ኑ፣ ተከተሉኝ
መጋቢት 30–ሚያዝያ 5 (እ.አ.አ) “ሞትን ለዘላለም ይውጣል“: ትንሳኤ


“መጋቢት 30–ሚያዝያ 5 (እ.አ.አ) ’ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣’ ትንሳኤ፡” ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች: ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) 2026 (እ.አ.አ)

“መጋቢት 30–ሚያዝያ 5 (እ.አ.አ) ’ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣’ ኑ፥ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ባዶ መቃብር

የባዶ መቃብር ምስል

መጋቢት 30–ሚያዝያ 5 (እ.አ.አ): “ሞትን ለዘላለም ይውጣል“

ትንሳኤ

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት “የሁሉም የሰው ልጆች ታሪክ እምብርት ነው“ (“The Living Christ: The Testimony of the Apostles፣” የወንጌል ላይብረሪ)። ያ ማለት ምን ማለት ነው? በከፊል፣ የአዳኙ ህይወት በእያንዳንዱ እስከዛሬ በኖረ ወይም ወደፊት በሚኖር የሰው ልጅ ዘላለማዊ ፍጻሜ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ማለት ነው፡፡ በዚያ የመጀመሪያ የፋሲካ እሁድ በትንሳኤው የተደመደመው የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ተልዕኮ በመላው ታሪክ ውስጥ ሁሉንም የእግዚያብሄር ህዝቦች ያገናኛል ልትሉም ትችላላችሁ: ከክርስቶስ በፊት የተወለዱት በእምነት በጉጉት ጠብቀውት ነበር ፤( ያዕቆብ 4፥4ይመልከቱ) እንዲሁም ከዚያ በኋላ የተወለዱት እርሱን በእምነት ወደኋላ ያስቡታል፡፡ የብሉይ ኪዳን ዘገባዎችን እና ትንቢቶችን ስናነብ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም አናገኝም ነገር ግን የጥንት አማኞች ለመሲሃቸው እና ለአዳኛቸው የነበራቸውን እምነት እና ናፍቆት ማስረጃ እናያለን፡፡ ስለዚህ እኛ እርሱን ለማስታወስ የተጋበዝን እርሱን በጉጉት ከጠበቁት ጋር ያለን ግንኙነት ሊሰማን ይችላል፡፡ በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ“ የሁላችንንበደል በእርሱ ላይ አኖረ“ (ኢሳይያስ 53፥6፤ አጽናኦት ተጨምሮበታል) እንዲሁም ”ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ”(1 ቆሮንቶስ 15፥22፤ አጽናኦት ተጨምሮበታል)

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የጥንት እንዲሁም የዘመናችን ነቢያት ስለአዳኙ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት ይመሰክራሉ።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ምንባቦች ወደ አዳኙ አገልገግሎት እና የሃጢያት ክፍያ ይጠቁማሉ። የሚከተለው ሰንጠረዥ እነዚህን አንዳንድ ምንባቦች ይዘረዝራል። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ስለአዳኙ ምን ሃሳብ ይመጣላችኋል?

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዘካሪያስ 9፥9

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 21፥1–11

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዘካሪያስ 11፥12-13

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 26:14–1627:3–8

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ኢሳይያስ 53:4

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 8፥16–1726፥36–39

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ኢሳይያስ 53፥7

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 14፥60–61

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 22፥16

አዲስ ኪዳን

ዮሃንስ 19፥17–1820፥25–27

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 22፥18

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥35

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 69፥21

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥34፣ 48.

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 118፥22

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 21፥42

ብሉይ ኪዳን

ኢሳይያስ 53፥9፣12

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥57–60ማርቆስ 15፥27–28

ብሉይ ኪዳን

ኢሳይያስ 25፥8

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 16፥1–6ሉቃስ 24፥6

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዳንኤል12፥2

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥52–53

ስለአዳኙ የሚያስተምሩ ትንቢቶች በመጽሃፈ ሞርሞን ውስጥ እጅግ ብዙ እና ግልጽ ናቸው፡፡ እምነታችሁ እንደዚህ ባሉ ጥቅሶች እንዴት እንደሚጠናከሩ አስቡ: 1 ኔፊ 11፥31–332 ኔፊ 25፥13ሞዛያ 3፥2–11አልማ 7:10–13

የኋለኛው ቀን ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ኃጢያት ክፍያው ተልእኮ ልዩ ምስክርነት መስጠትቸውን ቀጥለዋል። በዚህ የትንሳኤ ቅዳሜና እሁድ አጠቃላይ ጉባኤን ስታዳምጡ፣ የምትሰሙትን የክርስቶስን ምስክርነቶች አስተውሉ። ስለ እርሱ ምን ያስተምሯችኋል?

