”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች: የእስራኤል ቤት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) 2026 (እ.አ.አ)
የእስራኤል ቤት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች
የእስራኤል ቤት
በምስራቃዊ ከነአን ምድረ በዳ አንድ ቦታ ያዕቆብ ከመንታ ወንድሙ ከኤሳው ጋር ለመገናኘት በጭንቀት ጠበቀው፡፡ ከሃያ አመታት ቀደም ብሎ ያዕቆብ ለመጨረሻ ጊዜ ኤሳውን ባየው ጊዜ ኤሳው ሊገድለው ይፈልግ ነበር፡፡ ያዕቆብ የእግዚአብሄርን በረከት እየጠየቀ ለሊቱን ሙሉ ሲታገል አደረ፡፡ በያዕቆብ እምነት፣ ጽናት እና ቁርጠኝነት ምክንያት እግዚአብሄር ጸሎቱን መልሶለት ነበር፡፡ በዚያ ምሽት የያዕቆብ ስም “ከእግዚአብሄር ጋር የሚታገል የሚል ትርጉም ካለው“ ወደ እስራኤል ተቀየረ፡፡ (ዘፍጥረት 32፥28፣የግርጌ ማስታወሻ ለ፣ በተጨማሪም
ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ አጠገብ እስራኤል የሚለውን ስም ተቀበለ፡፡
እስራኤል የሚለው ስም በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው፤እናም በመላው መጽሃፍ እና በመላው ታሪክ ጸንቶ የኖረ ስም ነው፡፡ ስሙ ብዙም ሳይቆይ ከአንድ በላይ ሰዎችን ማመልከት ጀመረ፡፡ እስራኤል 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት፣እናም በጥቅሉ “የእስራኤል ቤት“፣“የእስራኤል ነገዶች“፣ “የእስራኤል ልጆች“ ወይም “እስራኤላውያን“ በመባል ይጠራሉ፡፡
በመላው ታሪክ ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ውስጥ ለመጡበት ለአንዱ የዘር ሃረጋቸው ትልቅ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ትውልዳቸው የቃልኪዳን ማንነታቸው አስፈላጊ ክፍል ነበር፡፡ ሃዋርያው ጳውሎስ “የቢንያም ወገን“ እንደነበረ ተናግሯል፡፡(ሮሜ 11፥1)፡፡ ሌሂ የነሃስ ሰሌዳዎቹን እንዲያመጡ ልጆቹን ወደ ኢየሩሳሌም በላከ ጊዜ አንደኛው ምክንያቱ ሰሌዳዎቹ “ የአባቶቹን የትውልድ ሃረግ“ ስለያዙ ነበር (1 ኔፊ 5፥14)። ሌሂ የዮሴፍ ዘር መሆኑን አወቀ እንዲሁም የእርሱ ትውልድ ከእስራኤል ቤት ጋር ስላላቸው ዝምድና ግንዛቤ በመጪዎቹ አመታት ለእነርሱ አስፈላጊ መሆኑ ተረጋገጠ።
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ “ የእስራኤል መሰባሰብ“ በመሳሰሉትን አገላለጾች ስለ እስራኤል ልትሰሙ ትችላላችሁ፡፡ ስለ“እስራኤል አዳኝ“ “የእስራኤል ተስፋ“ እና “እናንተ የእስራኤል ሽማግሌዎች“ እንዘምራለን፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ረገድ ስለጥንቷ እስራኤል መንግስት ወይንም እስራኤል ስለምትባለው ስለዘመናችን አገር ብቻ እያወራን እና እየዘመርን አይደለም፡፡ ይልቁን ከአለም ሃገራት ወደ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እየተሰበሰቡ ስለሉት ነው። በእግዚአብሄር ጽኑ ስለሆኑት፣በረከቶቹን በትጋት ስለሚፈልጉት እናም በጥምቀት አማካኝነት የእርሱ የቃል ኪዳን ህዝቦች ስለሆኑት ነው እያወራን ያለነው። በፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን አገላለጽ የእስራኤል መሆን ማለት “በህይወታችን እግዚአብሄር እንዲያሸንፍ … እግዚአብሄር በህወታችን ውስጥ ሃይለኛ ተጽዕኖ አድራጌ እንዲሆን መፍቀድ” ማለት ነው።
የፓትርያርክ በረከታችሁ ከአንዱ የእስራኤል ቤት ነገድ ጋር ግንኙነት እንዳላችሁ ይናገራል። ያ ከአንድ አስደሳች የቤተሰብ ታሪክ መረጃ በላይ ነው። ከዛሬያችሁ እና ከወደፊታችሁ ጋርም የተያያዘ ነው። የእስራኤል ቤት አካል መሆን ማለት ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የቃልኪዳን ግንኙነት አላችሁ ማለት ነው። እንደ አብርሃም ለእግዚአብሄር ልጆች ”በረከቶች” መሆን አለባችሁ ማለት ነው(ኦሪት ዘፍጥረት 12፥ 2፤ አብርሃም 2፥ 9–11)። በጴጥሮስ አንደበት “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፣የንጉስ ካህናት ቅዱስ ህዝብ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ“ ማለት ነው(1 ጴጥሮስ 2፥9)። እናንተ “እግዚአብሄር እንዲያሸንፍ የምትፈቅዱ”—ከእርሱ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማክበር “በእግዚያብሄር የምትጸኑ“ ናችሁ ማለት ነው።
የያዕቆብ (እስራኤል) የቤተሰብ ሃረግ፣ በብረንት ኢቫንስ