“ሚያዝያ 13–19 (እ.አ.አ)። ‘ቁሙ፣ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ፣ ዘፀአት 14–18 ‘“ ኑ፣ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)
“ሚያዝያ 13–19 (እ.አ.አ)። “ቁሙ፣ ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ“: ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 13–19 (እ.አ.አ)፤ “ቁሙ፣ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ“
ዘፀአት 14–18
እስራኤላውያን ወጥመድ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ በአንድ በኩል ቀይ ባህር ነበረ በሌላ በኩል ደግሞ የፈርኦን ሰራዊት እየገሰገሰ ነበር፡፡ ከግብጽ የመውጣታቸው ነገር በአጭሩ የሚቀጭ መስሎ ነበረ፡፡ ነገር ግን እግዚያብሄር እስራኤላውያን ለትውልድ ሁሉ እንዲያስታውሱት የሚፈልገው መልዕክት ነበረው: “አትፍሩ … እግዚያብሄር ስለናንተ ይዋጋል” (ዘፀአት 14፥13–14)፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ የእግዚያብሄር ህዝብ እምነት እና ድፍረት ሲያስፈልገው ይህን ታሪክ ይነግር ነበር፡፡ ኔፊ ወንድሞቹን ለማነሳሳት በፈለገ ጊዜ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ”ልክ እንደ ሙሴ ጠንካሮች እንሁን፣ እነሆ እርሱ በእውነት የቀይ ባሕርን ውሃ ተናገረው፣ ውሃውም ወዲያና ወዲህ ተከፈለ፣ አባቶቻችንም በውስጡ ተሻግረው ከግዛት በደረቅ ምድር ወጡ” (1 ኔፊ 4፥2)። ንጉስ ሊምሂ ምርኮኛ ህዝቡ “ራሳ[ቸውን] እንዲያቀኑ እና [እንዲ]ደሰቱ” በፈለገ ጊዜ ይህንኑ ታሪክ አስታውሷቸው ነበር (ሞዛያ 7፥19)። አልማም ለወንድ ልጁ ስለ እግዚያብሄር ሃይል ለመመስከር በፈለገ ጊዜ ይህንኑ ታሪክ ጠቅሶ ነበር( አልማ 36፥28ይመልከቱ)። እኛም ወጥመድ ውስጥ የገባን ሲመስለን—፣ “[ለመቆም] እና የጌታን ማዳን [ለማየት]” ትንሽ ተጨማሪ እምነት ስንፈልግ—“ጌታ በዚያን ቀን እስራኤልን … [እንደ]አዳነ“ ማስታወስ እንችላለን (ዘፍጥረት 14፥13፣ 30)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዘጸአት 14፤ ዘጸአት 15:1–21
እግዚአብሔር በህይወቴ “[ታላቅ ስራን]” መስራት ይችላል።
ዘፀአት 14፥1–10ን ስታነቡ፣ የፈርኦን ሰራዊት በተቃረበ ጊዜ እስራኤላውያን ምን ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል ገምቱ። ምናልባት የተጋፈጣችሁትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለማለፍ ተአምር እንደሚያስፈልጋችሁ ይሰማችሁ ይሆናል። ከዘፀአት14፥13–31 በህይወታችሁ ውስጥ የእግዚያብሄርን ሃይል እንድትፈልጉ የሚያነሳሳችሁን ምን ታገኛላችሁ? የእርሱን ሃይል ከዚህ በፊት እንዴት እንዳያችሁ አሰላስሉ። ከእነዚህ ተሞክሮዎች ስለ እርሱ ምን ተማራችሁ?
ዘጸአት 15፡1-19 እግዚአብሔር ቀይ ባህርን ከከፈለ በኋላ እስራኤላውያን የዘመሩት የምስጋና መዝሙር ነው። በዚህ መዝሙር ውስጥ የትኞቹ ሀረጎች የተለየ ትርጉም ይሰጧችኋል? ምናልባት ጌታ ለእናንተ አንድ አስደናቂ ነገር ሲያደርግላችሁ የምትዘምሩት መዝሙር ይኖራችሁ ይሆናል፣ ለምሳሌ “Redeemer of Israel” (መዝሙሮች፣ ቁ. 6)። እንደአምልኳችሁ አካል አድርጋችሁ ለመዘመርን ወይም ለማዳመጥ አስቡ።
እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8:2–3 ይመልከቱ።
ዘጸአት 15:22–27፤ 16:1–15፤ 17:1–7
ጌታ መራራ ነገሮችን ጣፋጭ ማድረግ ይችላል።
ስለ እስራኤል ጉዞ ማንበብ በህይወታችሁ ውስጥ እንደ ማራ ውሃ “መራራ” ስለሚመስሉ ነገሮች እንድታስቡ ሊያደርጋችሁ ይችላል (ዘፀአት 15፡23–27 ይመልከቱ)። ጌታ በህይወታችሁ መራራ ነገሮችን እንዴት ጣፋጭ አደረገ? እነዚህ ተሞክሮዎች በህይወታችሁ ውስጥ ምን ዋጋ ነበራቸው?
