዳንድ ምሳሌዎችን ለማየት የሚከተሉትን ለማነጻጸር ሞክሩ፡-
-
ዘፍጥረት 37፡3ን ከማቴዎስ 3፡17 ጋር።
-
ዘፍጥረት 37፡26–28ን ከማቴዎስ 26፡14–16 ጋር።
-
ዘፍጥረት 45፡5-7ን ከሉቃስ 4፡18 ጋር።
-
ዘፍጥረት 47:12ን ከዮሐንስ 6፡35 ጋር።
እነዚህን ጥቅሶች በምታነብበት ጊዜ ስለ አዳኙ እና ስለ ተልእኮው ምን ያነሳሳችኋል?
ኦሪት ዘፍጥረት 45፤ 50፥15-21
ይቅርታ ፈውስን ያመጣል።
ዮሴፍ ወንድሞቹ ያደረጉበትን አስከፊ ነገሮች ይቅር ስለማለቱ ማንበባችሁ በአሁኑ ወቅት ይቅር ለማለት ስለተቸገራችሁበት ስለአንድ ሰው እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ይህን መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ስትጥሩ የሚከተሉት ጥያቄዎች ሊረዷችሁ ይችላሉ:
-
ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር ማለት ከባድ ሊሆንበት የሚችለው ለምንድነው? (ያደረጉበትን ለመከለስ ዘፍጥረት 37ን ይመልከቱ)። ዮሴፍን ይቅር ለማለት የሚያስችል ጥንካሬ የሰጡት ምን ዓይነት ተሞክሮዎች ወይም ባህሪዮች ሊሆኑ ይችላሉ? (ለምሳሌ ዘፍጥረት 45፡1–15 ወይም 50፡15–21 ተመልከቱ)።
-
ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር ማለቱ ምን በረከቶችን አስገኝቶለታል? ለምሳሌ፣ በታሪኩ መጀመሪያ ላይ ያለውን የያዕቆብን ቤተሰብ ግንኙነት (ለምሳሌ ዘፍጥረት 7፡3–11 ተመልከቱ) መጨረሻው ላይ ከነበረው ጋር አወዳድሩ (ዘፍጥረት 45፡9–15፤ 50፡15–21 ተመልከቱ)። ዮሴፍ ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ባይሆን ኖሮ ሁኔታዎች ከዚህ የተለየ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው?
-
ይቅርታ ጠየቁም አልጠየቁ የእናንተ ይቅርታ የሚያስፈልገውን ሰው ስም ለመጻፍ አስቡ። የአዳኙን የፈውስ ኃይል ወደዚያ ሁኔታ ለመጋበዝ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ይቅርታ ማድረግ በጣም ከባድ መስሎ ከታያችሁ፣ የሽማግሌ ጌሪት ደብሊው ጎንግን “Happy and Forever” (ሊያሆና ህዳር 2022፣ 85) በተሰኘው መልእክቱ የመጨረሻዎቹ ስድስት አንቀጾች ውስጥ ያለውን ምክር ለመከለስ አስቡ። ይቅር ማለት እንደምትችሉ ተስፋ የሚሰጣችሁን ምን ታገኛላችሁ?
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፡9–11፣ “Forgiveness: My Burden Was Made Light” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
Forgiveness: My Burden Was Made Light
ዘፍጥረት 49
ያዕቆብ ለቤተሰቡ ትንቢታዊ በረከቶችን ሰጥቷል።
የያዕቆብ ለትውልዱ የሰጣቸው በረከቶች ግልጽ ምስሎችን የያዙ ቢሆኑም ለመረዳት ቀላል አይደሉም። ዳግም የተመለሰው ወንጌል ምስጋና ይግባውና ተጨማሪ እርዳታን ይሰጠናል። በ ኦሪት ዘፍጥረት 49፥22–26ለዮሴፍ ስለተሰጠው በረከት ስታነቡ፣የሚከተሉትን ጥቅሶችም አንብቡ፣ እናም ምን ግንዘዛቤ እንደሚሰጡ ተመልከቱ: 1 ኔፊ 15፥12፤ 2 ኔፊ 3፥4–5፤ ያዕቆብ 2፥25፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥44።
በ ዘፍጥረት 49፥8–12 ውሰጥ ያለውን የይሁዳን በረከት ስታነቡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ የዘር ሃረግ መሆኑን አስታውሱ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ አዳኙ የሚያስታውሳችሁን ምን ታገኛላችሁ? (በተጨማሪም ራዕይ 5፡5–6፣ 9፤ 1 ኔፊ 15፡14–15፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፡59፤ 133፡46–50 ተመልከቱ)።
እነዚህን በረከቶች ማንበብ የፓትርያርክ በረከቶቻችሁን እንድትከልሱ—ወይም ከሌላችሁ እንድትቀበሉ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። በበረከታችሁ ውስጥ ሀሳቦቻችሁን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመልሱት የትኞቹ ቃላት እና ሀረጎች ናቸው?
በተጨማሪም ራንዳል ኬ. ቤኔትን፣ “Your Patriarchal Blessing—Inspired Direction from Heavenly Father,” ሊያሆና ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 42–44 ይመልከቱ።
ዘፍጥረት 50:19–21
እግዚአብሔር በመከራዎቼ ውስጥ ትርጉም እንዳገኝ ሊረዳኝ ይችላል።
ዮሴፍ እያለፈ በነበረበት ወቅት ግልጽ ባይሆንለትም በስተመጨረሻ በግብፅ የነበረውን መከራ ወደ ኋላ መለስ ብሎ በመመልከት “እግዚአብሔር ለመልካም [እንዳሰበው]” (ዘፍጥረት 50፡20) ለማየት ችሏል። ዮሴፍ በጉድጓድ ውስጥ ወይም በእስር ቤት ውስጥ እያለ ልትጠይቁት ብትችሉ ኖሮ እንዴት ታጽናኑት ነበር? ዘፍጥረት 50:19–21 በመከራችሁ ጊዜ ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?
እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122 ይመልከቱ፤ “How Firm a Foundation,” መዝሙሮች፣ ቁ.85.
ጆሴፍ ስሚዝ በነቢያት መካከል፣ በፖል ማን (ዝርዝር)
ዘፍጥረት 50:24-25
“ባለራዕይን ጌታ አምላኬ ያስነሳል።“
ዘፍጥረት 50፡24–25 እና የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 50፡24–38 (በመፅሃፍ ቅዱስ አባሪ) ስታነቡ፣ ከብዙ ምዕተ አመታት በፊት ዮሴፍ ስለ ሙሴ እና ጆሴፍ ስሚዝ ማወቁ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ አስቡ። ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዮሴፍ ስለ እሱ የተናገራቸውን ትንቢቶች እንዴት ፈጸመ? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፡17–23፤ 20፡7–12፤ 39፡11፤ 135፡3 ተመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘፍጥረት 42–44; 45:4–15
ለቤተሰቤ ፍቅር እና ይቅርታ ማሳየት እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁ ዮሴፍ ከቤተሰቡ ጋር የተገናኘበትን ታሪክ መተወን ሊያስደስታቸው ይችላል (ዘፍጥረት 42–44 ይመልከቱ)። ወይም ደግሞ ታሪኩን እርስ በርስ ለመማማር “ዮሴፍ እና ረሃቡ” (በየሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 57-60) ወይም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች ሊጠቀሙ ይችላሉ። ልጆቻችሁ ከታሪኩ እንዲማሩ ሊረዷቸው የሚችሉ አንዳንድ ጥያቄዎች እዚህ ይገኛሉ፡
-
ዮሴፍ ለቤተሰቡ ፍቅር ለማሳየት ምን አደረገ? (ዘፍጥረት 45፡4–15 ይመልከቱ)።
-
ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር ያለው ለምን መስሎ ይሰማችኋል?
-
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍ ይቅር እንዳላቸው ሲያውቁ ምን የተሰማቸው ይመስላችኋል? በህይወታችሁ ውስጥ ማን ይቅር ሊባል ይገባዋል? ፍቅርና ይቅርታን ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
2:26Joseph and the Famine
-
ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ “ልጆቼ ለመማር ምን ያደርጋሉ?” በማለት ጠይቁ። ለምሳሌ፣ በዚህ አክቲቪቲ ውስጥ ልጆቻችሁ አንድን ታሪክ እየተወኑ ወይም እንደገና እየነገሩ ነው። ይህን ማድረጋቸው የተከሰተውን እና በታሪኩ ውስጥ ያሉትን የወንጌል መርሆች እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል።
-
እናንተ ወይም ልጆቻችሁ አንድን ሰው ይቅር ያላችሁበትን ወይም ይቅር ያላችሁን ጊዜ ተሞክሮ ለመካፈል ትፈልጉ ይሆናል። ከዚያም እንደ “Love One Another” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 136) ወይም “Help Me, Dear Father” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 99) ያለን መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።
ዘፍጥረት 48:8-9
ጌታ በክህነት በረከቶች አማካኝነት ይረዳኛል።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ያዕቆብ ልጆቹን ሲባርክ የሚያሳይበትን ምስል በዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ በመመልከት እየሆነ ያለውን ነገር መወያየት ትችላላችሁ (ዘፍጥረት 48፡8-9 ይመልከቱ)። ካስፈለገ፣ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ ለቤተሰቡ የክህነት በረከቶችን መስጠት እንደፈለገ አስረዱ። ምናልባት በክህነት በረከት በኩል ከእግዚአብሔር እርዳታ ስትቀበሉ ያጋጠማችሁን ማንኛውንም ልምድ አንዳችሁ ለሌላው ልታካፍሉ ትችላላችሁ። የክህነት በረከት ልንጠይቅ የምችልባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ምንድናቸው?
ዘፍጥረት 45:5-11
የሰማይ አባት እኔን ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከ።
-
ዮሴፍ ቤተሰቡን ከረሃብ ባዳነበት ታሪክ ውስጥ ልጆቻችሁ አዳኙን እንዲያዩ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? ዮሴፍ እና ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰኙ ሁለት ረድፎችን ያሉትን ቻርት ለመሥራት አስቡ። ልጆቻችሁ ዮሴፍና ኢየሱስ የሚያመሳስሏቸውን ነገሮች በቻርቱ ላይ በመሙላት የሚከተሉትን ጥንድ ጥቅሶች እንዲያጠኑ እርዷቸው: ዘፍጥረት 37:3 እና ማቴዎስ 3:17፤ ዘፍጥረት 37፡26–28 እና ማቴዎስ 26፡14–16፤ ዘፍጥረት 45:5–7 እና ሉቃስ 4:18 እና ዘፍጥረት 47፡12 እና ዮሐንስ 6፡35።
-
አንድን ሰው ማዳን ወይም ማስመለጥ ምን ማለት እንደሆነ ልጆቻችሁን ጠይቁ። ከመካከላቸው አንዳቸው የመዳን ወይም ከአደጋ የማምለጥ ገጠመኝ ካላቸው እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ዮሴፍ ወንድሞቹን ያዳነው እንዴት ነው? ( ዘፍጥረት 42:1–3፤ 45:5–7 ይመልከቱ)። ከዚያም የአዳኙን ምስል አንድ ላይ በማየት ልጆቻችሁ ኢየሱስ እንዴት እንደሚያድነን እንዲናገሩ መጠየቅ ትችላላችሁ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።