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ እና ደስታን ይሰጠኛል።

የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ የምናከብርበት ጊዜ ስለሆነ ፋሲካ አስደሳች ጊዜ ነው። ሆኖም ግን፣ በፋሲካ ወቅት እንኳን በተለያዩ ምክንያቶች ደስታ የማይሰማቸው ብዙ ሰዎች አሉ። በዚህ ፋሲካ የአዳኙን ሰላም እና ደስታ ተደራሽ ለማድረግ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

አንዱ ሃሳብ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚሰጠው ሰላምና ደስታ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እነዚህን የመሳሰሉ መልዕክቶችን በማግኘት ነው፡ መዝሙር 16፡8–1130:2–5ኢሳይያስ 1225:8–940:28–31ዮሐንስ 14:2716:33አልማ 26፡11–22። እነዚህን መልዕክቶች ለሌሎች እንዴት ማጋራት እንደምትችሉ አስቡ። ለምሳሌ በእነዚህ መልዕክቶች ላይ በመመስረት የትንሳኤ ካርዶችን በማዘጋጀት ማጋራት ትችላላችሁ። የትንሳኤ ሰላምታችሁን ማን መቀበል እንዳለበት ጸልዩበት። እንዲሁም ብዙ ሰዎች ሊያዩዋቸው በሚችሉበት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክቶቻችሁን ለማጋራት ልትወስኑ ትችላላችሁ።

ስለ ክርስቶስ እና ትንሳኤ እንደ “He Is Risen!” (መዝሙር፣ ቁ. 199) ያሉ መዝሙሮች እንዲሁም በፋሲካ ሰላም እና ደስታ እንዲሰማን ሊረዱን ይችላሉ። በመዝሙሩ ውስጥ በእናንተ አመለካከት የፋሲካን ደስታ ይገልጻሉ ብላችሁ የምታስቡትን ሀረጎች ፈልጉ።

እንዲሁም ጄፍሪ አር. ሆላንድ “Not as the World Giveth,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 35–38፤ ማርክ ኤስ ፓልመር፣ “Our Sorrow Shall Be Turned into Joy,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021(እ.አ.አ)፣ 88–90 ይመልከቱ።

ኢየሱስ ከመቃብሩ ውጭ ለማርያምን ሰላምታ እያቀረበ

ለምን ታለቅሺያለሽ፣ በሳይመን ዴዌይ 2021 (ዝርዝር)።

በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጢያትን፣ ሞትን፣ መከራን እና ድካምን እንዳሸንፍ ሊረዳኝ ሃይል አለው፡፡

በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው በኩል የሚመጡትን ብዙ በረከቶች እንድታዩ የሚረዳችሁ አክቲቪቲ እዚህ ይገኛል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንድናሸንፍ ስለሚረዳን ነገር ከዚህ በታች ያሉትን ጥቅሶች አንብቡ። ምንባቦቹን ወደሚከተሉት ለመከፋፈል ሞክሩ፡ ኃጢአት፣ ሞት፣ ፈተናዎች እና ድክመቶች (አንዳንድ ምንባቦች ከአንድ በላይ ምድብ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ)። ስታነቡ ስለ አዳኙ ኃይል ምን አይነት ግንዛቤ ታገኛላችሁ?

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ክርስቲያን ላልሆነ ጓደኛችሁ እንዴት ታስረዳላችሁ? የሽማግሌ አህመድ ኤስ ኮርቢት መልእክት “Do You Know Why I as a Christian Believe in Christ?” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)) ሊረዳ ይችላል።

እንዲሁም ሬይና 1 አቡርቶ፣ “The Grave Has No Victory,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 85–87፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ”፣ “ትንሳኤ”፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ለማዳን የመጨረሻውን ዋጋ ከፍሏል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ለማዳን ስለከፈለው ዋጋ ከሚከተሉት ጥቅሶች ምን ትማራላችሁ፡ ኢሳይያስ 53፡3–5ሞዛያ 3:7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፡16–19? የሰማይ አባትስ ምን ዋጋ ከፈለ? ( ዮሃንስ 3:16ን ይመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኔ መከራን ተቀብሏል እንዲሁም ሞቷል።

  • የፋሲካ ሳምንት አዳኙ በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ ስላደረገልን ነገር ልጆቻችሁን ለማስተማር ጥሩ ጊዜ ነው። ከታች ያሉትን ሥዕሎች በማሳየት እና በሥዕሎቹ ላይ እየሆነ ስላለው ነገር እንዲናገሩ በማድረግ መጀመር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ሥዕሎቹን እየተመለከቱ ሳለ እነዚህን ክንውኖች የሚገልጹ ጥቅሶችን ማንበብ ትችላላችሁ (ማቴዎስ 26፡36–4627፡35–50ሉቃስ 22፡39–46ዮሐንስ 19፡16–30 ተመልከቱ)። ልጆቻችሁ በጥቅሶቹ ውስጥ የሚሰሙትን ዝርዝር ገለጻ በሥዕሎቹ ላይ ሊጠቁሙ ይችላሉ።