በዘፀአት 16 እና 17 ውስጥ ስለ እስራኤላውያን መራራ ተሞክሮዎች ተጨማሪ ምሳሌዎችን ታያላችሁ። ማጉረምረማቸውን ወይም ቅሬታቸውን ለመተቸት ትፈተኑ ይሆናል፣ ነገር ግን ማንበባችሁን ስትቀጥሉ እናንተም ተመሳሳይ ነገር አድርጋችሁ እንደሆን አስቡ። ከእስራኤላውያን ተሞክሮ ብዙ እንዳታጉረመርሙ እና ይበልጥ በእግዚያብሄር እንድትታመኑ የሚረዳችሁን ምን ትማራላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች ስለእግዚያብሄር ምን ያስተምሯችኋል?
በተጨማሪም 1 ኔፊ 2:11–12 ይመልከቱ።
እስራኤላውያን መና እየሰበሰቡ። ኒዮ-ጎቲክ ፍሬስኮ፣ ትራናቫ (ዝርዝር)
ዘጸአት 16
ጌታ በየቀኑ መንፈሳዊ ምግብ ይሰጠኛል።
ሁላችንም መብላት ስለሚያስፈልገን ጌታ ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ነገሮችን ከምግብ ጋር ያነጻጽራል። በዘፀአት 16 ውስጥ እስራኤላውያን ከመና ጋር ስለነበራቸው ተሞክሮ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ፈልጉ። ለምሳሌ፣ በዘጸአት 16፡16፣ 19፣ 22–26 ላይ ጌታ በሰጠው መመሪያ ውስጥ ከመንፈሳዊ ምግብ ጋር የሚያያዝ ምን ታገኛላችሁ?
ጌታ ከዚህ ተአምር እንድትማሩ የሚፈልጋቸውን ሌሎች ትምህርቶች ለማግኘት የሚከተሉትን ጥያቄዎች አሰላስሉ፡
-
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንደ ሰጣቸው የዕለት ተዕለት መና አይነት ምን ይሰጠኛል?
-
መናን እንደ መሰብሰብ ያለ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ከእነዚህ ቪዲዮዎች ውስጥ በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑት ውስጥ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላችሁ፡ “Daily Bread: Pattern,” “Daily Bread: Experience,” እና “Daily Bread: Change” (ወንጌል ላይብረሪ)።
Daily Bread: Pattern
Daily Bread: Experience
Daily Bread: Change
ከመብላት በተጨማሪ በየቀኑ ስለምታደርጓቸው ሌሎች ነገሮችን አስቡ። ውጤታማ ለመሆን አንዳንድ ነገሮች በየቀኑ መደረግ ያለባቸው ለምንድነው? በየዕለቱ መንፈሳዊ ልምዶችን ለመፈለግ ምን ለማድረግ አነሳሽነት ይሰማችኋል?
በተጨማሪ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “Daily Restoration,” ሊያሆና፣ ህዳር 2021፣ 77–79፣ ይመልከቱ። “Daily Restoration” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ።
Daily Restoration
ዘጸአት 17፥1–7
ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ አለቴ እና ህያው ውሃዬ ነው።
ዘጸአት 17፥1–7ን ስታነቡ ስለ አዳኙ አስቡ። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ እንደ አለት የሆነው እንዴት ነው (መዝሙር 62፥6–7፤ ሄለማን 5፥12ን ይመልከቱ)። እንደ ውሃ የሆነው እንዴት ነው? ( ዮሃንስ 4፥10–14፤ 1 ቆሮንቶስ 10፥1–4፤ 1 ኔፊ 11፥25ን ይመልከቱ)።
ስለ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ቁሳዊ ነገሮችን ፈልጉ። ቅዱሳት መጻህፍት እንደ ዘጸአት 17፡1–7 የኢየሱስ ክርስቶስ ምልክቶች ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ሲገልጹ፣ ለቁሳዊ ትምህርት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ድንጋይን ወይም ውሃን መንካት ወይም መመልከት እነዚህ ነገሮች ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደሚመስሉ ለመረዳት ቀላል ሊያደርግ ይችላል። በመማር ውስጥ የተለያዪ የስሜት ህዋሳትን ማካተት ከቻላችሁ የበለጠ የማይረሱ እና ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ይሆናሉ።
ዘጸአት 17:8–16፤ 18:13–26
ደቀ መዛሙርት የጌታን ሥራ ለመሥራት አንዳቸው የሌላውን “[ሸክም በመሸከም]” ይረዳዳሉ።
