ኑ፣ ተከተሉኝ
ሚያዝያ 6–12 (እ.አ.አ)። “ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ“፡ ዘጸአት:7-13


“ሚያዝያ 6–12 (እ.አ.አ)። ‘ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፣’ ዘጸአት:7-13“ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች:ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026)

“ሚያዝያ 6–12 (እ.አ.አ)። ‘ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፣’“ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች:ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ሙሴ እና አሮን በፈርኦን ቤት

ሙሴ እና አሮን በፈርኦን ቤት ምስል በሮበርት ቲ. ባሬት

ሚያዝያ 6–12 (እ.አ.አ): “ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ“

ዘፀአት 7–13

ተከታታይ ቸነፈር ግብጽን ቢያጎሳቁላትም አሁንም ፈርኦን እስራኤላውያንን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሆኖም እግዚያብሄር ሃይሉን ማሳየቱን እና “እኔ እግዚያብሄር እንደሆንኩ“ እና “በምድር ሁሉ እንደኔ ያለ እንደሌለ“ የሚለውን ፈርኦን እንዲቀበል አጋጣሚ መስጠቱን ቀጠለ፡፡(ኦሪት ዘፀአት 7፥59፥14) ይህ በእንዲህ እንዳለ ሙሴ እና እስራኤላውያን ስለነሱ የሚደረጉትን እነዚህን የእግዚአብሄር ሃይል መገለጫዎች ያዩት በአድናቆት መሆን አለበት፡፡ በርግጠኝነት፣ አነዚህ እየቀጠሉ የነበሩት ምልክቶች በእግዚአብሄር ላይ ያላቸውን እምነት በማረጋገጥ የእግዚያብሄርን ነቢይ የመከተል ፍላጎታቸውን አጠናክረዋል፡፡ ከዚያም፣ ዘጠኝ አስፈሪ መቅሰፍቶች እስራኤላውያንን ለማስለቀቅ ባለመቻላቸው፣ አስረኛው ቸነፈር—የፈርኦንን የበኩር ልጅ ያካተተው የበኩር ልጅ ሞት—በመጨረሻ ምርኮው እንዲጠናቀቅ አደረገ። ይህ ተገቢ ይመስላል ምክንያቱም በእያንዳንዱ መንፈሳዊ ምርኮ በእውነት አንድ ብቻ ማምለጫ መንገድ አለ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት፣ በበኩር ልጅ፣ ያልረከሰ የበግ ደም—ብቻ ሊያድነን ይችላል።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኦሪት ዘፀአት 7–11

የሚራራ ልብ እንዲኖረኝ መምረጥ እችላለሁ።

ፈቃዳችሁ ልክ እንደ ፈርኦን የእግዚአብሄር ፈቃድ ፈጽሞ እንደማይቃወም ተስፋ ይደረጋል። ያም ሆኖ ሁላችንም ልባችን የምንፈልገውን ያህል ርህሩህ የማይሆንበት ጊዜ አለ። በዘጸአት 7፡14–258:5–329:1–2610:12–2912:29–33፣ ፈርዖን ለመቅሰፍቶቹ በሰጠው ምላሽ ምን ጎልቶ ይታያችኋል? በጆሴፍ ስሚዝ የዘፀአት 7፡3፣ 139:12 ትርጉም ላይ ያለውን ማብራሪያ አስተውሉ።

“[ደንዳና]” የሚለው የፈርዖን ልብ ጥሩ መግለጫ የሆነው ለምንድነው? ስለ ርሁሩህ ልብ ከእነዚህ ቁጥሮች የምትማሩትን አስቡ፡ 1 ኔፊ 2፡16ሞዛያ 3:19አልማ 24፡7–862:41ኤተር 12፡27። የፈርዖን ልበ ደንዳናነት ያስከተለውን መዘዝ ስታነቡ የልባችሁን ሁኔታ አስቡ። ምን ለውጦችን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

ዘፀአት 12፥1–42

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢያት ክፍያው ምክንያት ሊያድነኝ ይችላል።

ዘፀአት 11፥4–5 ውስጥ ከተገለጸው ከአስረኛ መቅሰፍት መዳኛው ብቸኛ መንገድ ጌታ ለሙሴ የሰጠውን የፋሲካ ስርአት በመባል የሚታወቀውን በኦሪት ዘፀአት12 ውስጥ ያለውን መመሪያ በትክክል መከተል ነበር። ፋሲካ በምልክቶች አማካኝነት ልክ ጌታ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት እንዳወጣቸው እኛንም ከሃጢያት ባርነት እንደሚያወጣን ያስተምረናል። በዘፀአት 12፡1-42 ውስጥ ያለውን ይህን ምልክት ለማጥናት እንደዚህ አይነት ቻርት መጠቀም ትችላላችሁ፡

ምልክት

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ለእኔ የእግዚአብሔር መልእክት

ምልክት

የወሮች መጀመሪያ (ቁጥር 2፤ ይህን ክስተት ጌታ እስራኤላውያን የቀን መቁጠሪያቸውን መጀመሪያ በማድረግ እንዲጠቀሙ አዘዛቸው)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ይህ ለእስራኤል አዲስ ጅማሬ ነበር። “ዳግመኛ መወለድ” ነበረባቸው።