የኢየሱስ ምስል በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ

ግራ፡ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ፣ በሃሪ አንደርሰን። ቀኝ፡ ስቅለት፣ በሃሪ አንደርሰን

  • ኢየሱስ ለእኛ ሲል በከፈለው መስዋዕትነት ምክንያት የተባረክነው እንዴት ነው? በኢሳይያስ 53፡4–12አልማ 7፡11–13 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፡16–19 ውስጥ ልጆቻችሁ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጡ ቃላቶችን እና ሀረጎችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ ስለአዳኙ ያላችሁን ስሜት አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ከሞት ተነስቷል።

  • የትንሣኤን ታሪክ ለልጆቻችሁ ለመንገር የዚህን ሳምንት የአክቲቪት ገጽ ወይም ሌሎች ሥዕሎችን መጠቀም ትችላላችሁ (በተጨማሪም “ኢየሱስ ተነስቷል”፣ በየአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 139-44 ይመልከቱ)። ከዚያም ልጆቻችሁ ታሪኩን ደግመው እንዲነግሯችሁ አድርጉ።

  • በዚህ ፋሲካ ልጆቻችሁ በክርስቶስ ደስታን እንዲያገኙ እንዴት መርዳት እንደምትችሉ አስቡ። ለምሳሌ፣ እንደ “Christ the Lord Is Risen Today” (መዝሙሮች፣ ቁ. 200) ወይም “Gethsemane” (የወንጌል ላይብረሪ) ያሉ ተወዳጅ የትንሳኤ መዝሙሮችን አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ። ስለ ትንሳኤ ሌሎች መዝሙሮችን ለማግኘት በ መዝሙሮች እና የልጆች መዝሙር መጽሃፍ ርዕስ ማውጫ ፈልጉ። እናንተ እና ልጆቻችሁ ለምን እነዚህን መዝሙሮች እንደምትወዷቸው እና ስትዘምሯቸው ምን እንደሚሰማችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እነዚህ መዝሙሮች ስለሰማይ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሩናል?

ልጆች መንፈስ ሊሰማቸው ይችላል፣ ነገር ግን የእርሱን ተፅዕኖ ለመገንዘብ እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ። መንፈስ ከእኛ ጋር የሚነጋገርባቸውን የተለያዩ መንገዶች ለልጆች አስተምሩ። እርሱ ሲናገራቸው የእርሱን ድምፅ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ይህ በሕይወታቸው ውስጥ ግላዊ ራዕይን የመሻት እና የመተግበር ልምድን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 32)። ለምሳሌ፣ ከልጆቻችሁ ጋር ስለ አዳኙ ስትዘምሩ፣ የእሱን ምስሎች ተመልከቱ ወይም የእርሱን ታሪኮች አንብቡ፣ ያላችሁንም መንፈሳዊ ስሜት አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።

  • የወንጌል ላይብረሪ ልጆቻችሁ ሊደሰቱባቸው የሚችሉ Easter videos[የፋሲካ ቪዲዮዎች] ስብስብ አለው። ምናልባት የሚመለከቱትን እንዲመርጡ ልትፈቅዱላቸው ትችላላችሁ። ከቪዲዮው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደተማሩ ጠይቋቸው። እንዲሁም የቪዲዮውን መልእክት በአንድ ዓረፍተ ነገር እንዲያጠቃልሉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ።

ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ኃጢያት ክፍያው ይመሰክራሉ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በዚህ የፋሲካ ቅዳሜና እሁድ አጠቃላይ ጉባኤን ስትመለከቱ፣ የአዳኙ ልዩ ምስክሮች የትንሳኤ ምስክርነትን ሲሰጡ እንዲያስተውሉ እርዷቸው። እንደ ፋሲካ ወይም የኃጢያት ክፍያ ወይም ትንሳኤ ያሉ ቃላትን በሰሙ ቁጥር እንዲቆሙ በማድረግ መጫወት ትችላላችሁ። በህይወት ያሉ ነቢያት ስለ አዳኙ ስለሚሰጡት ምስክርነት ለምን አመስጋኞች እንደሆናችሁ አንዳችሁ ለሌላው አካፍሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

የኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ሥዕል

ለዚህ ዓላማ፣ በዮንግሰንግ ኪም havenlight.com

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፥ ኢየሱስ ለእኔ ከሞት ተነስቷል