“ያዕቆብ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ያዕቆብ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 27–33
ያዕቆብ እና ቤተሰቡ
ጌታ ቃል ኪዳኖቹን እንዴት እንደሚጠብቅ
ያዕቆብ ከተቆጣው ወንድሙ ዔሳው ለማምለጥ ቤቱን ለቆ ሄደ። የያዕቆብ አባትም ጌታን የምታፈቅር እና ትእዛዛቱን የምታከብር ሴት እንዲያገኝና እንዲያገባ ባረከው።
ዘፍጥረት 27፥42–46፤ 28፥1–5
ያዕቆብ በጉዞ ላይ እያለ፣ ጌታ በራዕይ ጎበኘው። ሁልጊዜ ከያዕቆብ ጋር እንደሚሆንም ቃል ገባለት። ያዕቆብ ከተቀበለው ሁሉ አስራቱን ለጌታ ለመስጠት ቃል ገባ።
ዘፍጥረት 28፥10–16፣ 20–22
ጌታም ያዕቆብ ብዙ ልጆች እንደሚወልድ ቃል ገባለት። በያዕቆብ ልጆች በኩል፣ የምድር ቤተሰቦች አዳኙን በማወቅ ይባረካሉ። በኋለኛው ቀናትም የያዕቆብ ቤተሰብ የእስራኤል ቤት ተብለው ይታወቃሉ።
ዘፍጥረት 28፧3–4፣ 14፤ 1 ኔፊ 10፥14
ያዕቆብ ወደ ሐራን ምድር ተጓዘ። በዚያም ራሔል የምትባል አንዲት ጻድቅ ሴትን አፈቀረ።
ዘፍጥረት 27፥43፤ 29፥9–20
ያዕቆብም ላባን ራሔልን እንዲያገባ ከፈቀደለት፣ ለአባቷ ላባን ለሰባት ዓመት ለመሥራት ተስማማ። ላባንም ተስማማ። ያዕቆብ ለሰባት አመት ሰራ።
ዘፍጥረት 29፥21–27
ላባን ግን የመጀመሪያዋ ልጁ ልያ በመጀመሪያ እንድታገባ ፈለገ። በሠርጉ ወቅት ላባን ያዕቆብን በማታለል በምትኩ ልያን እንዲያገባ አደረገ። ነገር ግን ያዕቆብ ራሔልን ያፈቅር ነበር። እርሷንም ማግባት ከቻለ ሌላ ሰባት ዓመት እንደሚሠራ ቃል ገባ። ላባንም ተስማማ፣ እናም የያዕቆብ ቤተሰብ ማደግ ጀመረ።
ዘፍጥረት 29፥28–35፤ 30፥3–13፣ 17–24፤ ያዕቆብ 2፥27–30
ላባንም ያዕቆብን በትክክል አልከፈለውም። ነገር ግን ጌታ ያዕቆብን በብዙ እንስሳት ባረከው እናም ወደ ቤት እንዲመለስ ነገረው።
ዘፍጥረት 30፥31፣ 43፤ 31፥1–7፣ 17–18
ወደ ቤቱ በመጓዝ ላይ እያለም፣ ያዕቆብ ወንድሙ ዔሳውና 400 ሰዎች ሊገናኙት እንደመጡ ተረዳ።
ዘፍጥረት 32፥3–6
ያዕቆብም ዔሳው በእርሱ ላይ አሁንም ተቆጥቶ ሳይሆን እንዳልቀረ አሰበ። ያዕቆብ ለቤተሰቡ ደህንነት ፈራ፣ ስለዚህ ወደ ደህና ቦታ ወሰዳቸው እናም ጸለየ።
ዘፍጥረት 32፥7–24
ያዕቆብ ለሊቱን ሙሉ እንዲሁም እስከ ጠዋት ድረስ ጸለየ። ጌታ ያዕቆብን ጎበኘና ባረከው። እርሱም የብዙዎች ታላቅ መሪ እንደሚሆንም ጌታ ነገረው። ጌታም የያዕቆብን ስም ወደ እስራኤል ለወጠው።
ዘፍጥረት 32፥24–30
ወዲያውኑም ዔሳው እና ሰዎቹ ያዕቆብን እና ቤተሰቡን አገኙ። ዔሳው በያዕቆብ ላይ አልተቆጣም ነበር። ከያዕቆብ ጋር ለመገናኘት ሮጠ እናም አቀፈው። እርሱን ለማየት እና ከቤተሰቡ ጋር ለመገናኘትም በጣም ተደስቶ ነበር። ያዕቆብም ዔሳውን እንደገና በማየቱ ተደስቶ ነበር።
ዘፍጥረት 33፥1–7
ጌታ ለያዕቆብ የገባቸውን ቃል ኪዳኖች በህይወቱ ሙሉ ጠበቀ። ያዕቆብ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አገሩ ደረሰ በዚያም ሰፈረ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ ተጠራ፣ እናም ቤተሰቦቹም እስራኤላውያን ተባሉ። ትእዛዛትን ማክበሩን እና ጌታን ማምለኩን ቀጠለ።
ዘፍጥረት 33፥17–20