“ህጻኑ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ህጻኑ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፀአት 1–2
ህጻኑ ሙሴ
የወደፊቱን የእስራኤል መሪ መጠበቅ
የያዕቆብ ቤተሰብ በግብፅ ውስጥ ታላቅ ህዝብ ሆኑ እስራኤላውያን በሚባል ስም ይታወቁ ነበር። የግብፅ ንጉስ ፈርዖንም አንድ ቀን እስራኤላውያን በጣም ይባዛሉ እና ግብፅን ይወርሳሉ ብሎ ፈርቶ ነበር፣ ስለዚህ እስራኤላውያንን ባሪያዎቹ አደረገ።
ዘጸአት 1፥7–14
ከዚያም ፈርዖን አዲስ የሚወለዱ የእስራኤል ወንድ ልጆች እንዲገደሉ አዘዘ። የእስራኤላውያን ቤተሰቦችም በጣም ፈርተው ነበር።
ዘጸአት 1፥15–22
ዮካብድ የምትባል አንድ እስራኤላዊት እናት አዲስ የተወለደውን ወንድ ልጇን የምታድንበትን መንገድ አሰበች። ህጻን ልጇን በቅርጫት ውስጥ አስገብታ ቅርጫቱን በአባይ ወንዝ ዳርቻ ባለው ረዥም ሣር ውስጥ ደበቀችው። የህጻኑ እህት ማሪያም የእርሱን ደህንነት ለመጠበቅ ትከታተለው ነበር።
ዘጸአት 2፥1–4
በወንዙ ውስጥ እየታጠበ ሳለች፣ የፈርዖን ሴት ልጅ ቅርጫቱን አገኘችው። አቅመ ቢስ የሆነው የእስራኤላውያን ህፃን ልጅ እያለቀሰ አየች እና እንደራሷ ልጅ ልታሳድገው ፈለገች። ማሪያም ወደ ፈርዖን ሴት ልጅ መጥታ ሕፃኑን የምትንከባከብ አንዲት እስራኤላዊት ሴት ማምጣት ትችል እንደሆነ ጠየቀች።
ዘጸአት 2፥5–6
ማሪያም እናቷን ዮካብድን ወደ ፈርዖን ሴት ልጅ አመጣች። ህጻኑን ትንከባከበው ዘንድ የፈርዖን ሴት ልጅ ለዮካብድ ለመክፈል ተስማማች።
ኦሪት ዘጸአት 2፥8–9
እስራኤላዊው ህጻን ልጅ አደገ። የፈርዖን ሴት ልጅ እንደ እራሷ ልጅ አሳደገችው። እሷም ሙሴ ብላ ጠራችው።
ዘፀአት 2፥10፡