ምልክት

ጠቦት (ቁጥር 3-5)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ዮሐንስ 1:296:541 ጴጥሮስ 1፡19

ምልክት

የጠቦቱ ደም በበሩ መቃን ላይ (ቁጥር 7፣ 13፣ 23)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ሞዛያ 4፡2ራእይ 12:11 ተመልከቱ።

ምልክት

የቂጣ እንጀራ (ቁጥር 8፣15፣19-20)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

እርሾ በቀላሉ ስለሚበላሽ የመርከስ ምልክት ሊሆን ይችላል። ማቴዎስ 16:6–12 ዮሐንስ 6፡35ይመልከቱ።

ምልክት

መራራ ቅጠል (ቁጥር 8)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

የኃጢአት እና የምርኮ መራራነት ማስታወሻ። ዘጸአት 1:14ሙሴ 6፡55 ይመልከቱ።

ምልክት

ለመውጣት በመልበስ በችኮላ መብላት፣ (ቁጥር 11)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ከኃጢአት ምርኮ ለመውጣት የችኮላ ምልክት። ዘፍጥረት 39:122 ጢሞቴዎስ 2፡22 ይመልከቱ።

ምልክት

አጥፊው (ቁጥር 13፣23)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፡18–21 ተመልከቱ።

ምልክት

እስራኤላውያን ነጻ ወጡ (ቁጥር 29–32)።

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

2 ኔፊ 2፡26ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፡15–19፣ 31 ተመልከቱ።

በፋሲካ መመሪያዎች እና ምልክቶች ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የሃጢያት ክፍያውን የሚታስታውሳችሁ ሌላ ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ ምልክቶች የሃጢያት ክፍያውን በረከቶች እንዴት እንደምትቀበሉ ምን ይጠቁሟችኋል?

ስለ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ምልክቶችን በመለየት ወደ እርሱ ኑ። ጌታ “ሁሉ[ን]ም ነገሮች” “የፈጠርኳቸው እና የሰራኋቸው ስለእኔ እንዲመሰክሩ ነው” ብሎ ተናግሯል (ሙሴ 6፥63፤ እንዲሁም 2ኛ ኔፊ 11፥4 ይመልከቱ)። በዘፀአት 12፣ እንደ ጠቦት፣ ደም፣ ያልቦካ ቂጣ፣ ተአምራት እና ነጻ የመውጣት ምልክቶች በሙሉ ወደ ክርስቶስ ያመለክታሉ። “እነዚህ ነገሮች ከአዳኙ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ከተረዳን፣ ስለኃይሉ እና ስለባህሪያቱ ሊያስተምሩን ይችላሉ” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 7)

ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን ለደቀ መዛሙርቱ እየሰጠ

እኔን በማሰብ፣ በዋልተር ሬን

ዘጸአት 12፥14–27፣24–2713፥1–16

ቅዱስ ቁርባን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት መዳኔን እንዳስታውስ ይረዳኛል።

አዳኙ እስራኤላውያን እንዳዳናቸው ለማስታወስ እንዲረዳቸው ምንም እንኳን ምርኮአቸው የሩቅ ትውስታ ከሆነ በኋላም ቢሆን በየዓመቱ ፋሲካን እንዲያከብሩ አዟቸዋል። በዘጸአት 12፥14–17፣24–2713፥1–16ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ስታነቡ እግዚአብሄር የሰጣችሁን በረከቶች ለማስታወስ ምን እያረጋችሁ እንደሆነ አስቡ። ያንን መታሰቢያ “ለልጅ ልጃችሁ“ ማቆየት የምትችሉት እንዴት ነው? (ዘጸአት 12፥14፣ 26–27ይመልከቱ)።

በፋሲካ እና በቅዱስ ቁርባን መካከል ምን ተመሳሳይነት ትመለከታላችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስን “ሁል ጊዜ [ለማስታወስ] ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (ሞሮኒ 4፥35፥2)።

ጌታ እንድታስታውሱ የሚፈልጋቸውን ሌሎች ነገሮችንም ልታሰላስሉ ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ ሄለማን 5፥6–12ሞሮኒ 10፥3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥3–5፣ 1018፥1052፥40

በተጨማሪም ኬቨን ደብሊው ፒርሰንን፣ “Are You Still Willing?,” ሊያሆና፣ ህዳር 2022፣ 67–69 “Always Remember Him” (ቪዲዮ)፣ በወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ። ፤ “In Memory of the Crucified,” መዝሙሮች፣ ቁ.190።

