የሚያሳጣኝ የለም፣ በዮንግሳንግ ኪም በሄቭንላይት የቀረበ
5.
በጉዞአችሁ የእግዚአብሔርን ብርሃን ተከተሉ
ገላትያ 5፥25
ነገሮችን በግልፅ ማየት ስትችሉ የተሻሉ ምርጫዎችን ታደርጋላችሁ። ለዚያም ነው ብርሃን በጣም አስፈላጊ የሆነው ፦ ብርሃን ትክክለኛውን መንገድ ለማየት ቀላል ያደርጋል። የሰማይ አባት መልካሙንና መጥፎውን፣ ትክክልና ስህተትን በግልፅ እንድትመለከቱ እንዲረዳችሁ የሰማዩ የብርሃን ምንጭ ማለትም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሰጥቷችኋል።
ዘለአለማዊ እውነቶች
መንፈስ ቅዱስን እንደ ቋሚ ጓደኛ ማድረግ ትችላላችሁ። የቤተክርስቲያኗ አባል መሆናችሁ በተረጋገጠ ጊዜ “መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ” ተጋብዛቹሃል። መንፈስን እንደ ቋሚ ጓደኛችሁ የማግኘት እድል እግዚአብሔር ለእናንተ ከሚሰጣቸው ታላላቅ ስጦታዎች አንዱ ነው።
ጥሩ ምርጫ ማድረግ መንፈስን የመስማት ችሎታችሁን ያሻሽላል። በዚህ ዓለም ውስጥ ብዙ ጥሩ እና ጠቃሚ ነገሮች አሉ። በምትበሉትና በምትጠቱት ነገር ሰውነታችሁ እንደሚጎዳ ሁሉ፣ የምታነቡት፣ የምታዩት እና የምትሰሙት ነገሮች በአዕምሮአችሁ እና በመንፈሳችሁ ላይ በእጅጉ ተጽዕኖ ያሳድሩባችኋል።
ግብዣዎች
በየቀኑ ለጌታ ጊዜ ስጡ። ከእርሱ ተማሩ። ሁልጊዜ እርሱን አስታውሱ። ወደ ሰማይ አባት ጸልዩ። ቅዱሳት መጻህፍትንና የኋለኛው ቀን ነቢያትን ቃላት አጥኑ። ከዚያም በተማራችሁት መሠረት ለመኖር ጣሩ።
መንፈስን የሚያነሳን፣ የሚያነቃቃን እና የሚጋብዝን ነገር ፈልጉ። ምን ማየት፣ ማንበብ፣ ማዳመጥ ወይም መሳተፍ እንዳለባችሁ ምርጫን ስታደርጉ ምን እንደሚሰማችሁ አስቡ። ጥሩ ሀሳቦችን ይጋብዛል? በተቀደሱ ነገሮች ላይ ከሚያፌዝ ወይም ሥነ ምግባር ከጎደለው ነገር ራቁ። እንደ አመጽ፣ አልኮል እና ጎጂ እጾች አይነት ውሳኔዎቻችሁን ወይም ለመንፈስ ያላችሁን ስሜት በሚያደበዝዝ በማንኛውም ነገሮች ውስጥ አትሳተፉ። ቪዲዮን ወይም መጫወቻን ለማጥፋት፣ ከፊልም ወይም ከዳንስ ለመውጣት፣ ሙዚቃን ለመቀየር ወይም ከመንፈስ ጋር ከማይጣጣም ከማንኛውም ነገር ለመራቅ ድፍረት ይኑራችሁ።
ማህበራዊ ሚዲያን ለማነሳሳት ተጠቀሙበት። ማህበራዊ ሚዲያ ኃይለኛ የመገናኛ መሳሪያ ሊሆን ይችላል። የምትጠቀሙት ከሆነ፣ በብርሃን፣ በእምነት እና በእውነት ላይ አተኩሩ። ሕይወታችሁን ሌሎች ሰዎች እያጋጠሟቸው ካሉ ነገሮች ጋር አታነጻጽሩ። ብቁነታችሁ የሰማይ ወላጆች ልጅ በመሆን ላይ የሚመካ ነው እንጂ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚመጣ እንዳልሆነ አስታውሱ።
ጤናማ ልምዶችን እና እውነተኛ፣ ዘላቂ ግንኙነቶችን ፈልጉ። የቴክኖሎጂ እና የሚዲያ አጠቃቀማችሁ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር በአካል የምታሳልፉትን ጊዜ እንዳይሻማ ተጠንቀቁ። ማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በምላሹ ብዙ ዋጋ ሳይሰጡ ብዙ ጊዜአችሁን ሊወስዱ ይችላሉ። ከምናባዊው ዓለም ዕረፍት ውሰዱ እንዲሁም በእውነተኛ ህይወት ካሉ ሰዎች ጋር ተገናኙ።
ቃል የተገቡ በረከቶች
