“ሚያዝያ 20–26 (እ.አ.አ)። ‘ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን’፡ ዘጸአት 19–20፤ 24፤ 31–34“ ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች: ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
“ሚያዝያ 20–26 (እ.አ.አ)። ‘ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፣’“ ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች::ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ሙሴ እና ጽላቶች፣ በጄሪ ሀርስተን (ዝርዝር)
ሚያዝያ 20–26 (እ.አ.አ): “ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን“
ዘጸአት19–20፤ 24፤ 31–34
የእስራኤል ልጆች ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ቢያጉረመርሙም እንዲሁም ቢወላውሉም፣ በሲና ተራራ ስር ሙሴ ህጉን ሲያነብ፣ ይህንን ቃል ኪዳን ገቡ፥ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም” (ዘጸአት 24፥7)። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ተራራው ጠራው፣ “በመካከላቸውም አድር ዘንድ” በማለት መቅደስ እንዲሰራ ነገርው (ዘጸአት 25፥8)።
ነገር ግን ሙሴ በተራራው አናት ላይ እስራኤላውያን በመካከላቸው የእግዚአብሔር መገኘት እንዲኖር እየተማረ እያለ እስራኤላውያን ያመልኩ ዘንድ የወርቅ ጣዖት እየሠሩ በተራራው ታችኛው ክፍል ላይ ነበሩ። “ሌሎች አማልክት”ን እንደማያመልኩ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ከገቡት ቃል “ፈጥነው ፈቀቅ አሉ” (ዘጸአት 20፥3፤ 32፥8፤ እንዲሁም ዘጸአት 24፥3ን ይመልከቱ)። ይህ አስገራሚ ለውጥ ነበር፣ ነገር ግን እምነት እና ቁርጠኝነት አንዳንድ ጊዜ በትዕግስት ማጣት፣ በፍርሃት ወይም በጥርጣሬ ሊሸነፍ እንደሚችል ከልምድ እናውቃለን። በሕይወታችን ውስጥ የጌታን መገኘት ስንፈልግ፣ ጌታ በጥንቷ እስራኤል ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ እና በምንወዳቸው ሰዎች እንዲሁም በእኛም ተስፋ እንደማይቆርጥ ማወቁ የሚያበረታታ ነው—እርሱ “መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፣ ታጋሽም፣ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት” ነውና (ዘጸአት 34፥6)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኦሪት ዘጸአት 19፥3–6
የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች ለእርሱ ሃብቶች ናቸው፡፡
ፕሬዚደንት ረሰል ኤም ኔልሰን እንዲህ አስተምረዋል፡ “በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተመረጠ ርስት የሚለው ቃል የተተረጎመው ሴጉላህ፣ ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ‘ዋጋ ያለው ንብረት‘ ወይም ‘ሃብት‘ ማለት ነው። በጌታ አገልጋዮች ዘንድ የተመረጠ ርስት ተብሎ መታወቅ ለእኛ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ምስጋና ነው።(“Children of the Covenant፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1995 (እ.አ.አ)፣ 34)። የነቢዩ ኔልሰን ቃላት ዘጸዐት 19:3–6ን በምትረዱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው? ጌታ ሃብቱ እንደሆናችሁ ያሳያችሁ እንዴት ነዉ?
ዘፀአት 19፥10–11፣17
የተቀደሱ ልምምዶች ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል።
ጌታ የእስራኤል ልጆች “ከእግዚያብሄር ጋር ከመገናኘታቸው“ (ዘፀአት 19፥10–17) እና ቃል ኪዳን ከመግባታቸው በፊት መዘጋጀት እንዳለባቸው ለሙሴ ነግሮት ነበር (ዘፀአት19፥5 ይመልከቱ)። ቅዱስ ቁርባንን እና የቤተመቅደስን ስርዓቶችን ጨምሮ ለመንፈሳዊ ልምዶች የምትዘጋጁት እንዴት ነው? ሌሎች እንዲዘጋጁ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? ከሉቃስ 6፡12–13፤ ኢኖስ 1:2-6፤ አልማ 17፡2–3 ስለ ዝግጅት ምን ትማራላችሁ ?