5:27

Always Remember Him

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ዘፀአት 7–11

ጌታ በሁሉ ነገር ላይ ሃይል አለው።

  • ዘፀአት 7-11 የተገለጹት መቅሰፍቶች ለግብፃውያን እና ለእስራኤላውያን ጌታ ታላቅ ኃይል እንዳለው አሳይተዋል። ልጆቻችሁ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ በኃይሉ ላይ እምነት ሲኖራቸው ጌታ ይረዳቸዋል። ከዚህ ታሪክ እንዲማሩ ለመርዳት ለእያንዳንዱ ልጅ 10 ቦታ የተከፈለ ወረቀት መስጠት እና በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጹትን መቅሰፍቶች ሥዕል እንዲስሉ መጋበዝ ትችላላችሁ፡ ዘጸአት7:17–188:1–48:16–178:20–229:1–69:8–99:22–2310:4–510:21–2211:4–7 (በተጨማሪም “የግብፅ መቅሰፍቶች” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 67–69 ይመልከቱ።) እግዚአብሔር መቅሰፍቶችን የላከበትን ምክንያት ለማብራራት ዘጸአት 7፡5 እና 9፡14ን አብራችሁ አንብቡ።

    2:3

    The Plagues of Egypt

  • “በምድር ሁሉ እንደ [እርሱ] ያለ እንደሌለ” (ዘጸአት 9፡14) ጌታ እንዴት እንዳሳያችሁ ለልጆቻችሁ አካፍሉ። ጌታ ኃያል መሆኑን እንዴት እንደሚያውቁ እንዲያካፍሉ አድርጓቸው።

ዘጸአት 8:28–329:7

ጌታ የሚራራ ልብ እንዲኖረኝሊረዳኝ ይችላል።

  • ልጆቻችሁ የሚራራ ልብ ምን ማለት እንደሆነ በዓይነ ሕሊናቸው እንዲገነዘቡ ለመርዳት ጠንካራ የሆነን ነገር፣ ለምሳሌ እንደ ድንጋይ እንዲሁም ሌላ እንደ ስፖንጅ ያሉ ለስላሳ እና የሚመጡ ነገሮችን ማሳየት አስደሳች ሊሆን ይችላል። የሚራራ ልብ የጌታን ቃል እንዴት በቀላሉ እንደሚቀበል ለማሳየት በእነዚህ ነገሮች ላይ ውሃ ማፍሰስ ትችላላችሁ። ከዚያም ፈርዖን ከጌታ ለተላኩ መቅሰፍቶች እንዴት ምላሽ እንደሰጠ የሚገልጹ ጥቂት ጥቅሶችን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ (ዘጸአት 8፡28–329፡7 ተመልከቱ)። ከዕቃዎቹ ውስጥ የፈርዖንን ልብ ወይም አመለካከት በተሻለ ሁኔታ የሚወክለው የትኛው ነው? የሚራራ ልብ ሲባል ምን ማለት ነው? (ሞዛያ 3፡19 ይመልከቱ)።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ልባችን ሲደነድን (ለምሳሌ ደግነት የጎደላቸው ቃላትን መጠቀም ወይም ለማካፈል ፈቃደኛ አለመሆን) ልናሳይ የምንችላቸውን አንዳንድ ድርጊቶች መዘርዘር ትችላላችሁ። የሚራራ ልብ እንዲኖረን እንደምንፈልግ ጌታን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ቅዱስ ቁርባንን እየወሰደ ያለ ቤተሰብ

ዘጸአት 12፡1-13

ቅዱስ ቁርባን ኢየሱስን እንዳስታውስ ሊረዳኝ ይችላል።

  • ፋሲካ እስራኤላውያን አዳኙንና ለእኛ የከፈለውን መስዋዕትነት እንዲጠባበቁ አስተምሯቸዋል። ዘጸአት 12፡1–13ን አንድ ላይ ስታጠኑ ልጆቻችሁ በፋሲካ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ዝርዝሮች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲያዩ እርዷቸው (በተጨማሪም ““ፋሲካ”፣ በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች ፣ 70–74 የሚለውን ተመልከቱ)። ለምሳሌ፣ ኢየሱስ በቁጥር 5 ላይ እንደተገለጸው አይነት በግ የሆነው እንዴት ነው?

    2:54

    The Passover

  • ዛሬ፣ የኢየሱስን መስዋዕትነት ለማስታወስ ቅዱስ ቁርባንን እንካፈላለን። ለልጆቻችሁ የቅዱስ ቁርባንን ምስል ማሳየት እና ይህ ስርዓት ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ እንዴት እንደሚረዳን መናገር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በቅዱስ ቁርባን ጸሎት ውስጥ “እንደሚያስታውሱ” (ሞሮኒ 4–5 ይመልከቱ) የሚለውን ቃል እንዲያገኙ መርዳት ትችላላችሁ። ወይም ስለ ቅዱስ ቁርባን የምትወዱትን መዝሙር አብራችሁ ዘምሩና ልጆቻችሁ ስለ አዳኙ በሚያስቡበት ጊዜ የሚሰማቸውን ሰላማዊ ስሜት እንዲያስተውሉ እርዷቸው። ያንን ስሜት ቅዱስ ቁርባንን ስንካፈል እንዴት መፈለግ እንችላለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።

የፋሲካ እራት ስዕል

የፋሲካ እራት፣ በብራይን ኮል

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡- ቅዱስ ቁርባን ኢየሱስን እንዳስታውስ ይረዳኛል።