መንፈሱ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ሊኖር ይችላል። ይህ ቃል ቅዱስ ቁርባን በተካፈላችሁ ቁጥር የምትገቡት ቃል ኪዳን አካል ነው። መንፈስ ለእናንተ ስለ ሰማይ አባት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል። እርሱም ያፅናናችኋል፣ ይመራችኋል፣ ያስጠነቅቃችኋል እንዲሁም ይቀድሳችኋል። እውነትን እንድታውቁና በዓለም ውስጥ ያለውን መልካም ነገር እንድታስተውሉ ይረዳችኋል።
ጥያቄዎች እና መልሶች
ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ስሜት እየተሰማኝ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የመንፈስ ስሜትን ለመገንዘብ ጊዜን፣ ልምምድን እና ትዕግስትን ይጠይቃል። እርሱም ለተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ይናገራል። የአንድን ሰው ምስክርነት በማዳመጥ የሚሰማችሁን ሰላማዊ ስሜት ወይም የተሳሳተ ምርጫ ካደረጋችሁ በኋላ የሚሰማችሁን ያልተረጋጋ ስሜት የመሳሰሉትን ቀላል ነገሮች ችላ አትበሉ። መንፈስ የሚናገርባቸውን የተለያዩ መንገዶች ለማግኘት ቅዱሳት መጻህፍትን አጥኑ፣ ስለእነርሱ ጸልዩ እንዲሁም የመንፈስ ስሜት የሚያሰማችሁ አጋጣሚዎችን ፈልጉ።
የብልግና ምስል ምንድን ነው? ለምንስ ይህን ማስወገድ አለብኝ? የብልግና ምስል ወሲባዊ ስሜቶችን ለመቀስቀስ የተነደፈ በስዕሎች ወይም በቃላት የተነደፈ መግለጫ ነው። የብልግና ምስሎች ቪዲዮዎችን፣ ሥዕሎችን፣ መጻሕፍትን፣ ጨዋታዎችን እና ሙዚቃዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ይመጣሉ። እንዲሁም በጓደኞች መካከል የተላኩ መልዕክቶች ወይም ምስሎች ሊሆኑ ይችላሉ። የብልግና ምሥሎች የተቀደሱ ነገሮችን ማለትም ሥጋዊ አካላችንንና የጾታዊ ስሜታችንን ያንቋሽሻሉ። ሳታስቡ የብልግና ምሥሎች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ። ሆን ብላችሁ ሆነ ሳታውቁ የብልግና ምሥሎችን ከተመለከታችሁ ወዲያውኑ መመልከታችሁን አቁሙ። እንዲሁም ወላጅን ወይም ሌላ ታማኝ አዋቂን ለማነጋገር ትፈልጉም ይሆናል። ሆን ብሎ የብልግና ምስሎችን መመልከት ኃጢአት ነው እንዲሁም መንፈስን የመሰማት ችሎታን ይጎዳል። ራስን መግዛትን ያዳክማል እንዲሁም ራሳችሁን እና ሌሎችን የምታዩበትን መንገድ ያዛባል። ኢየሱስ ክርስቶስ የብልግና ምስሎችን እንዳትመለከቱ እና ንስሐ እንድትገቡ የመርዳት ኃይል አለው። ወደ እርሱ ተመለሱ እና ከጨለማም ራቁ። ኤጲስ ቆጶሳችሁ በአዳኙ በኩል ጥንካሬን እና ይቅርታን እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበታችሁ ነው።
መዝሙር 119፥105 (የእግዚአብሔር ቃል በመንገዳችን ላይ እንደ ብርሃን ነው)፤ አሞጽ 5፥14 (መልካሙን ፈልጉ)፤ ገላትያ 5፥22–23፤ (የመንፈስ ፍሬዎች)፤ ሞሮኒ 7፥18–19 (የክርስቶስ ብርሃን)፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥23 (ጌታ ሰላም ይናገራል)፤ 20፥77፣ 79 (የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶችን) ተመልከቱ።
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለማግኘት የሚጠየቅ ጥያቄ
-
ጌታ እንዲህ ብሏል ሁሉም ነገሮች በፊቴ “በንጽህና ይሰሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥41)። በአስተሳሰብህ/ሽ እና በባህሪህ/ሽ ውስጥ የሥነ–ምግባር ንጽህና እንዲኖርህ/ርሽ ጥረት ታደርጋለህ/ታደርጊያለስሽ?