በግብፅ የሚገኘው ይህ ተራራ በተለምዶ የሲና ተራራ እንደሆነ ይታመናል።
ዘጸአት 20፥1–17
የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መታዘዝ በረከቶችን ያመጣል።
እስራኤላውያን በሲና ተራራ ሥር ተሰብስበው በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምፅ አሥርቱን ትእዛዛት ሲሰጥ ሰሙ (ዘዳግም 4፡12–13 ይመልከቱ)። በእርግጥ፣ የእግዚአብሔር ትእዛዛት እነዚህ ብቻ አይደሉም—በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሌሎች ብዙ አሉ። ስለዚህ ዘፀአት 20፡1–17ን በምታነቡበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በእነዚህ በአሥሩ ላይ አፅንዖት የሰጠው ለምን እንደሆነ ራሳችሁን ጠይቁ። በህይወታችሁ ውስጥ የአስርቱን ትእዛዛት አስፈላጊነት ስታሰላስሉ ልትጠቀሙ የምትችሉት ሠንጠረዥ እዚህ ይገገኛል።
|
ትእዛዝ |
በሌላ አነጋገር፣ ጌታ የሚጠይቀኝ… |
ይህንን ትእዛዝ በመኖር የሚመጡ በረከቶች |
|---|---|---|
-
እነዚህን አስር ትእዛዛት ማክበር ኢየሱስ በማቴዎስ 22፡34–40 ላይ የሰጣቸውን ሁለቱን ታላቅ ትእዛዛት እንድትጠብቁ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?
-
ከእግዚአብሔር ልታስቀድሙ ልትፈተኑ የምትችሉባቸው ነገሮች ምንድናቸው? እግዚአብሔርን በማስቀደማችሁ ምን አይነት በረከቶችን አይታችኋል?
-
አሥርቱ ትእዛዛት ከረጅም ጊዜ በፊት የተሰጡ በመሆናቸው ዛሬ ላይ ተግባራዊ መሆን አይችሉም ለሚል ሰው ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ? እንደ መልሳችሁ አካል ከህይወታችሁ ምን ምሳሌዎችን ልታካፍሉ ትችላላችሁ? “How Gentle God’s Commands” ( (መዝሙሮች፣ ቁ. 125) የሚለው መዝሙር የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለሌሎች በምታብራሩበት መንገድ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
-
ጌታ በዘፀአት 20፡6 ላይ የገባውን ቃል በህይወታችሁ እንዴት ፈፀመ?
በየቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፡ ኤዝራ ታፍት ቤንሰን (2014) 37–45 ውስጥ “The Great Commandment—Love the Lord የሚለውን ይመልከቱ)፣ ዳሊን ኤች ኦክስ፣ “No Other Gods,” ሊያሆና ህዳር 2013፣ 72–75፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Commandments,”፣ የወንጌል ላይብረሪ።
ዘጸአት 24፥1–11
ቃል ኪዳን መግባቴ የእግዚአብሔርን ህግ ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆኔን ያሳያል።
ዘጸአት 24፡3–8ን ስታነቡ ከእግዚአብሔር ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አስቡ። የእስራኤል ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በዘመናችን ከሚፈልገው የተለየ የአምልኮ ሥርዓቶችን ያካተተ ቢሆንም አንዳንድ ተመሳሳይነቶችን አስተውላችሁ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ ቁጥር 4፣ 5 እና 8 መሰዊያን፣ የእንስሳት መስዋእትን እና ደምን ይጠቅሳሉ። እነዚህ ነገሮች ምን ሊወክሉ ይችላሉ፣ እንዲሁም ከእናንተ ቃል ኪዳኖች ጋር እንዴት ይዛመዳሉ?
ዘጸአት 32–34
ኃጢአት ከእግዚአብሔር መራቅ ሲሆን ንስሐ ደግሞ ወደ እርሱ መመለስ እና ከክፉ መሸሽ ነው።
ራሳችሁን በእስራኤላውያን ቦታ ለማስቀመጥ ሞክሩ—በምድረ በዳ ናችሁ፣ ሙሴ ለ40 ቀናት ሄዷል እንዲሁም ከከነዓናውያን ጋር በተስፋይቱ ምድር ዙሪያ ግጭት ፊታችሁ እየጠበቃችሁ ነው። (ዘጸአት 32፡1–8 ይመልከቱ)። እስራኤላውያን ለምን የወርቅ ጣዖት የፈለጉ ይመስላችኋል? በዘጸአት 33፥11–17 ውስጥ ሙሴ ጌታን ስለተማጸነው ምን ተነሳሳሽነት ይሰማችኋል?