በህይወታችሁ ሌሎች በእናንተ ላይ ሲደገፉ ነገር ግን “እጆ[ቻችሁ] ከብደ[ው]” (ዘጸአት 17፡12) የነበረበት ጊዜ ሙሴን እንድትረዱት አድርጓችሁ ሊሆን ይችላል። በሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ሙሴን እንደደገፉት እንደ አሮን፣ ሑር እና ዮቶር ልትሆኑ ትችላላችሁ። ዘጸዐት 17:8–16; 18:13–26 ስታነቡ በእነዚህ ሰዎች ቦታ ራሳችሁን አስቀምጡና ጌታ ስለ ስራው የሚያስተምራችሁን ተመልከቱ።
በተጨማሪም ሞዛያ 4:27፤ 18:8–9 ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዘጸአት 14:5–22
እግዚአብሔር በህይወቴ “[ታላቅ ስራን]” መስራት ይችላል።
-
ቀይ ባሕርን በከፈለ ጊዜ ሙሴና እስራኤላውያን ጌታ ምን ያህል ኃያል እንደሆነ አይተዋል። በዘጸአት 14፡5–22 ያለውን ታሪክ ለመተወን የሚያስደስት መንገድ እንድታስቡ ልጆቻችሁ እንዲረዷችሁ አድርጉ (በተጨማሪም “ፋሲካ” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 70–74 ይመልከቱ)። ምናልባት ወንበሮችን ወይም ብርድ ልብሶችን በማዘጋጀት እንደ ቀይ ባህር “[መክፈል]” ትችላላችሁ። ከዚያም በሕይወታችሁ ውስጥ የእግዚአብሔርን ኃይል እንዴት እንዳያችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።
2:54The Passover
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፡2-3 በዘፀአት 14 ላይ ስላለው ታሪክ ምን መረዳት ይጨምራል? ለልጆቻችሁ መንፈስ ቅዱስ በአእምሯችሁ ወይም በልባችሁ ውስጥ የሆነ ነገር ስለነገራችሁ ጊዜ ልምድ ለመናገር አስቡ እንዲሁም ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ ጋብዟቸው። እንደ “Let the Holy Spirit Guide” (መዝሙሮች፣ ቁ. 143) ስለ መንፈስ ቅዱስ መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።
ዘጸአት15:22–25
ጌታ መራራ ነገሮችን ጣፋጭ ማድረግ ይችላል።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ዘፀአት 15፡22-25ን አብራችሁ ስታጠኑ ጣፋጭ እና መራራ ነገር ልትጠጡ ትችላላችሁ። አዳኙ በሕይወታችን ውስጥ “መራራ” ነገሮችን “ጣፋጭ” ያደረገው እንዴት ነው?
ዘጸአት 15:23–25፤ 16:14–15፤ 17:1–6
ኢየሱስ የሕይወት ውሃዬ፣ የሕይወቴ እንጀራ እና ዐለቴ ነው።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ዘፀአት 15:23–25፤ 16:14–15፤ 17:1–6ን ስታነቡ እንደ ቅርንጫፍ (በማራ ያለውን ውሃ ለመፈወስ)፣ ገንቦ ወይም እንስራ (መና የሚሞላበት) እንዲሁም ድንጋይ (በኮሬብ ላለው ውሃ) ያለን ለእያንዳንዱ ታሪክ የሚጠቅም ነገር እንድታገኙ እንዲረዷችሁ አድርጉ። እነዚህ ታሪኮች ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሚያደርግልንን የሚያስታውሱን እንዴት ነው? እንደ ውይይታችሁ አንድ አካል ማቴዎስ 7:24–27 ዮሃንስ 4፥10-14፤ 6፥29–35፣ 48–51፤ ሄላማን 5፥12፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79ን ልታነቡ ትችላላችሁ።
በእግዚአብሄር ፊት አንድ፣ በጆሴፍ ብሪኪ (ዝርዝር)
ዘጸአት 17:8–16፤ 18:13–26
የጌታን ስራ የመስራትን ”ሸክም በመሸከም” መርዳት እችላለሁ።
-
ዘፀአት 17:8–16ን ስታነቡ አንድ ልጅ እጁን አየር ላይ ወደ ላይ ከፍ እንዲያደርግ ልትጋብዙ ትችላላችሁ። ልጁ ሲደክም አሮንና ሁር ሙሴን እንዳገዙት ሁሉ ሌሎች ልጆች ሊረዱት ይችላሉ። የእግዚአብሄር መንግሥት ስኬታማ እንድትሆን እንዴት መርዳት እንደምንችል ይህ ታሪክ ምን ያስተምራል? እንዲሁም ዘፀአት 18፡13–26ን ማንበብ እና በቅርንጫፋችሁ ውስጥ ስለሚያገለግሉ ሰዎች ከባድ ሀላፊነቶች ማውራት ትችላላችሁ። አሮንና ሑር ነቢዩ ሙሴን እንደረዱት የቤተክርስቲያናችንን መሪዎች ለመርዳት ዛሬ ምን ማድረግ እንችላለን?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።