“እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘጸአት 16
እስራኤላዊያን በምድረበዳ ውስጥ
በጌታ ላይ መደገፍን መማር
እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ብዙም ሳይቆይ በቂ ምግብ የለንም በማለት አጉረመረሙ። በምድረበዳ ከመራብ ይልቅ በግብፅ ባሪያ መሆን ይሻላል አሉ።
ዘጸአት 16፥1–3
እርሱን እንዲያምኑ እስራኤላውያንን ለማስተማር፣ ጌታ በየቀኑ ይሰበስቡት ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ላከላቸው። እንጀራውን መና ብለው ጠሩት። ጣእሙ እንደ ማር ነበር። ጌታ በሰንበት፣ በሳምንቱ ሰባተኛው ቀን መና አልላከም ነበር። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን፣ ለሁለት ቀናት በቂ መና እንዲሰበስቡ ነገራቸው።
ዘጸአት 16፥4–5፣ 14–31።
ለተወሰነ ጊዜም፣ ጌታ እስራኤላውያን እንዲበሏቸው ድርጭትን ልኳል። ጠዋት ላይ መና ሰበሰቡ እናም በምሽት ላይ ድርጭቶችን ሰበሰቡ። ጌታ እስራኤላውያን በእርሱ መታመንን እንዲማሩ ፈልጎ ነበር። በዚህ መንገድ እነርሱን በምድረበዳ ውስጥ ተንከባከባቸው።
ዘጸአት 16፥11–13