የእስራኤላውያን ኃጢአት ከባድ ቢሆንም፣ ይህ ታሪክ የእግዚአብሔር ምህረት እና ይቅር ባይነት መልእክትንም ያካትታል። ዘጸአት 34፡1–10 ስለ አዳኙ ምን ያስተምራችኋል? (ዘጸአት 32፡30–32፤ ሞዛያ 14፡4–8፤ 15፡9፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፡3–5 ተመልከቱ)።
ዘጸአት 31፡13-16
ሰንበት ምልክት ነው።
ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዲህ አብራርተዋል፡ “በወጣትነቴ፣ በሰንበት ምን መደረግ እና አለመደረግ እንዳለባቸው ሌሎች ሰዎች ያሰባሰቡትን የስራ ዝርዝር አጠና ነበር። በሰንበት የማደርገው እና የግል አስተያየቴ በሰማይ አባቴና በእኔ መካከል ያለ ምልክት እንደሆነ ከቅዱሳን መጻህፍት የተረዳሁት በኋላ ነበር [ዘጸአት 31፡13፤ ሕዝቅኤል 20:12፣ 20]። ያንን በመረዳት፣ የሚደረጉ እና የማይደረጉ ዝርዝሮች አያስፈልጉኝም። የምሳተፍባቸው ለሰንበት ቀን ትክክል እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ውሳኔ ማድረግ ሲኖርብኝ፣ ለእግዚአብሔር ‘ምን ምልክት ለማሳየት እፈልጋለሁ?’ ብዬ ራሴን እጠይቅ ነበር። ያም ጥያቄ ስለሰንበት ቀን ያለኝን ምርጫ ግልጽ ያደርግልኛል።” (“The Sabbath Is a Delight,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 130)። ሰንበትን በማክበር ለእግዚአብሔር ምን ምልክት ልትሰጡት እንደምትፈልጉ አሰላስሉ።
ዘጸአት 34:1-4
ሙሴ በሰራቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ሙሴ ከተራራው ሲወርድ፣ በድንጋይ ጽላቶች ላይ የተጻፈውን ሕግ አመጣ። እስራኤላውያን ቃል ኪዳናቸውን እንደጣሱ ካወቀ በኋላ ሙሴ ጽላቶችን ሰባበረ (ዘጸአት 31፥18፤ 32፥19ን ይመልከቱ)። በኋላም፣ እግዚአብሔር ሙሴን ሌሎች የድንጋይ ጽላቶች ሠርቶ ወደ ተራራው እንዲወስዳቸው አዘዘው ( ዘጸአት 34፥1–4ን ይመልከቱ)። የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘጸአት 34፥1–2 (ከመፅሐፍ ቅዱስ መግለጫ) የመጀመሪያው የድንጋይ ጽላቶች የእግዚአብሔርን “የቅዱስ ትዕዛዝ” ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ስርአቶች ያካተተ መሆኑን ያብራራል። ሁለተኛው ጽላቶች “የሥጋዊ ትእዛዝት ሕግ” ያካተቱ ነበሩ። ይህም እስራኤላውያንን ወደ እግዚአብሔር ፊት ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ እንዲገቡ ለከፍተኛ ሕግ እና ለከፍተኛ ክህነት ለማዘጋጀት የታቀደ አነስተኛ ህግ ሆኖ በ“አነስተኛ ክህነት” የሚተዳደር ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥17–27 ይመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘጸአት 20፥3–17
ደስተኛ እንድሆን ስለሚፈልግ እግዚአብሔር ትእዛዛትን ይሰጠኛል።
-
ስለ አሥርቱ ትእዛዛት መማር ለልጆቻችሁ አስደሳች እንዲሆን ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ዘፀአት 20፡3–17ን አንድ ላይ ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ እያንዳንዳቸውን አስርቱ ትእዛዛትን የሚወክል ምስል እንድታገኙ ወይም እንዲስሉ እርዱ። ከዚያም ልጆቻችሁ ተራ በተራ ሥዕል መርጠው ትእዛዝን እንዴት መኖር እንደሚችሉ ማውራት ይችላሉ። ያንን ትእዛዝ መኖር ደስታን እንደሚያመጣላችሁ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።
-
እንደ “Keep the Commandments” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 146–47) አይነት ስለ ትእዛዛት መዝሙር አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ ለምን እንደሚፈልግ ልጆቻችሁ ከመዝሙሩ ውስጥ ቃላትን እንዲያገኙ እርዷቸው።
ልጆች መንፈሳዊ ልምዶችን ሲያካፍሉ ምስክርነታቸው ያድጋል። የምትጠይቋቸው ጥያቄዎች ልጆቻችሁ ስለ አዳኙ ስላላቸው ስሜት እና ወንጌልን መኖር እንዴት እንደባረካቸው እንዲያካፍሉ ሊያበረታታቸው ይችላል (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 32 ይመልከቱ)። ይህን ሲያደርጉ ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። አስርቱን ትእዛዛት መኖር የሚያስገኘውን በረከቶች በምትወያዩበት ጊዜ ይህን እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።
ዘፀአት 20፥12፡፡
ጌታ ወላጆቼን እንዳከብር ይፈልጋል።
-
ልጆቻችሁ “አባትህንና እናትህን አክብር” (ዘጸአት 20፥12) የሚለውን ሐረግ እንዲማሩ እርዷቸው። አንድን ሰው “ማክበር” ማለት ለዚያ ሰው አክብሮት ማሳየት ወይም ደስታን ማስገኘት ሊሆን እንደሚችል ማስረዳት ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ምድራዊ እናቱን እና የሰማይ አባቱን ለማክበር ምን አደረገ? (ሉቃስ 2፡48–51፤ ዮሐንስ 19፡26–27 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ተራ በተራ ወላጆቻቸውን ለማክበር ማድረግ የሚችሉትን ነገር ሲተውኑ ሌሎች ልጆች ደግሞ የሚያደርጉትን ይገምቱ።
ዘጸአት 31፥13፤ 16–17
ሰንበትን ማክበር ለጌታ ያለኝ ፍቅር ምልክት ነው።
-
ልጆቻችሁ የምልክቶችን ምሳሌ ሲመለከቱ ደስ ሊላቸው ይችላል—እንደ የመንገድ ወይም በሕንፃ ላይ ያሉ ምልክቶች። የምልክቶች ዓላማ ምንድን ነው? ከዚያም ልጆቻችሁ በዘፀአት 31፡13፣ 16–17 ላይ “ምልክት” የሚለውን ቃል ማግኘት ይችላሉ። ጌታ በእኛና በእርሱ መካከል ምልክት ነው ያለው ምንድነው? እናንተ እና ቤተሰባችሁ በሰንበት ቀን ለጌታ ያላችሁን ፍቅር ለማሳየት የምትሞክሩባቸውን አንዳንድ መንገዶች አንዳችሁ ለሌላው አጋሩ።
ሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት እንደያዘ የሚያሳይ ምስል፣ በሳም ላውሎር (ዝርዝር)
ዘጸአት 32:1–8፣ 19–24፤ 34:6–7
ከእግዚአብሔር መንገድ “ፈቀቅ [አልልም]”።
-
ልጆቻችሁ በዘፀአት 32፡1–8፣ 19–24 የሚገኘውን ታሪክ እንዲማሩ ለመርዳት “ ሙሴን በሲና ተራራ”ን (በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 77–82) ለመጠቀም አስቡ። እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ይልቅ ጣኦት ማምለካቸው ስህተት የነበረው ለምንድን ነው?
2:55Moses on Mount Sinai
-
በዘፀአት 32:8 ላይ “[ከ]መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ” የሚሉትን ቃላት በምሳሌ ለማስረዳት ወለል ላይ መንገድ መፍጠር (ወይም በቤታችሁ አጠገብ ያለውን ማግኘት) አስደሳች ሊሆን ይችላል። በመንገዱ ላይ ስትራመዱ፣ ልጆቻችሁ ከእግዚአብሔር እንድንርቅ ስለሚያጋጥሙን ፈተናዎች ማውራት ይችላሉ። በእግዚአብሔር መንገድ እንድንቆይ—እንዲሁም ካጠፋን እንድንመለስ የሚረዳን ምንድን ነው? ( ዘጸአት 34፡6–7 ይመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።